>

ዜና ባልደራስ:- የሰንበት ተማሪዎች እንዳይሰበሰቡ  በአድማ በታኝ ፖሊስ ተከለከሉ!

ዜና ባልደራስ

የሰንበት ተማሪዎች እንዳይሰበሰቡ  በአድማ በታኝ ፖሊስ ተከለከሉ!

 

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች በአዲስ አበባ አምስት ኪሎ በሚገኘው ቅድስተ ማርያም ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዳይሰበሰቡ ፖሊስ ዛሬ አርብ ግንቦት 5 ቀን 2014 ዓ.ም. በሃይል ትኗቸዋል። “ፊታቸውን በመስታዎት የሸፋፈኑ ፖሊሶች መንገዱን በመዝጋትና ሃይል በመጠቀም  ገፈታትረውናል፤ ክስፍራውም አብርረውናል” ብለዋል አገልጋዮቹ። ፖሊሶቹ አድማ በታኝ የሚባሉ ናቸው።

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት የተውጣጡ የሰንበት ተማሪዎችና የቤተክርስቲያኗ አገልጋዮች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እየደረሰባት ስላለው ጅምላ ጭፍጨፋ፣ ስለ ሃይማኖት አባቶችና ምዕመናን በግፍ በመታረድ፣ ስለ ቤተክርስቲያናት በእሳት መቃጠል ብሎም ስለ እንቁ ልደታ ለማርያም ለመስቀሉ እሮጣለሁ የሩጫ መርሃ ግብር መከልከል ለመወያየት ታቅዶ ነበር።

ሆኖም መዘምራን የአገልግሎት ልብሳቸውን እያወለቁ ጭምር ከቤተክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ እንዲወጡ ተደርጓል። ወደ ቅጥር ግቢው ለመግባት በአካባቢው የነበሩትም ተበትነዋል።

Filed in: Amharic