>

ለወልቃይትና አካባቢው ችግር ዘላቂ መፍትሔው ምን ይሆን ? (ደረጀ መላኩ -የሰብአዊ መብት ተሟጋች)

ለወልቃይትና አካባቢው ችግር ዘላቂ መፍትሔው ምን ይሆን ?

 

ደረጀ መላኩ -የሰብአዊ መብት ተሟጋች

እንደ መግቢያ

በአሁኑ ግዜ ወደ ተባበረችው አሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት እየተገፉ ያሉት ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 (When looking at the Senate and House bills, HR. 6600 and S. 3199በሰሜን ኢትዮጵያ የተለኮሰውን ግጭት ለማብረድ ከወያኔ ጋር ሰለሚደረገው ውይይት፣ ወዘተ ዘወተ ስናስብ አንድ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኝ ስትራቴጂክ ስፍራ ዋነኛ የውይይቱ ማእከል ነው፡፡ ይህም የወልቃይት፣ጸገዴ ጸለምት ምድር ነው፡፡ 

ሁላችንም እንደምናውቀው ይህ ስፍራ ላለፉት ሰላሳ አመታት በወያኔ በሀይል ቁጥጥር ስር ወድቆ ነበር፡፡ በዚህ ግዜ ሰው ሰራሽ ድንበር ተበጅቶለት ነበር፡፡ ይህም በምእራብ ትግራይ የሚገኝ አንድ አካባቢ እንደሆነ በተደጋጋሚ ግዜ ሲነገር የተሰማ ጉዳይ ነው፡፡ 

ይህ ሰፊ ግዛት ሱዳንና ኤርትራን የሚያዋስን ሲሆን ለእርሻ ተስማሚ፣በማእድን ሀብትም የታደለ ነው፡፡

በነገራችን ላይ በረጅም ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የትግራይ ወንድሞቻችን ወደ አካባቢው በመምጣት ኖረዋል፡፡ ወልደው ከብደዋል፡፡ በአካባቢው ትግርኛም አማርኛም የሚናገሩ ኢትዮጵያውያን ሞልተው ተርፈዋል፡፡ እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1980ዎቹ ወታደራዊ የደርግ መንግስትን ሲፋለሙ የነበሩት ያንዬ የነጻ አውጪ ድርጅት ስያሜ የነበራቸው የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት አባላት የጦር መሳሪያ ከሱዳን ድንበር ይቀርብላቸው የነበረው በወልቃይት በኩል እንደነበር ከታሪክ እንማራለን፡፡

.ለአለም ችግር ዘላቂው መፍትሔ ምን ይሆን ?

እኛ የሰው ልጆች ለችግሮች መፍትሔ ለማግኘት የዳበረ ልምድ አለን ብዬ አስባለሁ፡፡ የእኛ እውቀት፣ በደመነፍስ፣ አንድን ነገር ወዲያውኑ የመረዳት ችሎታችን ለችግራችን መፍትሔ የማግኘት ችሎታ አዳብሮልናል፡፡ ለዚህም ነው ጊዜ በነጎደ ቁጥር የሰው ልጅ ሕይወት እየተሻሻለ የመጣው፡፡ በእርግጥ የሰው ልጅ ለችግር መፍትሔ ከመፈለግ አንጻር ያለው ችሎታ ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ጥንታዊው ሰው እሳትን ፈጥሯል፣ ከዚህ ባሻግር እሳትን ምግብ ለማብሰል ይጠቀምበት ነበር፣ በአስቸጋሪ የአየር ጸባይ ውሰጥ መኖር ችሏል( አስቸጋሪ የአየር ጸባይን ተቋቁሞ ኖሯል ወይም እየኖረ ነው፡፡) ፣ ራሱን ከአስፈሪና ጎጂ አራዊት ተከላክሏል፣ ወዘተ ወዘተ ከዚህ ባሻግር ዘመናዊው የሰው ልጅ ማሽኒችንና ሮቦቶችን በመፈልሰፍ  ለህይወት እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ቁሶችን አምርቷል፡፡ የቴክኖሎጂ ውጤት የሆነው የትራንስፖርቱ አለም፣ አለምን አንድ መንደር አስመስሏታል፡፡ ከአንዱ የአለም ክፍል ወደ ሌላው የአለም ክፍል በቀላሉ መድረስ ተችሏል፡፡ በአንዱ የአለም ጥግ የተፈጸሙ ድርጊቶች በአጭር ግዜ ውስጥ ወደ ሌላኛው የአለም ጥግ ይሰማሉ፡፡ የአለም መንደር እየተባለ መጠራት ተጀምሯል፡፡ በሌላ አነጋገር በአንዱ የአለም ክፍል የሚፈጠረው ችግር የአለም ችግር እየሆነ መጥቷል፡፡ የሚከተሉት ችግሮች ማለትም ችጋር፣ የጤና እና የንጹህ ውሃ አቅርቦት ጉዳይ፣ ዘረኝነት ፣የጾታ እኩልነት፣ ወዘተ ወዘተ የአለም ችግሮች ናቸው፡፡ ለተጠቀሱት ችግሮች አለም በአንድ ላይ መፍትሔ ይፈልጋል ወይም እያንዳንዱ ሀገር የራሱን መፍትሔ ይፈልጋል፡፡ በርግጥ እያንዳንዱ ሀገር ያለው ችሎታ በእጅጉ የተለያየ ነው፡፡ ግራም ነፈሰ ቀኝ የሰው ልጅ የአይምሮ ሀይሉን በመጠቀም ዘለቄታዊ መፍትሔ ለማግኘት ተቆጥቦ አያውቅም፡፡

እስቲ ሁላችንም በተባበረችው አሜሪካ ያለውን የዘረኝነት በሽታ ( ችግር) እናስብ፡፡ የእኩልነት ትግል ተቋርጦ አያውቅም፡፡ አሁን ድረስ ጥቁር አሜሪካውያን ዘረኞች የሚያደርሱባቸውን በደል በመቃወም ትግል እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡ እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር በሚያዚያ ወር መጀመሪያ 2022 ላይ የተባበረችው አሜሪካ ሴኔት ጃክሰን ተብለው የሚጠሩ ሴት በተባበረችው አሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሰጥ አባል የሆኑ የመጀመሪያዋ ጥቁር አሜሪካዊ ሴት ለመሆን በቅተዋል፡፡ the US Senate confirmed Jackson as the first Black woman in the U.S. Supreme Court ሚስስ ጃክሰን በዚህ ታሪካዊ የተባበረችው አሜሪካ ሴኔት ውሳኔ ላይ የሚከተለውን ታሪካዊ ንግግራቸውን አሰምተው ነበር፡፡ እጠቅሳለሁ፡፡ << ይህን እውን እንዲሆን ያደረግነው ሁላችንም ነን፡፡›› ‹‹ ትኩረት ማድረግ ያለብን በአረፍተ ነገሩ ላይ መሆን አለበት፡፡ ›› ‹‹ ሁላችንም ›› የህግ ምሁሯ አክለው ማያ አንጄላን ጠቅሰው (She also quoted Maya Angelou )  የሚከተለውን ንግግር አሰምተው ነበር፡፡ ‹፣ ‹‹ ይህን ስጦታ ከቅድመ አያቶቼ እንደተሰጠ ስጦታ እቆጠረዋለሁ፡፡ ›› ‹‹ እኔ ህልም አለኝ›› እርሳቸውም ወደፊት ለሚመጣው ትውልድ አርአያ እንደሚሆኑ ተስፋ አድርገዋል፡፡ ከዚህ ባሻግር ይህ አንጸባራቂ የሰው ልጆች ታሪክ ነው በማለት ነበር ታዳሚውን ያስደመሙት፡፡ ይህ በመላው አለም አንቂ ደውል ሆኖ ይቀጥላል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

