>

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ታሰሯል....!!! (ጋዜጠኛ መአዛ መሀመድ)

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ታሰሯል….!!!

ጋዜጠኛ መአዛ መሀመድ
በትናንትናው ዕለት 4 ስዓት አካባቢ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ከመኖሪያ ቤቱ ከ ሃያት አካባቢ በፀጥታ ሃይሎች ለ
ጥያቄ እንፈልግሃለን ተብሎ መወሰዱን እና  እና በየትኛው ፖሊስ ጣቢያ እንደታሰረ ማወቅ እንዳልቻሉ የስራ ባልደረቦቹ ነግረውናል።

ከማሰሩ መሰወሩ ምን ይሉታል…???

መስከረም አበራ
የዜጎችን ህይወት ለማዳን ሲሆን በስራቀን የማይገኘው መንግስት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን ትናንት በእሁድ ቀን አስሮታል፡፡ ጎበዜ ከኢሳት የተባረረው ነገ በአይን የሚታየውን ሃቅ ዛሬ ለምን ዘገብክ ተብሎ ነው፡፡ ከዛ ጊዜ ወዲህ ጥርስ ውስጥ እንደገባ ግልፅ ነው፡፡ ከእውነት ጋር ተጣልቶ ወዴት እንደሚደረስ የምናየ ነው፡፡
ትናንት ጠዋት ላይ አያት አካባቢ ወደሚገኘው የጎበዜ ቢሮ መጥተው “ለጥያቄ ትፈለጋለህ” ብለው ይዘውት መልሰው ደግሞ “ከሰው ጋር ተመሳስለህብን በስህተት ነው የያዝንህ” ብለው ለቀውት ነበር፡፡ ደግሞ ወደ ማታ ወደ ቤቱ ሄደው በአጥር ዘለው ገብተው ይዘውት ወደ ማይታወቅ ቦታ ወስደውታል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የታሰረበትን ቦታ አውቀው የሚለብሰው ልብስና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን ማቅረብ እንዳልቻሉ ጓደኞቹ ነግረውኛል፡፡
ያለፍርድ ቤት  መታሰሩ ሳያንስ ቦታውን መሰወር፣የታሰረበትን ምክንያት አለማሳወቅ ምን ይባላል?????? ወይስ አሁንም በአስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር ውስጥ ላይ ነው ያለነው???
Filed in: Amharic