>
5:13 pm - Tuesday April 18, 5437

ከዓለም አቀፍ አሸባሪዎች ተቀድቶ በአማራ ላይ የተፈፀመ የሽብር ስልት...!!! (ጌታቸው ሽፈራው)

ከዓለም አቀፍ አሸባሪዎች ተቀድቶ በአማራ ላይ የተፈፀመ የሽብር ስልት…!!!
ጌታቸው ሽፈራው

 

ሽብሩን በሚዲያ እንዴት ደገፉት ?  (ሚስጥራዊው የእነ አህመዲን ጀበል ሽብርን በሚዲያ የደገፉበት ሰነድ)
 ከስር የምትመለከቱት የእነ አህመዲን ጀበል ቡድን የዓለም አቀፍ አሸባሪዎችን ሁነኛ የሽብር ፕሮፖጋንዳ ተከትሎ በአማራና በኦርቶዶክስ ላይ ተግባራዊ እያደረገው ያለው ነው። ሰነዱ ከአንድ አመት በፊት የተሰራ ሲሆን ላለፉት ወራት በርካቶችን አሰልጥነው ወደ ተግባር ገብተዋል። ሰሞኑን በጎንደሩም ሆነ ከዛ ቀደም ባሉት የሽብር ተግባራት የሚጠቀሙት ይህን ስልት ነው። ምን አልባት በዚህ ሰነድ ጠላትና ወዳጅ ተብላችሁ የተፈረጃችሁ ግለሰቦች፣ ሚዲያዎች፣ ፓርቲዎች ትኖራላችሁ። ተመልከቱት።
ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ለማዳን ከጠላት ጋር በተፋጠጡበት ወቅት እነ አህመዲን ጀበል የሽብር ፕሮፖጋንዳ ስራ ላይ ነበር። በቅርቡ ከገጠሙት የእነ ሙፍቲ መጅሊስ ጀምሮ በርካቶች በጠላትነት ተፈርጀዋል። ከእነ ቴዲ አፍሮ እስከነ ሀሰን ኢንጃሞ በጠላትነት ተፈርጀዋል። እነ አብንና እናት ፓርቲ በጠላትነት ተፈርጀዋል። ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ አላማቸውን የሚደግፍ ፓርቲ ተደርጎ ተቀምጧል። አንዳንድ የመንግስት ባለስልጣናት እንቅፋት ይፈጥሩብናል ተብለዋል።
በዋነኛነት ጠላት የተባለው አማራው ነው። በፕሮፖጋንዳ እናሸብር የተባለው አማራውን ነው። የዚህ ፕሮጀክት ዋነኛ ተሳታፊ ሆነው የቀረቡት እነ አህመዲን ጀበል፣ ኢሳቅ እሸቱ፣  አብዱራሂም አህመድ፣ አብዱልጀሊል፣ ኢብራሂም ሙሉሸዋ ወዘተ ናቸው። የመጅሊሱ ከፍተኛ አመራሮች ጠላት ሲባሉ 17 ኮሚቴ ዋነኛው ደጋፊ ነው።
ይህን አላማቸውን ለማሳካት የማጥቃት ፕሮፖጋንዳን መጠቀም ቀዳሚው አጀንዳቸው እንደሆነ አስቀምጠዋል።
በአማራ ላይ የማጥቃት ፕሮፖጋንዳን እንጠቀማለን ብለው ካስቀመጧቸው  18  ስልቶች መካከል ጥቂቶቹ!
~ወጥመድ ውስጥ መክተት
~ማዋረድ
~ ፍርሃት መፍጠር
~ ችግራቸውን ማባባስ
~ማስጨነቅ
~ ጥርጣሬ መዝራት
~አንድነታቸውን መበታተን
~ማደናቀፍ ወዘተ ናቸው