የሰው ልጅ የሚጋጥመውን ችግር ለመፍታት ሀይል አለው፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፣አዲስ ችግር ለመፍጠርም እንዲሁ ሀይል አለው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ለኑሮ እድገት በምናደርገው ትግል ምክንያት የሰው ልጅ ለአለም ሙቀት መጨመር ምክንያት ከሆነ አመታቶች ተቆጠሩ፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና በ21ኛው ክፍለ ዘመን በሁሉም የአለም ክፍል ውስጥ የሰው ልጅ የአካባቢ ብክለትን ( ችግርን) ለመቀነስ መፍትሔ ሰራሄ እየፈለገ ይገኛል፡፡ ለአካባቢ ተስማሚ የሆነ ሰራሄ መፍትሔ እየፈለገ ይገኛል፡፡ የሰው ልጅ ለማይኖርበትም ዘመን ቢሆን ለመጪው ትውልድ የሚጠቅም ስራዎችን እየከወነ ይገኛል፡፡ በተለይም በሰለጠነው አለም የሰው ልጅ በመጪዎቹ መቶ እና ሁለት መቶ አመቶች ሊቆይ የሚችል ወይም የሚጠቅም ተግባራቶችን እየከወነ ይገኛል፡፡ ለአብነት ያህል የተባበሩት አሜሪካ ለመጪዎቹ ክፈለዘመናት የሚጠቅም የነዳጅ ሀብት አከማችታ ትገኛለች፡፡ ሌሎች የበለጸጉ ሀገራት ለክፉ ቀን የሚሆን መድሃኒት፣ምግብና ሌሎች ለሰው ልጆች የሚጠቅሙ ቁሶች እንዳይበላሹ በማድረግ ያከማቻሉ፡፡ ይሄን ገቢራዊ የሚያደርጉት ደግሞ የአይምሮ፣አካላዊና መንፈሳዊ ሃይላቸውን በመጠቀም እንደሆነ ኢትዮጵያውያን ልብ ልንል ይገባል፡፡ 

ዘለቄታዊ የሚለው ቃል በብዙ የአለም ጉዳዮች  ጥቅም ላይ የዋለ ነው፡፡ ለአብነት ያህል የተባበሩት መንግስታት 17 የሚገናኙ ዘለቄታዊ ጥቅም የሚሰጡ  አለም አቀፍ ግቦችን አውጥቷል ወይም አዘጋጅቷል፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና የሰውን ልጅ ፍላጎት ለማሟላት ገና ብዙ ዘለቄታዊ አላማ ያላቸው ግቦች መነደፍ አለባቸው፡፡ እንዚህን ግቦች እውን ለማድረግ በርካታ አክተሮች ወይም ተዋናዮች ይገኛሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከአካባቢ፣እርሻ፣ቴክኖሎጂ፣ጤና፣ ትምህርት ወዘተ ወዘተ የተገናኙ ችግሮችን አስጠንቶ መፍትሔ እየሰጠ ይገኛል፡፡

ለአካባቢያዊ ችግሮች ዘለቄታዊ የመፍትሔ ሃሳቦች

ከላይ በአጭሩ ለማብራራት እንደሞከርኩት በአለም አቀፍ ደረጃ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት ዘለቄታዊ የመፍትሔ ሃሳቦች እጅጉን ጠቃሚ ናቸው፡፡ ስለሆነም ይህ አለም አቀፍ ጥበብ የአካባቢዊ ችግሮችን ለመፍታት ጥቅም ላይ መዋል አለበት ብዬ አስባለሁ፡፡ ልክ እንደ ወልቃይትና አካባቢው ችግሮች የወልቃይት ችግሮች የሚለውን አውድ መጠቀም እንችላለን፡፡ የወልቃይት ችግር ካለፉት 50 አመታት ጀምሮ የታየ ነው፡፡ ችግሩ ከሃምሳ አመታት በፊትም እንደነበር የታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ የወልቃይት ችግር ከባህል፣ ታሪክ እና ማህበራዊ አኳያ መፈተሸ ይገባዋል ብዬ አስባለሁ፡፡ ስለሆነም ለዚህ ችግር ዘለቄታዊ መፍትሔ መሻቱ አማራጭ የለውም፡፡ ከዚህ ሌላ ማለትም የውሸት መፍትሔ መፈለጉ የትም አያደርሰንም፡፡ ለአብነት ያህል አሳዛኝ ድራማ መስራት ማለትም የህዝብ አሰፋፈፈርን በመለወጥ ማለትም የህዝብ ኢንጂነሪንግ ገቢራዊ በማድረግ  ሌሎችን ከሌላ አካባቢ በማምጣት በሀይል በማስፈር ይህ መሬት የእናንተ ነው ማለት ፣ የራስን ድምጽ ብቻ መስማት፣ የራስን ጨካኝ ፍላጎት ብቻ ለማሟላት ብቻ በመስገብገብ  የሚደረግ ውሳኔ መፍትሔው ጊዜያዊ ነው፡፡ በአጭሩ ነባሩን፣ታሪካዊዉን፣ ባለመሬቱን የወልቃይት ህዝብ ለግማሽ ክፍለ ዘመን ያህል በረቀቀና አረመናዊ ሁኔታ ከርስቱ ካፈናቀሉ  በኋላ ህዝበ ውሳኔ ይካሄዳል መባሉ ለችግሩ ግማሽ መፍትሔን እንኳን የሚያስገኝ አይደለም፡፡ ይህ ግብታዊና በሴራ የታጀለ ውሳኔ ራስን ከማታለል ውጭ ሌላ ቁም ነገር የለውም፡፡ 

