>

"ሀገር አቀፍነቱና ፋኖን ለማጥቃት መሆኑ ሲገባን ራሳችንን መከላከል ጀምረናል" የጎንደር ኗሪ (በጌጥዬ ያለው)

 

“ሀገር አቀፍነቱና ፋኖን ለማጥቃት መሆኑ ሲገባን ራሳችንን መከላከል ጀምረናል” የጎንደር ኗሪ 

በጌጥዬ ያለው


በጎንደር ከተማ ትናንት ሐሙስ ሚያዝያ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ ግጭቱ ዳግም አገርሽቶ ቆይቷል። ምክንያቱ ደግሞ   አንድ የተገደለ ሙስሊምን በቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ለመቅበር በተደረገ ሙከራ ነው። ሙከራው ጠባጫሪነት ነው የሚሉት የዓይን እማኞች አስክሬን ይዘው ሲመጡ በየሕንፃው ብሬን እና ስናይፐር የጠመዱ እና በእግር የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችን ይዘው ሲሆን የአረብ መገናኛ ብዙሃንም አስክሬኑን በሥፍራው እንደነበሩ ጠቅሰዋል።

በዚህም የሙስሊም መካነ መቃብርን አልፈው የጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ቅርጥ ግቢን ጥሰው ለመቅበር ባደረጉት ሙከራ አንድ ክርስቲያን ወጣት በግፍ ተገድሏል። ትምህርታቸውን በመቀፀል ላይ የነበሩ የአብነት ተማሪዎች በጥይት ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል። ከሁለቱም ወገን ከ10 በላይ ሰዎች ቆስለዋል። በጠባጫሪ እንቅስቃሴው ውስጥ በከተማዋ የማይታወቁ ሰዎች ጭምር እንደነበሩበትም ምንጮች አረጋግጠዋል።

በመሆኑም ጉዳዩ “ሀገር አቀፍ መሆኑን እና ፋኖን ለማፍረስ መሆኑን ስለተረዳን ራሳችንን መላከል ጀምረናል። ወጣቱም ሕዝቡን፣ ቤተክርስቲያናቱን እና አካባቢውን መጠበቅ ጀምሯል” ብለዋል ኗሪዎች።

ትናንት የፖለቲካ አላማን ባነገቡ ፅንፈኞች የተመሩ ሙስሊሞች በጎንደር መስቀል አደባባይ  ለመስገድ ጉዞ ሲጀምሩም የከተማዋ ወጣቶች በሰላማዊ ጠንካራ እምቢታ መልሰዋቸዋል።

ከወራት በፊት በከተማዋ በሚገኝ መስጊድ ውስጥ ኢ-መደኛና በጥላቻ የተሞላ ስብሰባ ይደረግ እንደነበር፣ የጦር መሳሪያም ወደ መስጊዱ በገፍ ይባ እንደነበር ለመንግሥት ጥቆማ መስጠታቸውን የገለፁት የጎንደር ኗሪ መንግሥት ተገቢውን ጥንቃቄ አለማድረጉን ገልፀዋል።

በተመሳሳይ በትናንትናው ዕለት በደባርቅ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያንን ለማቃጠል የተሞከረ ሲሆን በአካባቢው ኗሪ ፈጥኖ ደራሽነት ከሽፏል። በደብሩ የነበሩ የብነት ተማሪዎች ቆስለው ለሕሀክምና ጎንደር ከተማ ገብተዋል። ጎጆዎቻቸውም በከፊል ተቃጥለዋል።

Filed in: Amharic