ባልደራስ
በአዲስ አበባ ትምህርት ቤት የተሰቀለ ህገ ወጥ የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ ዓላማን በቪዲዮ ቀርፀው ነበር!
/
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ እና የፓርቲው ረዳት የፅህፈት ቤት ኃላፊዋ ወ/ሮ ቀለብ ስዩም፣ እንዲሁም የካሜራ ባለሙያው ሱራፌል አንዳርጌ ትላንት በፖሊስና ሲቪል ደህንነቶች ለሰዓታት ታፍነው ከቆዩ ቦኃላ ተለቀዋል።
አመራሮቹ በአዲስ አበባ መንግሥታዊ ት/ቤቶች ከሰንደቅ ዓላማ ጋር በተያያዘ እየተደረገ ያለውን ለመመልከት በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ካራአሎ ቅድመ መጀመሪያ እና 1ኛ ደረጃ ት/ቤትን በመጎብኘት ላይ እያሉ ነበር በበርካታ ፖሊሶችና የደህንነት አባላት የታገቱት።
ርዕሳነ መምህራኑ ሰንደቅ አላማውን እንዲሰቅሉ እና ተማሪዎችን በኦሮምኛ እንዲያስዘምሩ ከበላይ አካል የቃል ትዕዛዝ የተሰጣቸው መሆኑን ገልፀዋል።
የተማሪዎች ወላጆች በበኩላቸው ያለፈቃዳቸው ልጆቻቸው በማያውቁት ቋንቋ እንዲዘምሩ መገደዳቸውን ተናግረዋል። እነኝህ አስተያየቶች የተቀረፁበትን ፊልም የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት እና የመንግሥት ደህንነቶች ነጥቀው ወስደውታል።
በከተማዋ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ያለው አርማ የመስቀልና ተማሪዎችን በኦሮምኛ የማስዘመር እንቅስቃሴው የኦሕዴድ-ብልፅግና መንግሥት ከሚመራበት ሕገ መንግሥት ውጭ መሆኑ ይታወቃል።