በአንድ የታሪክ አጋጣሚ አንድ ቡድን ጠንካራ ወይም ሀይለኛ እንደሆነ በሚሰማው ግዜ የራሱ ያልሆነን መሬት በወረራ ሊይዝ ይችለዋል፡፡ በሌላ ግዜ ደግሞ ሀይለኛ የነበረው መዳከሙ አይቀሬ ይሆናል፡፡ ሌሎች መሬታቸው በግፍ የተነጠቁ ቡድኖች ወይም ማህበረሰቦች መሬታቸውን እንደገና ሀይል በመጠቀም ሊያስመልሱ ይችላሉ፡፡ ይህ ማለት ግን የተከሰተውን ችግር ዘለቄታዊ በሆነ መንገድ መፍታት ይቻላል ማለት  አይደለም፡፡ የሚያዋጣው አንቺ ትብሽ፣አንተ ትብስ ማባባሉ ነው፡፡ የወልቃይት ምድር በህግ፣ታሪክ እና ባህል መሰረት ለመባለቤቱ ወልቃይቴ ተመልሶ ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ተከባብረው የሚኖሩበት ምድር እንዲሆን መፍትሔ መፈለጉ ያዋጠናል፡፡ ብረትና ጉልበት የትም አያደርሰንም፡፡ በአለም ላይ የሚከሰቱ ችግሮች በህሊና ሚዛን ካልተመዘኑ መፍትሔ አይገኝላቸውም፡፡ አልጠግብ ባይነት፣ ስግብግብነት ለችግሮች መፍሔሰራሂ አስገኝተውም አያውቁም፡፡ ለአብነት ያህል የአለም የሙቀትን መጨመር ለመቀነስ የሚያስብ የሀገር መንግስት ወይም ድርጅት የተቃጠለ አየር ማምረት የለበትም፡፡ የተቃጠለ አየር በብዛት( ያለገደብ) እያመረቱ (continue to produce more CO2,) የአለምን የሙቀት መጠን ለመቀነስ እገዛ እያደረኩ ነው ማለት ማታለል ነው፡፡ ስለሆነም ይህን በገሃድ የሚታይ የአለም ሙቀት መጠን ችግር ለመፍታት አዳጋች ነው፡፡ ለዚህም ነው በአለም የሚገኙ ሀገራት በተለያዩ ግዜያት የአለምን የሙቀት መጠንን ለመቀነስ ስምምነት የሚፈራረሙት፡፡

ማናቸውም የአለም ሀያላትና ተቋማት በአንድ አካባቢ የሚያደርጉት ጥናት በገለልተኛ እሳቤ መሆን አለበት፡፡ የአንዱን ማህበረሰብ ድምጽ ሰምቶ ሌላውን ማግለል ለጥልቅ ስህተት ይዳርጋል፡፡ በቅርቡ ሁለት አለም አቀፍ ሰብአዊ መብት አስከባሪ ድርጅቶች በወልቃያት አካባቢ ተፈጸመ ያሉትን የሰብአዊ መብት ጥሰት ሪፖርት ከአንድ ወገን ብቻ መሆኑ አግባብ አልነበረም፡፡ ለአብነት ያህል የጎንደር ዩንቨርስቲ ህክምና ፋኩሊቲ በመስኩ ባለሙያዎች በኩል ባደረገው ምርመራ ወልቃይት ምድር ውስጥ አገኘሁ ስለላው የጅምላ መቃብር ጉዳይ ያለቱ የለም፡፡ ወይም ሁለቱም አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት አስከባሪ ድርጅቶች በምን ጉዳይ ከዩንቨርስቲው ጋር ተባብረው ስለመስራታቸው የተናገሩት ጉዳይ አልነበረም፡፡ ምናልባት እኔ መስማት ካልቻልኩ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፤

በዛሬው ጽሁፌ ላይ ለመዳሰስ የምሞክርው መሰረታዊ ችግሩን ነው፡፡ (የወልቃይትና አካባቢውን ችግር ማለቴ ነው፡፡) ከዚህ አኳያ ሁለቱም አለም አቀፍ የመብት አስከባሪ ድርጅቶች በሪፖርታቸው ላይ የወልቃይ ጸገዴ መሬት በምእራብ ትግራይ የጂኦግራፊ ክልል እንደሚገኝ አስፍረዋል፡፡ in the report, they claim that this region belongs to Western Tigray ይህ ግን ከባድ ስህተት ይመስለኛል፡፡ ‹‹ የምእራብ ትግራይ›› የሚለው ቃል በወያኔ አገዛዝ የተዋወቀ የአንድ ወገን ቃል ነው፡፡ ይህም ብቻ አይደለም የወልቃይት አካባቢ በምእራብ ትግራይ እንደሚገኝ በህገመንግስቱ ተጠቅሷል፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና ህገመንግስቱ በሁሉም ሰዎች ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው በብዙ ነገሮች ታይቷል፡፡ ይህ በግድ የተጫነ ስለመሆኑ የሚያከራክር አይመስለኝም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ይህን ጽሁፍ በማዘጋጅበት ግዜ ወልቃይት በምእራብ ትግራይ የሚገኝ ግዛት ስለመሆኑ በብዙ መንገድ ለማረጋገጥ ሞክሬ ለማወቅ አልቻልኩም፡፡ በተጠቀሰው ምክንያት አለም አቀፍ የሆኑት ሁለቱ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች በሪፖርታቸው ላይ ምእራብ ትግራይ የተፈጸመ የሰብአዊ መብት ጥሰት ብለው በመጥቀሳቸው በርካታ ሰዎችን አሳዝነዋል፡፡ በተለይም ባለፉት አርባ እና ከዚያ በላይ አመታት ውሰጥ በወያኔ አገዛዝ ግፍ የተፈጸመባቸው የወልቃይት ተወላጆችን ልብን ሰብሯል፡፡ ልባቸው ብቻ አልነበረም የተሰበረው፡፡ የወጣውን ሪፖርትም እንደማይቀበሉት በብዙ መልኩ ገልጸዋል፡፡ ይህም ማለት በሁለቱ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ላይ ህዝቡ ጥሩ ምልከታ እንደሌለው ከማሳየቱ ባሻግር  እነኚሁ አለም አቀፍ ድርጅቶች እውነታውን እያወቁ ሆን ብለው ችላ ብለውታል ባይም ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ችግሮችን የምንይዝበት መንገድ አግባብ ካልሆነ  መፍትሔ ለመፈለግ ያስቸግረናል፡፡ በዚህ መንገድ ከሄድን የችግሩ አካል መሆናችን አይቀሬ ነው፡፡ ለማናቸውም የሚያዋጣው እንደ ሰው ማሰብ ነው፡፡ ለአብነት ያህል የሃይማኖት ነጻነትን ለማስጠበቅ ነው በማለት የአክራሪነት ባህሪ ያላቸው ፣ በውጭ ሀገር፣ በባእድ ሀገር አስተምህሮ አይምሯቸው የተመረዘ የሃሰት፣ሼኪዎች፣ካህናት፣የሀሰት የባህል አባቶች ወዘተ ወዘተ ለሰላም የሚበጅ መፍትሔ ለማፍለቅ አይቻላቸውም፡፡ እነርሱ የግጭት ጠማቂዎች፣የክፋት ሃዋርያዎች ናቸው፡፡

ይህ ችግር እንዴትና መቼ ነበር የተፈጠረው ?

