>

የኦነግ የሃይማኖት ክንፍ ፕሮፓጋንዲስቱ አሕመዲን ጀበል የጻፋቸው ጸረ አማራ መፈክሮች...!!!  (አቻምየለህ ታምሩ)

የኦነግ የሃይማኖት ክንፍ ፕሮፓጋንዲስቱ አሕመዲን ጀበል የጻፋቸው ጸረ አማራ መፈክሮች…!!! 
አቻምየለህ ታምሩ

ጎንደር ላይ በተከሰተው ግጭት የተሳተፈ አንድ ፋኖ እንኳን ስለመኖሩ ማስረጃ ያቀረበ ያለው ሰው የለም። የኦነግ የሃይማኖት ክንፍ ፕሮፓጋንዲስቶቹ እነ አሕመዲን ጀበል ግን ፋኖን አሸባሪ እያሉ እያወገዙ ናቸው። ይህ የሚያሳዬው የኦነግ የሃይማኖት ክንፍ ፕሮፓጋንዲስቶቹ እነ አሕመዲን ጀበል የጎንደሩን ግጭት አስተክከው ከጣራው በላይ የሚጮኹት የሃይማኖት ጉዳይ ግድ ብሏቸው ሳይሆን  ኦነጋዊ መመሪያቸው ያደረጉትን ጸረ አማራነታቸውን በእስልምና ስም ሸፍነው የሚያራምዱበት እድል የተፈጠረላቸው ስለመሰላቸው ነው። የኦነግ የሃይማኖት ክንፍ ፕሮፓጋንዲስቶቹ እነ አሕመዲን ጀበል የሃይማኖት ጉዳይ ግድ የሚላቸው ቢሆን ኖሮ አባይን አቋርጠው ወደ ጎንደር ሳይሻገሩ አማራ በመሆናቸው ብቻ በየቀኑ ፍዳና መከራ ሲቀበሉ የሚውሉ የጅማ፣ የኢሉባቦርና የወለጋ ሙስሊም አማሮች ስቃይ ያምማቸው ነበር።
በአዲስ አበባ በኒና አንዋር መስጅዶች፤ እንዲሆም በጅማ በጎንደሩ ግጭት የተጎዶ ሙስሊሞች ጉዳይ አሳስቧቸው የነ አሕመዲን ጀበልን መፈክሮች አንግበው ጎንደርን ለማውገዝ ወደ አደባባይ የወጡ ሙስሊሞች እዚያው እዚያው ሸዋ ውስጥ ሸዋ ሮቢት፣ እንዲሁም በወለጋ በጅማ ናዚ ኦነግ አማራ በመሆናቸው ብቻ በጅምላ የፈጃቸውና ያፈናቀላቸው ሙስሊሞች ጉዳይ አያሳስባቸውም? ነው በናዚ ኦነግ ከወለጋ፣ ከጅማ፤ ከኢሉባቦርና ከሸዋ በጅምላ የፈጃቸውና የተረፉት ሃብታቸው እየተዘረፈ፣ ቤት ንብረታቸው እየተቀማ፣ በሕይዎታቸውና በአካላቸው ላይ ጉዳት እየደረሰ የሚፈናቀሉት በየከተማው በመጠለያ ውስጥ ከነሕጻናት ልጆቻቸው ጋር ፍዳቸውን እያዩ የሚገኙት ሙስሊም አማሮች የማያሟሉት የሙስሊምነት መመዘኛ አለ?
የጎንደር ሙስሊሞች ጉዳይ አሳስቧቸው ከጣራው በላይ የሚጮሁት ሙስሊሞች በወለጋና ኢሉባቦር «በ1977 የድርቅ ወቅት ከወሎ መጥታችሁ የሰፈራችሁ አማሮች ናችሁ» ተብለው በኦነግና በኦሕዴድ በጅምላ እየተፈጁና የተረፉት ሃብታቸው እየተዘረፈ፣ ቤት ንብረታቸው እየተቀማ፣ በሕይዎታቸውና በአካላቸው ላይ ጉዳት  እየደረሰ እንዲፈናቀሉ የተደረጉትና በየከተማው በመጠለያ ውስጥ ከነሕጻናት ልጆቻቸው ጋር ፍዳና መከራቸውን የሚያዩት ሙስሊም አማሮች ጉዳይም አሳስቧቸው በነቂስ ወጥተው ድምጻቸውን ከፍ አድርገው የሚያሰሙት መቼ ይሆን? ስለእነዚህ ግፉዓን ሙስሊም አማሮች ጉዳይ አንድ ቀን ትንፍሽ ሳይል ኖር በጎንደር የተከሰተውን ግጭት አስታክኮ በግጭቱ የተሳተፈ አንድም ፋኖ ስለመኖሩ ማስረጃ ማቅረብ በማይችልበት ሁናቴ ፋኖን ለማውገዝ ከጣራው በላይ የሚጮኽ አረመኔ  ቢኖር ዐይን ያወጣ ጸረ አማራ  ኦነጋዊ እንጂ የሃይማኖት ባለ ጉዳይ አይደለም።
እኛ ግን እንዲህ አሁንም በድጋሜ እንዲህ እንላለን፤ የጎንደር አማሮች በሃይማኖት ሊለያዩዋችሁ የተሰለፉትን ኦነጋውያኑን እነ አሕመዲን ጀበልን የምታስገቡበት ቀዳዳ አትክፈቱ። ጥፋተኞችን ለፍርድ አቅርቡ። የወደመውን ንብረታችሁን እንደ ጥንቱ ልማዳችሁ በጋራ አሰሩት። የተቃጠለውን የጋራ መገልገያችሁን በጋራ ወደ ነበረበት መልሱ። ለዚህ መላው አማራና አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ከጎናችሁ ነው። በናንተ በአማሮች መካከል የሃይማኖት ወንድሞች መስለው የሚሰብኳችሁ እነ አሕመድን ጀበል አማሮች ስለሆናችሁ ብቻ ከጅማ፣ ከወለጋ፣ ከኢሉባቦር ሰፋሪዎች ናችሁ ብለው የሚያባርሯችሁ፣ ጠላት አድርገው በዱልዱም የሚያርዷችሁና ሀብት ንብረታችሁን የሚቀሟችሁ ኦነጋውያን እንጂ መንፈሳዊ ሰዎች አለመሆናቸውን ከወለጋና ለኢሉባቦር አማራ በመሆናቸው ብቻ ዛሬ የሃይማኖት ወንድሞች መስለው በሚቀርቧችሁ የአሕመዲን ጀበል ተከያዮች ከተገደሉትና ከተፈናቀሉት ወገኖቻችሁ ተማሩ።
Filed in: Amharic