ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ
እነዐቢይ አህመድ የምኒልክን ቤተመንግሥት ለመልቀቅ ወጥነዋል!
/
በአዲስ አበባ፣ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10፣ የካ አባዶ አካባቢ አዲስ ቤተ መንግሥት እና የመዝናኛ ማዕከል ለመገንባት ተብሎ፣ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ኗሪዎች ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲፈናቀሉ ተረኛው የኦሕዴድ-ብልፅግና መንግሥት አዟል።
የቤተ መንግሥት ግንባታው፣ ከፈረንሳይ ለጋሲዮን እስከ የካ አባዶ ድረስ ያለውን የእንጦጦ ሰንሰለታማ ተራሮችን በሚያካልለው ‘የጫካ ቤቶች ፕሮጀክት’ በተሰኘ መርሃ ግብር ስር የተካተተ ነው።
ኗሪዎች ባለፈው ሚያዝያ 14 ቀን 2014 ዓ.ም. በዕለተ ስቅለት፣ የባልደራስ አመራሮች ባሉበት በመንደራቸው የተቃውሟቸውን እና ቁጣቸውን ገልፀዋል።
‘የጫካ ቤቶች ፕሮጀክት ‘ ነባር የአዲስ አበባ ገፅታዎችን በልማት ስም የሚያጠፋና ከተማዋን አፍርሶ ለመሥራት የሚሞክር ነው። ከቤላ እስከ እንቁ ልደታ ለማርያም የተጀመረውን የመስቀል ፕሮጀክትም ያስተጓጉላል።
እንዲሁም፣ ለዐቢይ አህመድ ዋነኛ የማህበራዊ መሠረት ምላሽ በሚሰጥ መልኩም፣ የምኒልክ ቤተ መንግሥት ዋነኛ የመንግሥት ማዕከል መሆኑ እንዲቀር ለማድረግ አዳስ ቤተመንግሥት እንዲገነባ የሚያደርግ ነው።
አዲሱ ቤተመንግሥት ሲጠናቀቅ የምኒልክ ቤተመንግሥትን ወደ ሙዚየምነትና መዝናኛ ፓርክነት የመቀየር እቅድ አላቸው።