>

ዶ/ር አብይም ሆኑ ተከታዮቻቸው ከትህነግ የተማሩት የሚቃወማቸውንና የሚገዳደራቸውን ሰው ማግለል ነው...!!!   (ዶ/ር ሲሳይ መንግሥቴ)

/ር አብይም ሆኑ ተከታዮቻቸው ከትህነግ የተማሩት የሚቃወማቸውንና የሚገዳደራቸውን ሰው ማግለል ነው…!!!
  ዶ/ር ሲሳይ መንግሥቴ

የብልጽግና ፓርቲና የመሪያቸው ነገር በእጅጉ ግራ ያጋባል፣ በአንድ በኩል በርዕዮተ ዓለምና በፖለቲካ ፕሮግራም ከብልፅግና ፓርቲ ፍጹም ተቃራኒ የሆኑ የፖለቲካ ሰዎችን ለማሳተፍ በሚል ሰበብ ይሾማሉ። በሌላ በኩል በመርህ ደረጃ የብልፅግና ፓርቲን ዓላማ ደግፈው በተግባር የሚታዩ ችግሮችን ግን ያለምህረት የሚተቹ ሰዎችን ያገላሉ።
ይኸ ሁኔታ ከማንም በላይ የሚጎዳው ብልጽግናንና መሪውን እንጂ የሚገለሉ ሰዎችን አይደለም። ዶ/ር አብይም ሆኑ ተከታዮቻቸው ከትህነግ የተማሩት የሚቃወማቸውንና የሚገዳደራቸውን ሰው ማግለል ነው። ትህነጎች ለሁለት በተሰነጠቁ ጊዜ የራሳቸውን መሪዎች በአሸናፊነት ስሜት ውስጥ ሆነው ከስራ አገዷቸው፣ ከቤትም አባረሯቸው።
ሰሞኑን ብልጽግናም ሆነ መሪዎቹ ይህንን የተሳሳተ ፈለግ የተከተሉ ይመስላሉ፣ ዮሀንስ ቦያለው የዚህ ቂመኛ የሆነ እርምጃ ሰለባ ሆነዋል። ሌሎቹም ከዚህ ቂመኛ እርምጃ ላያመልጡ ይችላሉ። በጣም የሚያሳዝነው ነገር ሁሉም ነገር በማስመሰልና በጥላቻ የተሞላ መሆኑ ነው። የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆኖ አለመመረጥና የተለየ ሀሳብ መያዝ ከሀላፊነት ማስነሳቱ ደግሞ ገራሚ ነው።
ለማንኛውም ዮሀንስ ቦያለው ወደ ድርጅቱ የተመለሰው ለውጡን ወደ ፊት ለማስኬድና ህዝቡን ለመጥቀም በማሰብ እንጂ ስልጣን ይዞ በመንግስት ኮብራ ለመንፈላሰስ አልነበረም። ይኸንማ ቀደም ሲል ትቶት ወጥቶ ነበር። ምናልባትም ዶ/ር አብይ ገና ተራ ሰው እያሉ ዮሀንስ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ነበር። አሁንም ጥሩ ሞያና የህዝብ ፍቅር ስላለው የትም ሊወድቅ አይችልም።
ሲሳይ መንግሥት)ዶ/ር)
የብልጽግና ፓርቲ የአ/አበባ ም/ቤት አባል
Filed in: Amharic