>

ፋኖነት ጥበብ ነው!!!  (ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ)

ፋኖነት ጥበብ ነው !!!

ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ

 

ፋኖነት መንፈስ ነው የጀግና ልጅነት የሚወረስበት

ፋኖነት አቅም ነው የጀግና ጉልበት የሚታደስበት

ፋኖነት ጥበብ ነው ልብ የሚበራበት፤ ፋኖነት ጥበብ ነው ታዳሚ ያለበት

ፋኖነት ረቂቅ ነው ሁሉም የሆነበት

ፋኖነት ሀሳብ ነው

በልባችን ፅላት ነው የተሞሸረው

ቃርሚያ ውስጥ ያደጉ የነቀርሳ እባጮች

አፍ ሲከፍቱ ታዩ በዚህ ቆራጥ ዘማች

ፋኖነት አይወይብ፣ አይገረጣ ቶሎ

ሲዘከር ይኖራል  በድፍረት ተንጣሎ

ተምጦ ተወልዶ ተጠምቆ በብሶት 

የሀገር መቋሚያ ነው የሚመረኮዙት

ፋኖነት ሀሳብ ነው

በልባችን ፅላት ነው የተሞሸረው

ፋኖነት መንገድ ነው መቋጫ የሌለው

በትውልድ መካከል  የሀረግ ገመድ ነው

ሁላችን ፋኖ ነን፤ ማን ከማን ይለያል

ባርነትን ጠልተን ነፃነት ናፍቆናል

ፋኖነት ራዕይ ነው ነፃ ሚወጡበት

ፋኖነት ሀሳብ ነው ትጥቅ ማይፈታበት

ፋኖነት ታሪክ ነው እውነት የሚያድርበት 

ፋኖነት ኩራት ነው ሀገር ሚድንበት፡፡

Filed in: Amharic