>

የኦነግ የሃይማኖት ክንፍ ፕሮፓጋንዲስቶቹ እነ አሕመዲን ጀበል በሃይማኖቱ ስም የከፈቱት ጸረ አማራ ዘመቻ!  (አቻምየለህ ታምሩ)

የኦነግ የሃይማኖት ክንፍ ፕሮፓጋንዲስቶቹ እነ አሕመዲን ጀበል በሃይማኖቱ ስም የከፈቱት ጸረ አማራ ዘመቻ! 
አቻምየለህ ታምሩ

ጎንደር በሁለቱም ወገን የተጎዱት ወንድማማቾቹ አማሮች ናቸው። በዚህ በወንድማማቾቹ ላይ በድረሰው ጉዳት ግን ወንድማማቾቹን ለማጣላት ከጣራው በላይ የሚሰማ ጩኸት የሚያስጮሁት ትናንትና ከወለጋ፣ ከጅማ፣ ከኢሉባቦር፣ ወዘተ ሙስሊም አማራዎች በግፍ ያሰደዱት፣ ንብረታቸውን የቀሙት፣ የገደሉትና ሰፋሪዎች ብለው ቤታቸውን ያፈረሱት ጸረ አማራዎቹ  ኦነጋውያን እነ አሕመዲን ጀበል ናቸው።
የወለጋ ምድር በየቀኑ በደም የሚጨቀየው በአማራ ሙስሊሞች ደም ነው። ወለጋና ኢሉባቦር  «በ1977 የድርቅ ወቅት ከወሎ መጥታችሁ የሰፈራችሁ አማሮች ናችሁ» ተብለው በጅምላ እየተፈጁና የተረፉት ሃብታቸው እየተዘረፈ፣ ቤት ንብረታቸው እየተቀማ፣ በሕይዎታቸውና በአካላቸው ላይ ጉዳት እየደረሰ የሚባረሩት ሙስሊም አማሮች በየከተማው በመጠለያ ውስጥ ከነሕጻናት ልጆቻቸው ጋር ፍዳቸውን እያዩ ይገኛሉ።
ጎንደር ደረሰ ከተባለው የንብረት ጉዳት  በሚሊዮኖች እጥፍ የሚሆን ፍዳና መከራ አማራ ናችሁ ተብለው ከከወለጋና ኢሊባቦር በተባረሩ ሙስሉም አማሮች ሕይወትና ንብረት ላይ በአሕመዲን ጀበል ተከታዮች ጉዳት ደርሷል። ይህ ሲሆን ግን የኦነግ የፕሮፓጋንዳ ጸሐፊዎቹ እነ አሕመዲን ጀበል አንዳች ነገር ትንፍሽ አላሉም።
የአማራ ጥላቻን መመሪያቸው ያደረጉት ኦነጋውያኑ እነ አሕመዲን ጀበል ባለፈው ሰሞን ሞጣ፣ አሁን ደግሞ ጎንደር ላይ የተከሰቱ  የአማሮች ጉዳቶች ሰርግና ምናሽ እያደረጉ ያለው አማራን የሚያጠቁበትና መንጋቸውን በጸረ አማራነት የሚቀሰቅሱበት እድል ስለተፈጠረላቸውን እንጂ ለሙስሊም አማሮች ተቆርቁረው አይደለም። እነ አሕመዲን ጀበል ለሙሊስም አማሮች ቢቆረቆሩ ኖሮ ሞጣና ጎንደር በሙስሊሞች ላይ ከደረሰው ጉዳት ስንት እጥፍ የሚሆን አማራ እስላም በግፍ በጅምላ የተፈጀባቸውንና ንብረታቸው ለወደመባቸውና ለተዘረፈባቸው የወለጋና ኢሉባቦር ሙስሉም አማሮች ሲቆረቆሩ እናገኛቸው ነበር።