ይህን ሁሉ በአማራ ላይ አድርገውታል። እያደረጉትም ይገኛሉ። ራሳቸው ሽብር ከፈጠሩ በኋላ እየፈፀሙት ያሉት በሙሉ በእነዚህ ሰነዶች የፃፏቸውን ነው። ይህን ሽብር የሚደግፍ ፋይናንስ ከተለያዩ አካላት አግኝተዋል። ይህን አላማ በአማራና በኦርቶዶክስ  ላይ እየፈፀመ ነው። ሽብር ነው። ሽብርን በሚዲያ ማስፋፋት ነው። አልቃይዳ ይህንኑ አድርጎታል። ስልቱ ቃል በቃል የተቀዳውም ከአልቃይዳና ከሌሎች አሸባሪዎች ነው።
ኢትዮጵያ በጦርነት ውስጥ ሆና፣ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ለማዳን ዋጋ በሚከፍሉበት ወቅት እነ አህመዲን ጀበል ቀጣዩን ሽብር ለማቀጣጠል የስልጠና ስራ ላይ ነበሩ። አንደኛው ሽብሩን በሚዲያ  መደገፍ ነው። ለዚህ ደግሞ ስለ ኢትዮጵያ የሚዘግቡትን ሚዲያዎች እንዴት ማጥቃትና ከእነሱ በተቃራኒ እንዴት አጀንዳ መስጠት እንዳለባቸው ሲዘጋጁበት ከርመዋል።
ለዚህም በዋነኛነት የገንዘብ ምንጩ ውሃብያን ከሚደግፉ ተቋማትና አካላት የተገኘ ሲሆን ዋናው የስራውና የፋይናንሱ አስተባባሪ አቶ አህመዲን ጀበል ነው።
የተለያዩ ቡድን ያሉት የዚህ ቡድን የተለያዩ ሚዲያዎችንና ግከሰቦችን በሚመቸው መልኩ በመፈረጅ ከእነሱ በተቃራኒ እንዴት ፕሮፖጋንዳ መስራት እንዳለበትና ለሽብር ተግባር የሚያስፈልገውን የሚዲያ ስራ መስራት እንዳለበት ሲዘጋጅበት ቆይቷል።
በዋነኛነት አህመዲን ጀበል፣ ከእሱ በመቀጠል ኢሳቅ እሸቱ፣  ሙጅብ አሚኖ፣ ነጃሽ ራዲዮ፣ አክመል ነጋሽ፣ አብዱራሂም አህመድ፣ የዛውያና ሌሎች ቲቪ ሰራተኞች የተካተቱበት ሲሆን በተለያዩ ምድብ ተከፋፍለው ሲሰሩበት ቆይተዋል። ይህ ቡድን “ሚዲያን በመቆጣጠር አገርን መቆጣጠር” በሚል አላማ አሁን ስለ ኢትዮጵያ የሚዘግቡ ሚዲያዎችና ግለሰቦችን መረጃ በማዛባት፣ 18 አይነት የፕሮፖጋንዳ ስልቶችን ነድፎ የሽብር ተግባሩን ለማገዝ ሲሰራ ከርሟል።
በዚህ ወቅት የተለያዩ የሽብር ተግባር በመፈፀም፣ በእስልምና ውስጥም ሆነ ከእስልምና ውጭ የሚጠሏቸውን ቡድኖች ስም በማጠልሸት፣ የሀሰት መረጃ በማጋላት፣ ግጭት በማባባስና ግጭት በመፍጠር የሚሰሩት በርካታ አክቲቪስቶቻቸውና ሚዲያዎቻቸው ውሃብያን በሚደግፉ ተቋማት፣ ግለሰቦችና ሌሎች አካላት ገንዘብ የሰለጠኑ የዚህ ቡድን አባላት ናቸው።
በእነ አህመዲን የሽብር ቡድን የተፈረጃችሁ ሚዲያዎች፣ ግለሰቦች ወዘተ ዝርዝራችሁን ታገኙታላችሁ።
አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ ሌሎቹን የዚህን ቡድን አላማዎች የምናወጣ ይሆናል!
Filed in: Amharic