በዚህ ችግር ላይ አሁን ድረስ የተዘፈቀንበትን ምክንያት ሁላችንም ማወቅ ያለብን ይመስለኛል፡፡ ዛሬም ከዚህ የችግር አረንቋ መውጣት አልተቻለንም፡፡ በነገራችን ላይ ይሄ ችግር ሆን ተብሎ በማርክሲስት ሌኒንስት ወያኔ ፓርቲ አገዛዝ የዛሬ አርባ እና ሃምሳ አመታት በፊት የተፈጠረ ነው፡፡ ይህ ችግር በወያኔ የተፈጠረ የሞት ድግስ ነው፡፡ ወያኔዎች የዳርዊንን ፍልስፍና ገቢራዊ በማድረግ ‹‹ ሃይለኛው ያስገብራል፣ ወይም ያሸነፈው ይኖራል›› የሚለውን ማለቴ ነው፡፡ (principle of “the survival of the fittest.) የወልቃይት ምድርን በሃይል በጉልበታቸው ተቆጣጥረውት ነበር፡፡ መቆጣጠጠር ብቻ አልነበረም የሰሊጥና እርሻ ምርቶችን ወደ ውጭሀገር፣ወደ ባእድ ሀገር ያለከልካይ በመላክ ለብቻቸቸው በብዙ መቶ ሚሊዮን የሚቆጠር የአሜሪካን ዶላር ዝቀውበት ነበር ፡፡ ነበር ልበል ዛሬ ለግዜውም ቢሆን  የሀፈረት ሸማ ተከናንበው፣ በጦር ሜዳ ላይ የሽንፈት  ጽዋ ተጎንጭተው የወልቃይትን ምድር ለቀው ወደ ትግራይ ክልል ሸሽተው ለመሄድ ተገደዋል፡፡ በነገራችን ላይ የወያኔ ቡድን የወልቃይት መሬትን ከመርገጡ በፊትም ሆነ የደርግ ወታደራዊ መንግስት አካባቢውን ሳይቆጣጠር በፊት የኢዲዩ፣ኢህአፓ ( የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ) ታጋዮች በአካባቢው መሽገው ደርግን ይፋለሙ እንነበር የውቤ በረሃው አቶ ያሬድ ጥበቡ( ጌታቸው ጀቤሳ) ከጻፉት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ መጽፍ ላይ እንማራለን፡፡

የወያኔ ቡድን የወልቃይት ምድርን የተቆጣጠረው የኢህአፓና ኢዲዩ ሰራዊቶችን በተለያዩ ግዜያት ጦርነት ገጥሞ በማሸነፉ ነበር፡፡ ከዚህ ባሻግር እነኚሁ የፖለቲካ ሀይሎች ( ኢዲዩና ኢህአፓ) አልፎ አልፎ ርስበርሳቸው እና ከኢትዮጵያ ወታደሮች ጋር ውጊያ ይገጥሙ እንደነበር የሚሳዩ የጥናት ወረቀቶችን እንዳነበብኩ አስታውሳለሁ፡፡ በነገራችን ላይ የሁለቱም ፓርቲዎች አባል የነበሩ አንጋፋ የፖለቲካ ሰዎች ( እንደነ አቶ እያሱ አለማየሁ( ሃማ ቱማ)፣አቶ ያሬድ ጥበቡ፣ ራስ መንገሻ ስዩም ዛሬም በህይወት የሚገኙ ስለሆነ እውነታውን በተመለከተ ጥልቀት ያለው ምስክርነታቸውን ለዚህ ትውልድ በሚያመቻቸው መንገድ እንዲሰጡ በታላቅ ትህትና አስታውሳለሁ፡፡

ማስታወሻ፡- የአካባቢው ወራሾች እነማን ናቸው ? ተብሎ ቢጠየቅ የሚያመጣውን ችግር ለመረዳት ያስቸግረናል፡፡ የየትኛው ማህበረሰብ ክፍል ነበር የሚኖረው ? በዛን ግዜ ምን አይነት አስተዳደር ነበር ? የወልቃይት መሰረታዊ ችግር የሚመነጨው የሀገሪቱን ፖለቲካ በበላይነት ለመያዝ በሚደረገው ትግል ምክንያት ነው፡፡ የሀገሪቱን ማእከላዊ መንግስት የሚቆጣጠረው መንግስት ዲሞክራት ከሆነ የወልቃይት ችግር እዳው ገብስ ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡

የታሪክ መረጃዎች ፍንትው አድርገው እንደሚያሳዩት የወያኔ ቡድን ከኤርትራው ሻቢያ ጋር በማበር ( ያንዬ አንድነትና ትብብር ነበራቸው)፣ በምእራባውያን ሀይሎች እና በአረቦች በተለይም በታሪካዊ ጠላታችን ግብጽ መጠነ ሰፊ እርዳታ በማግኘት፣ ሱዳን የስንቅና ትጥቅ ማደራጃ   በመስጠቷ በቀድሞዋ ሶቪዬት ሕብረት ይረዳ የነበረውንና የኢትዮጵያ ህዝብ ፊት የነሳውን  ማእከላዊ መንግስት አሽቀንጥረው ከስልጣኑ ጥለውታል፡፡ ይህ አጋጣሚ ወያኔ በኢትዮጵያ ላይ የፈለገውን ነገር እንዲፈጽም መልካም እድል ፈጥሮለታል፡፡ በተለይም በስልጣን ዘመናቸው በወልቃይት ምድር ይፈጽሙት የነበረውን ግፍና በደል በተመለከተ ይደብቁ ነበር፡፡ በአጭሩ መንግስታዊ ስልጣንና መዋቅራቸውን ከለላ በማድረግ ሚስጥራዊ ወንጀል ይፈጽሙ ነበር፡፡ በነገራችን ላይ ወያኔ ለስልጣን ከመብቃቱ በፊት ከዚህ አካባቢ ( ወልቃይት ማለቴ ነው) ልዩ ፍቅር ነበረው፡፡ በትግሉ ዘመንም ለአመታት የተቆጣጠረው ስፍራ መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡

