>

ሙጂቡ አምኖ ጭንብል ሲገለጥ....!!!  (ልጅ አቤል)

ሙጂቡ አምኖ ጭንብል ሲገለጥ….!!! 

ልጅ አቤል

ሀ…• ሙጂብ አሚኖ ሙስሊሞች አንዋር መስጊድ በአስቸኳይ እንዲገኙ አዘዘ። ጥሪም አቀረበ።
ሁ…• ያው እንደ ልቡ ሙጂብ አሚኖ ለአዲስ አበባ ፖሊስ የተቃውሞ ሰልፍ ስለምናደርግ ኮሚሽኑ ፖሊስ እንዳይልክ መመሪያ ሰጠ።
ሂ…• ከዚያ እንደልቡ ሙጂብ አሚኖ ሌሊቱን ሙሉ ሲያዘጋጅ ያደረውን መፈክር ለወጣቶቹ አድሎ ፎቶ ሲነሣ አረፈደ።
ሃ…• በመጨረሻም እነ ሙጂብ አሚኖ ለስፖንሠራቸው ለግብፅ ፎቶውን ለኩላት። ግብጽም በጋዜጦቿ ላይ አተመችላቸው።
“…ሙጂብ ግን ታድሎ።  እንደፈለገ እኮ ነው የሚሆነው። ሕግ አይጠይቀው፣ ፌደራል አያዘው። ታድሎ።
“…ያሁሉ ቤተ ክርስቲያን ሲቃጠል፣ ያ ሁሉ ክርስቲያን ታርዶ ለማልቀስ፣ ጋዜጣዊ መግለጫ እንኳ እንዳይሰጥ መከራውን የሚበላው የብልፅግና መንግሥት አሁን እንዲህ አይነት የግለሰብ አደገኛ ዐመፅ ያለ ከልካይ ሲነዛ አደብ ለማስገዛት አይፈልግም። ታዬ ደንደአና ኃይሉ ጎንፋ የዐማራን ፅንፈኛ፣ የዐማራን ፋኖ እናጠፋዋለን ያሉት በዚህ መንገድ መሆኑን ለማወቅ ጠንቋይ መሆን አይጠበቅብህም። ግብፅ ራሷ ፋኖ ይውደም አላለችም። ስታስቅ።
ሙጂቡ እንዳንተ ፍላጎት ቢሆን የሶማሌ የትግራይ እና የአማራ ህዝብ ሙሉ አልቆ ነበር. Trust me ምንም አታመጣም We already dumped your hate speech. You are calling yourself as a religious man but 99% of your post showed the whole Ethiopians that you have hidden agendas behind. Because of you so many innocent civilians have been killed. ዛሬ ጥሩ ነው እራስክን ደህና አድርገህ ስለገለፅክ ሌላውን ተወው እራሱ የሙስሊሙ ህዝብ ታዝቦሀል። የፖስት ናዳወችን አዘነብክ ቢቻልህ ገጀራ እና ነዳጅ አቀብለህ ይሄን መስኪን ህዝብ ማሳረድ ቋምጠሀል።
 ከዛም አለፍክና ጭንብልህን አውቅልቀህ “ፋኖ” ብለህ መጣህ አየህ። ፋኖ ስትል ፋኖ ሙስሊም መሆኑንም ዘነጋህ ለበይ ጭራቆች መንግስት አልባ ሆኖ ብቻውን በቀረበት እለት የእሳቱን ወጀብ እየሞቀ ህይወቱን ገብሮ የአማራን ህዝብ እና ኢትዮጵያን የታደገ ጀግና ነው ፋኖ። ፋኖ ህይወቱን ገብሮ የክፉ ቀኑን መከራ የተጋፈጠ ነው። የታቀደችው ሴራ አንዷ አካል ነበረች ፋኖን ላይ ያነጣጠረች ስለዚህ ፋኖ ከሌሉ በነፃ ሜዳ ይሄን መስኪን ህዝብ እንጨርሰዋለን ነው ህልሙ። ፋኖ እኮ ፋኖ ነው አልጠየቅክም እንዴ ፈኖ ማለት እኮ ወሎ ላይ የዛ ሰው በላ ጭራቆች የሙስሊም እናቶችን አጋድመው ሲያርዱ እና ሲደፍሩ የእሳት እረመጥ እየረገጠ መከላከያ ፈርቶ ጥሎ የወጣውን እሳት ያጠፋ ጀግና ነው ምንድነው የምታወራው? በሙስሊም አማራ ዘንድ ፋኖን ለማስጠላት የሄዳችሁበት እርቀት የስህተታችሁ መጀመሪያ መሆኑን ያሳያል።
