>
5:26 pm - Friday September 15, 9589

የባልደራሱ ቢንያም ታደሰ በድጋሜ ታሰረ (ጌጥዬ ያለው)

የባልደራሱ ቢንያም ታደሰ በድጋሜ ታሰረ

ጌጥዬ ያለው

የአድዋና የካራማራ የድል በዓላትን ሰበብ በማድረግ ከአንድ ወር በላይ በግፍ በአባ ሳሙኤል ወህኒ ቤት ታስሮ የቆየው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አባሉ ቢንያም ታደሰ በድጋሜ በፖሊስ ታስሯል። ቢንያም ከሰሞኑ በስልጤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞችና አብያተ ክርስቲያናት ላይ እየደረሰ ያለውን ሃይማኖታዊ ጥቃት ሲያወግዝና አንድነትን ሲሰብክ ቆይቷል። ወጣቱ ከዚህ ቀደም ኦርቶዶክሳውያን ሲታሰሩም ታስሮ ቆይቷል።
ቢንያም በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የታሠረ ሲሆን በቀድሞው ማዕከላዊ፣ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛል።
Filed in: Amharic