 ህይወታቸውን ሙሉ በአካባቢው የኖሩ ሰዎች ዛሬም አሉ፡፡ አስፈላጊ ከሆነ የትውልድ ሀረጋቸውን መጠየቅ ይቻላል፡፡ እነኚህ ለዘመናት በወልቃይት አካባቢ የኖሩና የተወለዱ ሰዎች ጥንታዊ አያቶቻቸውና አባቶቻቸው በየትኛው የኢትዮጵያ ግዛት ይኖሩ እንደነበር መግለጽ ወይም መናገር ይችላሉ፡፡ በነገራችን ላይ ያንዬ አማጺ ቡድን የነበሩት ሀይሎች ሁሉ ይደበቁ የነበሩት፣ ምግብ ያገኙ የነበረው፣ ውሃ የሚጠጡት፣ መጠለያ ያገኙ የነበረው ከዚሁ ከወልቃይት ህዝብ ነበር፡፡ ታሪክ አይሸፈጥም፡፡ በዚህ ላይ ምንም የሚያጠራጥር ወይም ግራ የሚያጋባ ነገር የለም፡፡ እዚች ላይ ማናቸውም ኢትዮጵያዊ በወልቃይት ምድር መኖር እንደሚችል ማስታወሱ ተገቢ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የመሬት ችግር የለባትም፡፡ የኢትዮጵያ መሰረታዊ ችግር የአስተዳደር ችግር ነው ተብሎ ቢጻፍ ስህተት አይመስለኝም፡፡ ( ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል ቢሆንም)  አሁን በስራ ላይ ያለው ህገመንግስት ሳይቀር አንቀጽ  ‹‹15 ›› ላይ ማናቸውም ኢትዮጵያዊ  በመላው ሀገሪቱ የመኖር፣ የመስራት እና ሀብት የማፍራት መብት አለው ይላል፡፡ ›› ሆኖም ግን ይሁንና ከአስተዳደር አኳያ የወልቃይትና አካባቢው በትግራይ ክልል ውስጥ እንዲካተት በወያኔ ይመራ የነበረው የኢትዮጵያ አገዛዝ ከወሰነ በኋላ ከባድ ችግር ተፈጥሯል፡፡ ወያኔ ከባድ ችግር ፈጥሯል፡፡ ይህ የችግሩ አንድ ክፍል ነው፡፡ ይህ በንጹህ ልቦና የተወሰነ አልነበረም፡፡ ይህ ግዜውን ጠብቆ እንደሚፈነዳ ፈንጂ አይነት ነው፡፡ ይህን እኩይ ድርጊት እንደው በተራ መንፈስና፣ በማንአህሎተኝነት  ወይም በሃይል መፍታት አይቻልም፡፡ የወልቃይት ጉዳይ በጥበብና እውቀት ነው የሚፈታው፡፡ የወልቃይት ጉዳይ ኢትዮጵያዊ የታሪክ፣የፖለቲካ፣የባህል፣ማህበራዊ፣መልክአምድራዊ እና ፖለቲካዊ አዋቂዎችን ጥናትና ሽምግልና ይጠይቃል፡፡ ማዶ ለማዶ እምቡር እምቡር ማለቱ አያዋጣንም፡፡ በተለይም ከትግራይ ወንድሞቻችን አካባቢ የሚመታው የጦር አዶከበሬ ለማንም አይጠቅምም፡፡ ከገባን ገና ድሮ ጠዋት ጋሼ ጥላሁን ገሠሠ ‹‹ የማን ቤት ጠፍቶ የማን ሊለማ…….) በዛ ጥኡም ድምጹ ነግሮናል፡፡ ለማናቸውም እንደ አንድ ተራ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የወልቃይት ችግር የሚፈታው በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስራ ይፈታል ብዬ አስባለሁ፡፡ ምርጫውን ግን ለኢትዮጵያውያን በተለይም በጥንቱ አጠራር ለቤጌምድር ወልቃይት ተወላጆችና ለትግራይ ወንድሞቻችን ትቼዋለሁ፡፡ እባካችሁን ልብ ግዙ ከሩቅም ሆነ ከቅርብ ሆነው የኢትዮጵያን ሞት ለሚመኙ በተግባርም ለሚደግፉ ታሪካዊ ጠላቶቻችን  ድብቅ ሴራ ውስጥ ተጠልፋችሁ አትውደቁ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የወልቃይት ተወላጆች የወልቃይት ችግር በዲሞክራሲያዊ መንገድ እንዲፈታ ለዘመናት ሲጠይቁ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና የተሰጣቸው መልስ የዝሆን ጆሮ ነበር፡፡( በተለይም በወያኔ ዘመን እንደነ አቶ መብራቱን የመሰሉ ስመጥር የወልቃይት ተወላጆች የመብት ታጋዮች የወልቃይት ችግር በዲሞክራሲያዊ አካሄድ በመጠየቃቸው ብቻ ዘብጥያ ተወርውረው ነበር፡፡ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ወልቃይቴዎች በወያኔ ካራ ተገድለዋል፡፡ ህይወታቸው የተረፈውም እስከ አውስትራሊያ ድረስ እንደ ጨው ዘር ተበትነዋል፡፡ ምን ያህል የሀገር አድባሮች፣ወጣቶች በወያኔ ገዳይ ቡድን አባላት እንደተገደሉ ወደፊት ታሪክ ያወጠዋል፡፡) ይህን ሁሉ ግፍ ሲፈጽሙ ምክንያታቸው ብዙ ነው፡፡ በነገራችን ላይ የወልቃይት ስልታዊ የመልክአምድር አቀማመጥ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ በተለይም ለወልቃይትና አካባቢው ደግሞ የበለጠ ጠቃሚ ነው፡፡

ለምንድን ነው የወልቃይት ችግር እጅግ የተወሳሰበ የሆነው ?

  1. ፖለቲካ ስልጣን (ሀይል)፡-  በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች ካቀረቡት የጥናት ወረቀት ላይ ለመረዳት እንዳቻልኩት ወልቃይትን የተቆጣጠረ ሁሉ ኢትዮጵያን መቆጣጠር ይችላል፡፡ ይህ አረፍተ ነገር የተጋነነ ሊመስል ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና  ይህ እውነት ነው፡፡ But it is a fact. በነገራችን ላይ የወያኔ አገዛዝና የቀድሞው ወዳጁ ሻቢያ የወልቃይት ዛሬ ያሉበትን ሁኔታ ለማሳካት የቻሉት የወልቃይት ምድርን በመቆጣጠራቸው ነበር፡፡( ሻቢያ አስመራ ላይ መንግስት ለማቆም የቻለው፣ ወያኔም አዲስ አበባ ምኒሊክ ቤተመንግስት ዘው ብሎ ለመግባት የበቃው የወልቃይት ምድርን በመጀመሪያ ለመቆጣጠር በመቻሉ ነበር፡፡ ግብጽን የመሰሉ የኢትዮጵያ ታካዊ ጠላቶች ለወያኔ ድጋፍ ያደርጉ የነበረው በዚሁ በወልቃይት ምድር በኩል እንደነበር ለማወቅ የአሁኑ ትውልድ ታሪክን መመርመር አለበት፡፡ የወልቃይት ምድርን ለአመታት ባይቆጣጠሩ ኖሮ ያሳቡትን ለማሳካት አይቻላቸውም ነበር፡፡) በነገራችን ላይ የጦር ሰዎች በማስታወሻ ደብተራቸው ላይ እንደ አስቀመጡት ከሆነ ይህ የኢትዮጵያ ክፍል የአማጺ ሀይሎች ታጣቂዎቻቸውን በጦር ስልት ለማስልጠን ያመቻቸዋል፡፡ ራሳቸውን ለመደበቅም ያመቻቸዋል፡፡ ለሰሜን ተራራ ( ራስ ዳሽን ተራራ) እና ለተከዜ ወንዝ ባለው ቅርበት ምክንያት የወያኔ ጦር ለብዙ አመታት ጦሩን በማንቀሳቀስ ወታደራዊ የደርግ አገዛዝን ለመዋጋት አመቺ ሁኔታ ፈጥሮላቸዋል፡፡ ይህ የወልቃይት ምድር የኢትዮጵያን ማእከላዊ መንግስትን በጦር ሀይል ለመገዳደደር ተሰልፈው ለነበሩ ሀይሎች ተዋጊ ሀይላቸውን እንደ ልብ ለማንቀሳቀስ ምቹ ምድር ከመሆኑ ባሻግር ለአስርተ አመታት ያህል ለመዋጋት አስችሏቸው ነበር፡፡