 ፋኖን ሲጀመር የከተበው ማን እንደሆን አውቀሀል ነው ወይስ ጦርነቱ ትንሽ ረገብ ስላለ ረሳሀው ፋኖ እኮ ሙስሊም ክርስቲያንም ነው። እና የተከበሩ ነጭ ለባሽ ሂድና የዛ ጭራቅ ሰው በላወች የደፈሯትን ሙስሊም ክርስቲያን እናት ጠይቅ በእንባ ሲቃ ትነግርሀለች ቦንብ እየረገጠ አዳነን ክብራችን ነው ትልሀለች።
ከዚህ በሁዋላ ምንም አታመጣም ምንም ያንተ ክልል ላይ 189 ሙስሊሞች የታረዱበትን ቪዲዮ ልላክልህ ተባብራችሁ አጠፋን ያላችሁት መረጃ ከነ ሙሉ ቪዲዮው አለኝ ግን እኔ እንዳንተ ህሊናየን የሸጥኩ ሰው አይደለሁም በእኔ ምክንያት አንድ ሰው ቢጎዳ ህሊናየ እረፍት አያገኝም እንዳንተ ክርስቲያንን ውጣ ዝመት ግደል አልልም እንዳንተ ሙስሊም ውጣ ግደል አልልም ቢያድለን ኖሮ ህግ እና ስርአት ባሰፈን ነበር የምናየው ሁሉ ወንጀል መንግስታዊ መዋቅር ተጠቅሞ ክፋት እንደናንተ አይነቱ ህዝብን በይፋ ግደሉ ብሎ የሚያወጅቱን የማይጠይቅ መንግስት ስለተፈጠረ በያቅጣጫው አገሪቱ ተራ ሆነች። አየህ እንደ ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን ትንሽ እንኳን የሳቸውን ሀቂቃ ይዘህ ለፍትህ ቆመህ ባይ ኖሮ በተገረምኩ ነበር።
ቀሰቀስክ ጠራህ የቻልከውን እጅግ እስኪላጥ ፖሰትክ መንግስት አንተን አይነካህም ዋና አላማ አስፈፃሚ ስለሆንክ በቃ ብዙ አደረክ 189 ንፁሀን የአማራ ሙስሊሞች የታረዱበትን ቪዲዮ እና የጅምላ መቃብር በመንግስት ባለስልጣናት ሴራ ተሸፋፍኖ እንዲቀር ሲሆን ያኔ አንተ ትንፍሽ አላልክም ምክንያቱም ያንተ ቤት ሀጢያት ፅድቅ ነው እሱ ብቻ ግን እንዳይመስልህ ከወለጋ በሌሊት ሸሽተው አባታቸው በመንገድ ታሞባቸው በዛ ጭንቅ በአላህ ስም እርዱኝ ብለው የህክምና ደጅ የጠየቁትን ከእነ አባታቸው ያሳረዳቸውን ቪዲዮውስ እንልቀቀው ?
ዛሬ አንተ ወተህ የአማራ ሙስሊም ተቆርቋሪ ልትሆን ቀርቶ ፈጣሪ ምስክሬ ነው የአንተን እጅ የጨበጠ ሙስሊም ሁሉ የሚረክስ ነው የሚመስለኝ ሰላም ባሳቸው ላይ ይሁን የረሱል(ሰ.ዐ.ወ ) እንዲህ አይነቱን ሰው ተፀየፉ ብለው ነበር።
አሁንም አይቆምም ይቀጥላል ስርአት ህግ እና መንግስት በሌለባት አገር ፍትህ እና መሰረታዊ የመንግስት አቋም አይኖርም። ንፁሀን በአንደነዚህ ክፉወች ቅስቀሳ ይገደላሉ ቤተ እምነት ይፈርሳል በቀላሉ የሶስተኛውን ፈለም ህዝብ በወሬ በመንዳት እራሱን እንዲያወድም ይሆናል።
ፍትህ የሚመጣው በየፊናው በተናጠል በዘር በሀይማኖት እየጮሁ እየተገዳደሉ የሴራ ሰለባ እየሆኑ አይደለም።
አሁን ሁሉም ተበላሽቷል እራሱ መንግስቱም ተሳታፊ ነው በነገራችን ላይ የመንግስትን ተሳትፎ አሁን ህዝቡም አውቋል።
በእንደነዚህ አይነት ሴረኞች እና በመንግስት ዋና ቀማሪ ጎንደር ላይ ለተሰው ወንድሞቻችን አላህ የጀነት ይበላቸው እያንዳንዷን ሚስጥር ከሴራዋ ጥንስስ ጀምሮ ህዝቡ እና የክልሉ የፀጥታ ሀይል በመቀናጀት ወንጀለኞቹን በፍጥነት ወደህግ ማቅረብ አለበት እርስ በርስ ተናበቡ እመኑኝ ወንጀለኞቹን ተውትና ዋና የሴራው ባለ ቤቶችን ሙሉ መረጃ እኛ እንሰጣችሁዋለን። እንዲህ አይነት ወንጀል እንዳይደገም ሴራን ማክሸፍ ያስፈልጋል።
Filed in: Amharic