>

"…የደም የራት ግብዣ…!  ( ዘመድኩን በቀለ)

“…የደም የራት ግብዣ…!

ዘመድኩን በቀለ

“…ዳግማዊ ግራኝ አሕመድ፣ ፀረ ቤተ ክርስቲያኑ ዐቢይ አህመድ ነገ በዳግማይ ትንሣኤው ዕለት በዕለተ እሁድ ያስፈጥራቸው ዘንድ የተመረጡ 16 ሊቃነ ጳጳሳትን ወደ ቤተ መንግሥት ለእራት ግብዣ መጥራቱ ተነግሯል። 16ቱ ሊቃነ ጳጳሳት የራት ግብዣውን “የዘገየ ቢሆንም”  በደስታ መቀበላቸው ተሰምቷል። 
“…ቅዱስ ፓትርያርኩም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ “ኢትዮጵያ በዚህ ጭንቅ ውስጥ ባለችበት ሰዓት፣ ሰው በራብ እንደ ቅጠል በሚረግፍበት፣ ያለ ሕግ በከንቱ በሚገደልበት፣ አብያተ ክርስቲያናትና ምዕመናንም እንደ ችቦ በሚቃጠሉበት በዚህ ሰዓት እኔ ወደ ራት ግብዣው አልመጣም፣ አልሄድም ብለው የነበረ ቢሆንም፣ ለብዙ ልምምጥና  ለብዙ ማስፈራራያዎችም አልበገርም ቢሉም ቆይቶ ግን ” የኢትዮጵያ የሃይማኖት ጉባኤ” የቦርድ አባላት በግንባር በመሄድ ከብዙ አሰልቺ ውትወታ በኋላ እሺ ማለታቸው ተሰምቷል። ያስደነግጣል።
“…እንግዲህ ምን ቀረን? ጳጳሳቱ ማፍጠር አለባቸው ተብሎ ቤተ መንግሥት ለመግባት ሲባል ብቻ እሺ ካሉ ምን ቀረን? የደስደስ መሆኑ ነው? እስቲ የሚሆነውን አብረን አብረን እናያለን። እኔ በበኩሌ አትሂዱ፣ አትብሉ ብዬ አልልም። አልናገርምም። ነገር ግን በእውነት የሚያደርጉት ከሆነ በዐብይ አሕመድ ወታደሮች በግፍ የተገደሉት ህጻናት፣ ካህናት፣ ምእመናን፣ የታረዱ ነፍሰጡሮችን ጽንሳቸውን በገበታው ላይ እንደመብላት አድርጌ ነው የምቆጥረው። ደማቸውን በፅዋ እንደመጠጣት። ቱ…!
“…ትናንት ያን መልእክት ከጻፍኩ በኋላ ሁለት ሊቃነ ጳጳሳት አናደርገውም። አንሄድም የሚል ማረጋገጫ ሰጥተውኛል። አንደኛው ሊቀጳጳስ ከፈለግክ ስሜንም ቢሆን አውጣውም ብለውኛል። አላደርገውም። ፓትርያሪኩን ካልተገኙ እርምጃዬ የከፋ ነው የሚሆነው ያለው አውሬ ዐብይ እንዲተናኮላቸው አልፈልግም። ግን አክብሮቴ ከፍ ያለም ነው።
“…የንጹሐን ደም በሚጠጣበት፣ የንጹሐን ሥጋ በሚበላበት በአረመኔው ማዕድ ላይ መሳተፍ ከአረመኔው በላይ አረመኔ መሆን ነው።
“…እየታዘባችሁ።
Filed in: Amharic