በርካታ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ ጸሃፊዎች በጥናት ወረቀታቸው ላይ እንዳሰፈሩት ከሆነ የወያኔ ሀይል ወልቃይትን ሳይቆጣጠር በተከዜ በሌላ አቅጣጫ ተወስኖ ቢቀር ኖሮ በድርጅትና መሳሪያ ሃይል በከፍተኛ ደረጃ ላይጠናከር ይችል ነበር፡፡ የመሳሪያ፣የሎጂስቲክና የምግብ አቅርቦት መስመርም ላያገኝ ይችል ነበር፡፡ ከሱዳን ጋር ቀጥተኛ የግንኙነት መስመር ሳይኖረው፣ኢትዮጵያን በሁመራ መስመር የሚዋሰነውን የኤርትራን ድንበር በቅጡ ሳይቆጣጠር በአካባቢውን የሃይል አሰላለፍ በበላይነት ለመቆጣጠር አይቻለውም፡፡ የወልቃይት አካባቢ ወያኔ ተቀናቃኝ ወይም ጠላት ብሎ በሰየማቸው ሃይሎች ቁጥጥር ስር ወደቀ ማለት የወያኔ ህልውና አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱ አይቀሬ ነው፡፡ ከትግራይ ህዝብ ከባድ ተቃውሞ ሊያጋጥመው ይቻለዋል፡፡ ወያኔ የጀርባ አጥንቱ እንደተሰበረ ነብርም ሊቆጠር ይቻለዋል፡፡ ወያኔ ትርጉም ያለው እንቅስቃሴ ማድረግም ይሳነዋል፡፡ በትግራይ የሚቀረው የወያኔ ጭንቅላት ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም ሁነኛ የፖለቲካ መፍትሔው በተባበረች እና አንደነቷ በተጠበቀ ኢትዮጵያ የወልቃይት ምድር አስተዳደደር በቀድሞው ግዛቱ ቤጌምድር ወልቃይት ሆኖ ማናቸውም ኢትዮጵያውያን የሚኖሩበት አካባቢ መሆኑ መፍትሔ ያስገኛል የሚለው የግል አስተያየቴ ነው፡፡ እንደው ዝም ብሎ ጦር ሰብቆ አካባቢው በምእራብ ትግራይ ጂኦግራፊ ክልል መካተት አለበት ብሎ መነሳት መፍትሔ አያመጣም፡፡

2.የምጣኔ ሀብት ምክንያት፡-  ወልቃይት እና አካባቢው እምቅ የእርሻ ሀብት እንዳለው በብዙ እርሻ ባለሙያዎች የጥናት ወረቀት ላይ ተጠቅሷል፡፡ ወልቃይት ለም መሬት ያለው ሲሆን በሜካናይዝድ እርሻ እጣን፣ጥጥ፣ኑግ ማምረትም ይቻላል፡፡ ለአብነት ያህል በሀይለስላሴ ዘመነ መንግስት በወልቃይት፣ሁመራ አካባቢ በትራክተር የሚያርሱ ባለሀብቶች እንደነበሩ ማስታወሱ ተገቢ ሳይሆን አይቀርም፡፡ አብዛኞቹ የሚመረቱት የእርሻ ሰብሎችም ወደ ውጭ ሀገር ለሽያጭ የሚቀርቡ ናቸው፡፡( mostly export goods )  በነገራችን ላይ የወልቃይት አካባቢን የተቆጣጠረ አካል ወልቃይትን ከሚያዋስኑት ሌሎች አካባቢዎች ከምጣኔ ሀብት አኳያ የተሻለ ጥቅም እንደሚያገኝ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

  1. የጸጥታና መረጋገጥ ምክንያት እንደ ብዙ የፖለቲካ ሰዎችና የሚሊተሪ አዋቂዎች ጥናት ውጤት ከሆነ የወልቃይትና አካባቢውን ጸጥታ ጉዳይ የተቆጣጠረ ( በአካባቢው ወታደራዊ የበላይነት ያለው) የሀገሪቱን ጸጥታና መረጋጋት ለመቆጣጠር ይቻለዋል፡፡ በሱዳንና ኤርትራ አኳያ ኢትዮጵያን የሚያዋስነውን ድንበር ይቆጣጠራል፡፡ ይህም ማለት ሶስት ነጥቦችን ወይም ሶስት የድንበር አካባቢዎችን ይቆጣጠራል፡፡ ስለሆነም የወያኔ ሀይል ወልቃይትን ከተቆጣጠረ ወደ ሱዳንና ፖርት ሱዳን እንደ ልቡ መመላለስ ይቻለዋል፡፡ ይህም ብቻ አይደለም ይህ አደገኛ ቡድን የኢትዮጵያን አንድነት ለማናገት ለዘመናት እንቅልፍ  አጥታ  ሴራ ስትጎነጎን ከኖረችው ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ከሆነችው ግብጽ ጋር ያለው ግንኙነት እየተጠናከረ ይመጣል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በአካባቢው የኤርትራ ተጽእኖን መቆጣጠር ይቻላቸዋል፡፡ ለዚህም ነው ወልቃይትን በመዳፋቸው ስር ለማስገባት ሲሉ  ላለፉት ሁለት አመታት ከ30 ግዜያት በላይ ጦር ሰብቀው ጦርነት የከፈቱት፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና የከፈቱት ጦርነት ውጤታማ አልነበረም፡፡

ለወልቃይት ችግር ዘለቄታዊ መፍትሔው ምን ይሆን  ?

ለአካባቢው መሰረታዊ ችግር ዘለቄታዊ መፍትሔ መምጣት አለበት ብዬ አስባለሁ፡፡ ይህ ዘለቄታዊ መፍትሔም እውነተኛ እና የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላም እና እድገት እንዲኖር ከማሰብ የመነጨ ቀና አመለካከት ነው፡፡ ለማናቸውም ሶስት የመፍትሔ ሃሳቦችን እንደሚከተለው አቀርባለሁኝ፡፡

ዘለቄታዊ መፍትሔ አንድ

በእኔ የግል አስተያየት መሰረቱን ጎሳ ላይ ያደረገውን የክልልና አከባቢ መስተዳድርን ከህገመንግስቱ መፋቅ አለበት ብዬ አስባለሁ፡፡ በሌላ አነጋገር የክልሎችና አካባቢ መስተዳድር መሰረቱ የጎሳ ፍልስፍና መሆኑ ቀርቶ በመልእከአምድራዊ ወይም በሌላ በኢትዮጵያ ህዝብ ይሁንታ ያገኘ የመስተዳድር አይነት በኢትዮጵያ ምድር እውን መሆን አለበት፡፡ አፋጀሸኝ ከሆነው የጎሳ ፖለቲካ የኢትዮጵያ ህዝብ መገላገል አለበት፡፡ ይህ የአንድ ተራ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ብቻ አስተያየት እንዳልሆነ የዛሬዬቱ ኢትዮጵያ ጌቶች በቅጡ እንድትረዱት ሳስታውስ በአክብሮት ይሆናል፡፡ ስመ ጥሩ የኢትዮጵያ ልጆች ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም፣ፕሮፌሰር ጌታቸው ሀይሌ፣ የእውቀት ጎተራው ጋሼ ሙሉጌታ ሉሌ፣ አንጋፋው ጋዜጠኛ ጋሼ ክበበው እና  ከፍያለው፣ ( ነብሳቸውን ከደጋጉ አባቶቻችን ነብስ ጎን ያኑርልን)፣ አንጋፋ ጋዜጠኖች ጋሼ ክፍሌ ሙላት፣ጋሼ ጎሹ ሞገስ፣ጋሼ ታዬ፣ጋሼ አረጋ፣ፕሮፌሰር ጳውሎስ ሚልኪያስ፣ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ፣ዶክተር ታዬ ወልደሰማያት፣ፕሮፌሰር ጌታቸው መታፈሪያ ወዘተ ወዘተ የጎሳ ፖለቲካ በሌላ ተራማጅ የፖለቲካ አይነት እንዲተካ አይናቸው ደም እስኪመስል፣እጃቸው እስኪዝል ምክረ ሃሳባቸውን በብዙ መንገድ አቅርበው ነበር፡፡

