>

ቱርክና ስልጤ…!! (ዘመድኩን በቀለ)

ቱርክና ስልጤ…!!

ዘመድኩን በቀለ

“…ግራኝ አህመድ የተገደለው ጎንደር ውስጥ ነው። ጎንደር ደግሞ ዐማራ ነው። ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የሚበዛው ዐማራ። ያኔ የግራኝ አህመድ መሳሪያ አቀባይዋ ደግሞ ቱርክ ነበረች። ግራኝ ሲሸነፍ አብራ የተሸነፈችው ቱርክ ነበረች። ህልሟ በአጭር የተቀጨው በዚህ ምክንያት ነበር። 
“…አሁን ቱርክ ዳግማዊ ግራኝን ያገኘች መስሏታል። ኦርቶዶክስን መበቀያው፣ የግራኝ አሕመድን ገዳይ ጎንደርን መበቀያው ጊዜ አሁን ነው ብላ ቆርጣ መነሣቷ ነው የሚታየው። ዜማ ቀረሽ ጎንደር ጎንደር የሚል መግለጫም የምታወጣው ለዚሁ ነው።
“…ጎንደርን ማፍረስ፣ መዋጥ የኢትዮጵያን ፖለቲካ መቆጣጠር ነው ባዩ ዐቢይ አሕመድ አስቀድሞ ከጎንደር ሴት ያገባው፣ ወዳጅ መስሎም በአማችነት የተጠጋውም ለዚሁ ነው። አሁን ጎንደርን ለማፍረስ ፋኖን ማፍረስ በሚለው ስትራቴጂው መሠረት ዊኒጥ፣ ዊኒጥ እያለ ነው። በጣም እየደከሙ ነው። ነገር ግን አይሳካም።
“…ለማስታወስ ያህል ጎንደር የግራኝ አህመድ መቀበሪያ ስፍራ ነበረች። እደግመዋለሁ። ኢስጣንቡላውያን ስሙኝ ጎንደር የግራኝ አህመድ መቀበሪያ ስፍራው ናት። ሃላስ።
“…እየታዘባችሁ…!
Filed in: Amharic