>

ጎበዜ በመለቀቁ ብንደሰትም ሀይ ባይ ባጣው የአጋች ታጋች ድራማው ከልብ አዝነናል...!!! (ያሬድ ሀይለማርያም)

ጎበዜ በመለቀቁ ብንደሰትም ሀይ ባይ ባጣው የአጋች ታጋች ድራማው ከልብ አዝነናል…!!!
ያሬድ ሀይለማርያም

 

“ከምሽቱ 3:00 አይኔን በጨርቅ አስረው ቤቴ በር ላይ ጥለውኝ ሄደዋል።  እስከ ዛሬ የት እንዳቆዩኝ ግን አላውቅም…!!!”
ጎበዜ ሲሳይ በጤና መለቀቁ እጅግ መልካም ዜና ቢሆንም በሕገ-መንግስቱ አናት ላይ እንዲህ የተረማመዱበትን አፋኝ ሃይሎች ማነው ሃይ የሚላቸው? ማነው ተጠያቂው? መንግስት እና ሕግ ባለበት አገር፤ አንድ ሰላማዊ ሰው ቤት በአጥር ዘሎ መግባት፣ ከዛም አፍኖ መውሰድ፣ ከዛም ከቤተሰብና ከሕዝብ ሰውሮ ለ9 ቀናት ማቆየት፣ ከዛም ያለ ምንም ክስ አይኑን በጨርቅ አሥሮ ከቤቱ ደጃፍ ጥሎ መሄድ ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው? ጎበዜ በራሱ የፌስቡክ ገጽ ይህን ጽፎ እቤቱ መግባቱን አብስሮናል፤
“ከኢድ አልፈጥር አንድ ቀን ቀደም ብሎ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት በአጥር ዘለው አፍነው ከወሰዱኝ በኋላ አሁን ከምሽቱ 3:00 አይኔን በጨርቅ አስረው ቤቴ በር ላይ ጥለውኝ ሄደዋል።
እስከ ዛሬ የት እንዳቆዩኝ ግን አላውቅም። በጤናዬ ላይ የደረሰ ነገር የለም።”
ለወደፊቱ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት
በእውነት በጣም የሚያስደስት አጋርነት ነበር የታየው፤ ሰሞኑን በጠራራ ፀሐይ ከመኖሪያ ቤቱ ታፍኖ ተሰውሮ ለነበረው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን ከአፈና ለማድለቀቅ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የተደረገው ተፅዕኖ ፈጣሪ ድምፅ የሚበረታታ ነው።
መንግሥት የዜጎችን መብት በሚያፍንበት ጊዜ ዜጎች ለጋራ መብታቸው በአንድነት መቆም ለወደፊቱ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ሁላችንም ስለ ራሳችን ስንል ፍትሕ የተሞላበት የጋራ አገር ያስፈልገናል።
የጋዜጠኛ ጎበዜ ከታፈነበት መልቀቅ መልካም ቢሆንም ለዚህ ድርጊት የሚመለከተው አካል ማብራሪያ መስጠት አለበት።
Filed in: Amharic