The ultimate best solution is to eradicate ethnic-based regional and local administration from the constitution. 

በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ በማናቸውም የሀገሪቱ ክፍል ተዘዋውሮ ሰርቶ የመብላት ነጻነቱ መከበር አለበት፡፡ ( ወልቃይትንም ይጨምራል፡፡) ለዚህ ስኬት ደግሞ  የኢትዮጵያን ህገመንግስት በሰለጠነ መንገድ ማሻሻል ለዚህ ከባድ ችግር ዘለቄታዊ መፍትሔ ያስገኛል ብዬ አስባለሁ፡፡ ይህ እጅግ ስኬት ያለው ዘለቄታዊ መፍትሔ ያስገኝልናል፡፡ ለወልቃይት ችግር ብቻ አይደለም መፍትሔ የምናስገኘው፡፡ በብዙ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለሚከሰቱ ደም አፋሳሽ ግጭቶች ሁሉ ሁነኛ የሰላም መፍትሔ ይመጣል፡፡ ሁሉም ወይም አብዛኛው የአፍሪካ ሀገራት ተራማጅ ህግ እያነበሩ የሚገኙበት ግዜ ላይ እንገኛለን፡፡ ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ( ከኢትዮጵያ በቀር) የሁሉም ሰይጣናዊ ስር ከሆነው ጎሳ ፖለቲካ እየተገላገሉ ነው፡፡ ለራሳችን የጎሳ ማንነት በመጀመሪያ ስንታገል እንደ ማር ይታፍጠናል፡፡ መጨረሻው ግን መራር እና ሞት ነው፡፡ ለአብነት ያህል በጎሳ ፖለቲካ አቅላቸውን የሳቱ ሩዋንዳውያን በጎሳ ልነት ብቻ እርስበርስ ተላልቀዋል፡፡ በኢትዮጵያም ቢሆን ባለፉት ሰላሳ አመታት በጎሳ ማንነታቸው ብቻ በአክራሪ ብሔርተኞች ጭፍን ጥላቻ የተገደሉትን ቤት ይቁጠራቸው፡፡ ስለሆነም መሰረቱን ጎሳ ላይ ያደረገው የክልልና አካባቢ መስተዳድር በሌላ በህዝብ ይሁንታ ተቀባይነት ባገኘ የመስተዳድር አይነት መተካት አለበት፡፡ ይህ ማለት የጎሳዎች ባህል፣ቋንቋ እና መብት አይከበርም ማለት አይደለም፡፡ ሁሉም የጎሳ ማንነት መከበር አለበት፡፡ ማናቸውም ጎሳዎች ተከባብረው፣ በአንድነትና በፍቅር ህብረ ዝማሬ መኖር የቅንጦት ምርጫ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው፡፡

ዘለቄታዊ መፍትሔ ሁለት 

መጀመሪያው የመፍትሔ ሃሳብ ተቀባይነት ከሌለው ወይም ህዝቡ በጎሳ ፖለቲካ ላይ ከተጣበቀ( የጎሳ ፖለቲካ ያዋጣኛል የሚል ከሆነ) ባለፉት አመታት የወልቃይትን ቸግር ለመፍታት የተኬደበት መንገድ በስህተት የታጀለ ነበር፡፡ በመጀመሪያ የወያኔ ቡድን አካባቢውን በሃይል በጉልበት ተጠቅሞ ከመቆጣጠሩ ባሻግር ነባሩን የአካባቢውን ተወላጆች  ስርአታዊ እና በተቀነባበረ ዘዴ አካባቢውን እንዲለቁ ተገደው  ነበር ፡፡ይህ ህዝብን የመቀየር ወንጀል የተፈጸመው ደግሞ ለብዙ አስርተ አመታት ነበር፡፡ demographic engineering was done systematically for more than two decades  ስለሆነም እውነተኛ እና ዘለቄታዊ ሰላም ለማስገኘት ቅን ፍላጎት ካለን ይህን በወልቃይት ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን ወንጀል መመርመር ያስፈልገናል፡፡ ባለፉት 40 አመታት በወልቃይት ህዝብ ላይ ወያኔ የፈጸመው ግፍ ወደፊት ታሪክ የሚጽፈው በመሆኑ አሁን የምለው የለኝም፡፡ ምናልባትም ጥልቀት ያለው የታሪክ መረጃ ለማወቅ ለሚፈልጉ አንባቢያን አቶ አቻምየለህ ታምሩ የተባሉ እውቅ ምሁር የሚከተለውን ዌብሳይት እንዲጎበኙ እጋብዛለሁ፡፡

(https://ecadforum.com/2016/08/12/ethiopia-a-quest-for-identity-and-geographic-restoration-of-wolkait-tegede/)

ማስታወሻ፡- ያለፈውን ታሪክ የማይቀበሉ ሰዎች ከአንድ ወይም ከብዙ አቅጣጫዎች ሊገጥሙን እንደሚችሉ ማስታወሱ ተገቢ ነው፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና ታሪክን በጥልቀት ባነበብን ግዜ ወደ እውነቱ እንጠጋለን፡፡ ዘላቂ ሰላምም ለማስፈን ይቻለናል፡፡

