>
5:33 pm - Wednesday December 5, 2903

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት   ሊደብቀው ያልቻለው ጭፍጨፋ ...?!? (ስንታየሁ ቸኮል)

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት 
 ሊደብቀው ያልቻለው ጭፍጨፋ …?!?
ስንታየሁ ቸኮል

 

   “መጤዎች ለቃችሁ ውጡልን!”  ባዮቹ የአማራ አርሶአደሮችን በዘግናኝ ሁኔታ ገለው ሲያርዷቸው የአካባቢዉ መስተዳድር የፀጥታ ሃይልም እጁ እንዳለበት ተናግረዋል። 
 ምስራቅ ሸዋ፤ በናዝሬት እና አዋሽ መልካሳ መካከል 20 ኪ.ሜ.  ገባ ብሎ በተለምዶ ‘ሮጌ ባልዎልድ’ የሚባል ገጠራማ ቦታ ቅዳሜ ሚያዚያ 23/08/2014 ዓም በታጠቁ የኦሮሚያ ሃይሎች ዘግናኝ ግድያ ተፈፅሟል።
የሮጌ ባልዎልድ ማኛ ጤፍ በማምረት የሚታወቁት የአማራ አርሶ አደሮች የሚኖሩበት ስፍራ ድንገታዊ ጥቃት ተፈጽሟል።
በዚህም በሰዉና በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት እንዳደረሱ ለማወቅ ተችሏል።  በአካባቢ ከጊዜ በኋላ የገቡ የኦሮሞ ተጣቂዎች መጤዎች ቦታችንን መልሱ የእርሻ መሬታችንን “ለቃችሁ ውጡ” በሚል ብዙ ጊዜ ትንኮሳ ይደረግ ነበር።
 የክልሉ መንግስት የሮጌ አማራዎችን በቅድሚያ ትጥቅ በማስፈታት የኦነግ የሽብር ቡድን ከቦሰት ተራራ እየተነሱ በአካባቢው ተላላኪዎች እየተጠቆሙ ባሳለፍነው ቅዳሜ  አባትና ልጅን፣ ባልና ሚስትን ገለው በማረድ የጭካኔ ጥግ በማሳየት ሌላውም ፈርቷቸው እንዲሸሽ ተደርጓል።
በቦታው ህግ ለማስከበር ምቹ አይደለም የሚሉት የሮጌ ነዋሪዎች  የኦሮሚያ መስተዳድር በቂ መረጃ ቢኖረውም  በሚዲያም ስለነዚህ ሰዎች አያወራም በማለት በቁጣ ገልፀዋል።
የአማራ አርሶአደሮችን በዘግናኝ ሁኔታ ገለው ሲያርዷቸው የአካባቢዉ መስተዳድር የፀጥታ ሃይልም እጁ እንዳለበት ተናግረዋል። የክልሉ መንግስት መረጃውን ለሕዝብ እንዲያሳውቅ ጠይቀዋል።
Filed in: Amharic