ፋሽስት ወያኔና ናዚ ኦነግ የአማራ እስላሞችን በወለጋ፣ በመተከል፣ በወሎና በሸዋ በጅምላ ሲፈጇቸው፣ ጥሪታቸውን ዘርፈው ከቤታቸው አፈናቅለው ሜዳ ላይ ሲጥሏቸው፣ ቅዱስ ቁርዓናቸውን ሲያቃጥሉ፣ መስጂዳቸውን በመድፍ ሲደበድቡና ሲያወድሙ፣ በአገልግሎት ላይ የነበሩ ሸኾችን፣ ኡላማዎችንና ደረሳዎችን በዱልዱም ሲያርዱ፣ መስጂድ ውስጥ ቢራና ሴት ይዘው ገብተው በመስጅድ ውስጥ ነውር እየፈጸሙ ሲያረክሱት ምንም ትንፍሽ ያላሉና ምንም ያልመሰላቸው የኦነግ የሃይማኖት ክንፍ ፕሮፓጋንዲስቶቹ እነ አሕመዲን ጀበል  ጸረ አማራነታቸውን በእስልምና ስም ሸፍነው በአማራ መካከል የሆነ ነገር የተፈጠረ በመሳላቸው ቁጥር የዋሆችን ለማጥመድ ከጣራው በላይ የሚጮኹት የኦነግነት እንጂ የሃይማኖት አላማ ኑሯቸው አይደለም።
የጎንደር አማሮች በሃይማኖት ሊለያዩዋችሁ የተሰለፉትን ኦነጋውያኑን እነ አሕመዲን ጀበልን የምታስገቡበት ቀዳዳ አትክፈቱ። ጥፋተኞችን ለፍርድ አቅርቡ። የወደመውን ንብረታችሁን እንደ ጥንቱ ልማዳችሁ በጋራ አሰሩት። የተቃጠለውን የጋራ መገልገያችሁን በጋራ ወደ ነበረበት መልሱ። ለዚህ መላው አማራና አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ከጎናችሁ ነው። በናንተ በአማሮች መካከል የሃይማኖት ወንድሞች መስለው የሚሰብኳችሁ እነ አሕመድን ጀበል አማሮች ስለሆናችሁ ብቻ ከጅማ፣ ከወለጋ፣ ከኢሉባቦር ሰፋሪዎች ናችሁ ብለው የሚያባርሯችሁ፣ ጠላት አድርገው በዱልዱም የሚያርዷችሁና ሀብት ንብረታችሁን የሚቀሟችሁ ኦነጋውያን እንጂ መንፈሳዊ ሰዎች አለመሆናቸውን ከወለጋና ለኢሉባቦር አማራ በመሆናቸው ብቻ ዛሬ የሃይማኖት ወንድሞች መስለው በሚቀርቧችሁ የአሕመዲን ጀበል ተከያዮች ከተገደሉትና ከተፈናቀሉት ወገኖቻችሁ ተማሩ።
እነ አሕመዲን ጀበልና ፋሽስት ወያኔና ናዚ ኦነግ የአማራ እስላሞችን በወለጋ፣ በመተከል፣ በወሎና በሸዋ በጅምላ ሲፈጇቸው፣ ጥሪታቸውን ዘርፈው ከቤታቸው አፈናቅለው ሜዳ ላይ ሲጥሏቸው፣ ቅዱስ ቁርዓናቸውን ሲያቃጥሉ፣ መስጂዳቸውን በመድፍ ሲደበድቡና ሲያወድሙ፣ በአገልግሎት ላይ የነበሩ ሸኾችን፣ ኡላማዎችንና ደረሳዎችን በዱልዱም ሲያርዱ፣ መስጂድ ውስጥ ቢራና ሴት ይዘው ገብተው በመስጅድ ውስጥ ነውር እየፈጸሙ ሲያረክሱት ምንም ትንፍሽ ያላሉና ምንም ያልመሰላቸው ኦነጋዊ  ኡስታዞች አማራውን በሃይማኖት ከፋፍለን ለማጣላት ይጠቅመናል ብለው የሚያስቡትን አላማ ለማሳካት የማይፈነቅሉት ድንጋይና አዛኝ መስለው የማያነጉቱት ቅቤ የለም።
እኅታችን የጣይቱ ልጅ ትደመጥ!
Filed in: Amharic