ዘለቄታዊ መፍትሔ ሶስት 

ለአብነት ያህል እስቲ የወያኔን ሀይል ለአንድ አፍታ ከጥያቄ ውስጥ እናውጣው፡፡ ይህ አደገኛ ቡድን በራሱ ግዜ ወይም በሃይል ፣ ወይም በትግራይ ህዝብ ትግል ( ህዝቡ ወደ ህሊናው ከተመለሰ ማለቴ ነው) ከኢትዮጵያ የፖለቲካ አውድ ገለል ሊል ይችላል ብለን እንገምት፡፡ ( በርግጥም ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ ከማእከላዊ የመንግስት ስልጣኑ ገሸሽ ብሎ ነበር፡፡ ወደፊትም ተመልሶ በማእከላዊ መንግስት ውስጥ የሚመጣ አይደለም፡፡) ይህ እውን ከሆነ በኢትዮጵያ የስልጣን ምንጭ ህዝብ ይሆናል፡፡ በመጨረሻም ሁሉም  የኢትዮጵያ ህዝብ በፈለገበት የሀገሪቱ ክፍል በነጻነት ተዘዋውሮ የመኖር እና የመስራት መብቱ ምሉሄበኩልሄ በሆነ ሁኔታ ይከበርለታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ወንድማችን  የትግራይ ህዝብም ቢሆን ወልቃይትን ጨምሮ በመላው ሀገሪቱ ሰርቶ የመብላት እና የመኖር መብቱ ይከበርለታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ የትግራይ ህዝብ እንደ ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቹና እህቶቹ ሁሉ በመላው ሀገሪቱ በነጻነት የመኖር፣የመስራት መብቱ ደግሞ የሚከበረው ታሪካዊ ጠላታችን የወያኔ ቡድንን በመሸከም እና ለስልጣን በማብቃት አይደለም፡፡ ከዚህ ባሻግር ታሪካዊ ጠላታችን ግብጽና ምእራባውያን የያዙትን ድብቅ አጀንዳ በማስፈጸም አይደለም፡፡ ሁላችንም እንደምናውቀው የትግራይ ወጣቶች የተደበቀውን የግብጽን አጀንዳ ለማስፈጸም በጦርነት ውስጥ ተማግደዋል፡፡ የትግራይ ወጣቶች በጦርነት ላይ የወደቁት አብዛኛውን የትግራይ ህዝብ ለመጥቀም አልነበረም፡፡ አነርሱ የኢትዮጵያን አንድነት ለማናጋት የተሰለፉ የግብጽ የህልም ሀይሎች ናቸው፡፡ እርግጥ ነው ይገባኛል ለትግራይ ወጣቶች የግብጽ አጀንዳ አስፈጻሚዎች ስለመሆናቸው በቀጥታ አይነገራቸውም፡፡ ጠዋት ማታ በወያኔ ካድሬዎች የሚነገራቸው ነገር ቢኖር እናንተ የምትዋጉት ለትግራይ ህዝብ ነጻነት ነው በሚል ነው፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና ይህ ነጭ ውሸት ነው፡፡ (But that is a pure lie) ለዚህ ደግሞ ማረጋገጫው በመሬት ላይ የሚታየው አጠቃላይ የትግራይ ህዝብ ህይወትና ኑሮ ማሳያ ነው፡፡ ላለፉት 47 አመታት በተካሄደው የትግል ዘመን ጥቂት የወያኔ የፖለቲካ ፊትአውራሪዎችና አሽኮሌሌዎቻቸው ሰማየ ሰማያት ( በሀብት ማማ ላይ) ደረሱ እንጂ እንደ ሌላው የኢትዮጵያ ክፍል እንደሚኖረው ( እንደ ኑሮ ከተቆጠረ ማለቴ ነው) ኢትዮጵያዊ ሁሉ አላለፈለትም፡፡ ኢኮኖሚው በአፍጢሙ ተደፍቷል፡፡ የኑሮ ደረጃው እየባሰ ነው የመጣው እንጂ አልተሻሻለም፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና የትግራይ ህዝብ እጅና እግር በወያኔ ሰንሰለት የታሰረ ነው፡፡ ስለሆነም የትግራይ ህዝብ ራሱን ከወያኔ የግፍ ሰንሰለት ነጻ ማውጣት አለበት ብዬ አስባለሁ፡፡ ይህ የነጻነት ትግል ለአካባቢውና ለኢትዮጵያ ሰላም የሚበጅ ነው፡፡

በእርግጥ ወያኔ ለብዙ አመታት ሊቆይ የቻለው በምእራባውያንና ግብጽ በሚደረግለት መጠነ ሰፊ ድጋፍ የተነሳ እንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡  ለዚህም ነው አለም በተለይም የምእራቡ አለም የሰሜኑን ጦርነት ወይም ግጭት በተመለከተ አንድ አይነት አመለካከት የሚያንጸባርቁት( ወያኔን በብዙ መልኩ የሚደግፉት፣ በኢትዮጵያ ላይ የፕሮፖጋንዳ ጦርነት የሚከፍቱት፡፡) ወያኔን የሚደግፉ እና በአለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እንዳሉት በአንዳንድ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ምሁራን የጥናት ወረቀቶች ላይ ተጠቅሶ ይገኛል፡፡ ( ለአብነት ያህል በአምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ሂዩማን ራይትስወች፣ዩኤስኤይድ፣ ተቀጥረው የሚሰሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ይጠቀሳሉ፡፡ (TPLF has many people at the top of the western echelon: WHO, Amnesty International, Human Rights Watch, USAID). የወያኔ ጥንካሬ የሚመነጨው ከእነኚህ አለም አቀፍ ሀይሎች እንደሆነ መታወቅ ይኖርበታል፡፡ ለዚህም ይመስለኛል የኢትዮጵያ መንግስት ለሰሜኑ ኢትዮጵያ ችግር መፍትሔ ለማስገኘት ያስቸገረው፡፡( ሌሎች እንደ የጎሳ ፖለቲካ የመሰሉትን የሀገሪቱን የፖለቲካ ችግር ሳንዘነጋ ማለቴ ነው፡፡)

ያለ ኢትዮጵያ ፈቃድ ጣልቃ መግባት አለብኝ ለሚለው አለም አቀፉ ሀይል የማቀርበው ምክር ሃሳብ

የውጭው አለም በተለይም የምእራቡ አለምና የተባበረችው አሜሪካ በአንድ ሀገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡት በሚከተሉት ሶስት ምክንያቶች እንደሆነ የነገው የሀገሪቱ ወጣት ትውልድ ማወቅ አለበት፡፡ እነኚህም፡-

  • ብሔራዊ የጸጥታ ጉዳይ
  • ብሔራዊ የኢኮኖሚ ጸጥታ ጉዳ
  • የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ናቸው፡፡

የአለም ሀይሎች በእርግጥ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚደማ ልብ ካላቸው፣በኢትዮጵያ ምድር ሰላም እንዲሰፍን የሚባጁ ከሆነ ከላይ እንደ የመፍትሔ ሃሳብ የቀረቡትን ነጥቦች ገቢራዊ ማድረግ አለባቸው የሚለው የግል አስተያየቴ ነው፡፡ ለትግራይ ህዝብ የሚስቡ ከሆነ ችግሩን ለኢትዮጵያ ህዝብ መተው አለባቸው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነቱን ካገኘ ለችግሩ የመፍትሔ ሃሳብ ማመንጨት አያዳግተውም፡፡

ኢትዮጵያን ለመርዳት ከፈለጋችሁ በብዙ መልኩ ልትተባበሩ ይቻላችኋል፡፡ ያለ አንድ ሀገር ይሁንታ በአንድ ሀገር ላይ ጣልቃ መግባት፣ ለአንድ ወገን ብቻ ማድላት ዘለቄታዊ ሰላም ማስፈን አይቻልም፡፡ ለማናቸውም ቸር ወሬ ያሰማን፡፡

 

Filed in: Amharic