>

ወዲ ነጮ... "ወገኑን ያገለገለ"¡¡¡ (ውብሸት ሙላት)

ወዲ ነጮ… “ወገኑን ያገለገለ”¡¡¡

ውብሸት ሙላት

ወዲ ነጮ የከሃዲዎች ራስ ነው። የሰሜን ዕዝን ለማስመታት የመገናኛ ዘዴውን መቆጣጠር አስፈላጊ ነበር። ወዲ ነጮ ከጥቅምት 24 ቀደም ብሎ ወደ ትግራይ ተጓዘ፤ የመከላከያ ሠራዊቱ የመገናኛ ኃላፊው እሱ ስለሆነ። በሰሜን ዕዝ ሥር የሚገኙት ዘጠኝ ክፍለጦሮች የመገናኛ ኃላፊዎች አሏቸው። ከዘጠኙ መካከል ስምንቱ የወዲ ነጮ ብሔር አባላት ናቸው። ወዲ ነጮ ወደ ትግራይ ተጉዞ የመገናኛ ፕሮግራሙን በሙሉ ቀይሮት መጣ። ቀይሮት ወደ አዲስ አበባ እንደመጣ በጥቂት ቀናት ጥቅምት 24 ሆነ። (ታሪኩን የተካደው የሰሜን ዕዝ፣የ፶ አለቃ ጋሻዬ ጤናው መጽሐፍ ላይ አለ።)
 የሰሜን ዕዝ የመገናኛ ሥርዓት ከመከላከያ ሠራዊቱ ቁጥጥር ውጪ ሆኗል። የመገናኛ ሥርዓቱን የትሕነግ አድርጎታል። እናም የሰሜን ዕዝን በቀላሉ ለመምታት እንዲሁም የዕዙም ክፍለጦሮችና ብርጌዶች እርስ በርሳቸውም ሆነ ከማዕከል ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲቋረጥ ሆነ ። ግንኙነት ቢደረግም ግንኙነቱ በትሕነግ ቁጥጥር ሥር ስለሆነ መረጃዎቹ ለወገን ሳይሆን ጠቀሜታቸው ለጠላት ነው። እናም የሰሜን ዕዝ ተመታ። እንዲህ እንዲሆን የክህደት ፊታውራሪነቱን የመራው ወዲ ነጮ ነው። ወዲ ነጮ  ለአሸባሪው ት*ሕ*ነ*ግ ሠርቷል። አገርን የካደ ባንዳ ነው።
ወዲ ነጮ የኢትዮ ኤርትራ ጦርነትም በሶማሊያም  ውስጥ የክህደት ሥራዎችን ሠርቷል። በተለይ ከአልሸባብ ጋር በመመሳጠር የኢትዮጵያን የኮማንዶ ብርጌድ ማስመታቱን በብዙዎች ያውቁታል።
እናም፣ እንዲህ ዓይነቱ ርእሰ ከሐዲ በአርበኞች መቃብር ተቀበረ። በድል ቀን (በአርበኞች ቀን) ዋዜማ በአርበኞች መቃብር ኢትዮጵያን የካደው ባንዳ ተቀበረ።  የአሸባሪው አባል በክብር ቦታ ተቀበረ። ለዚያውም “ወገኑን ያገለገለ” ተብሎ በፓትርያርኩ ተመሠከረለት። “ወገኑን” ማለት ትርጉሙ ሌላ ካልሆነ በስተቀር። አሸባሪ በሚል በሠየመው ፓርላማ በጥቂት ሜትሮች ርቀት አሸባሪው ተወደሰ፤ተሞገሰ። “ትግራይ ትስዕር” ተባለ። የዚህ የተገላቢጦሽ ንባቡ  ‘ኢትዮጵያ ትሸነፍ’ ማለት ነው።
Filed in: Amharic