>

"መልእክት ለጄነራል አበባው ታደሰ...!!!" (በመምህርት መስከረም አበራ)

“መልእክት ለጄነራል አበባው ታደሰ…!!!”

በመምህርት መስከረም አበራ


*…. ወታደር ብሄር የለውም ይሉት ጨዋታ አምጥታችኋል – ወታደርማ ብሄር አለው

*… ወታደርማ በኢትዮጵያ ብሄር አለው፤ ብሄር ባይኖረው ኖሮ ያኔ በወያኔ ዘመን የእርስዎ አባት የሚሆኑት ሳሞራ ቁጭ ብለው እርስዎ በጡረታ አይገለሉም ነበር

*….  ወታደር ብሄር ባይኖረው ህወሓት ሰሜን እዝን ለማጥቃት አልጋ በአልጋ አይሆንለትም ነበር

*….  ወታደር ብሄር ባይኖረው ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት እርስዎ አይመረጡም ነበር

*… እርስዎ እየተባበሩ ያሉት ፋኖን የማጥፋቱን ሴራ መንግስት ወገቡን ታጥቆ እየሰራው ያለው ለምን ይመስልዎታል ከአማራ ወገን ጀግና የሚባል አጥፍቶ  ክልሉን ብትንትኑን ለማውጣት መንገዱን አልጋ በአልጋ ለማድረግ ነው፤ ይታይዎ እርስዎ እየተባበሩ ያሉት ይህን ንሥሀ የሌለው ሀጤያት ነው።

*… ምን ቢያገለግሉ አማራ እስከ ሆኑ ድረስ እጣ ፈንታዎ በአማራ ህዝብ አይን መታየትና መገፋት ነው፤

ዛሬ የሾሙዎትም የህወሀት ስሪት ናቸውና የእርስዎ መጨረሻ ህወሓት ካደረገዎ ቢከፋ እንጂ አይሻልም።

*… ባለፈው በባለ ጊዜው ኤታማዦር ስር ሆኑ ተብለው በጡረታ ነው የተገለሉት አስተውለው ከሆነ አሁንም በባለጊዜው ኤታማዦር አጠገብ ያሉት እርስዎ ነዎት ፤ የአሁኑ እጣ ፈንታዎ በጡረታ መገለል ሳይሆን እንደ ጄነራል ሰአረ መሆንም ሊሆን ይችላል።

*… ይህ ስራዎ ጄነራል አበባው የሚለውን ስም በታሪክ መድረክ ባደፈ ብእር በከረፋ ቀለም የሚያጽፈው ነው የሚሆነው።

https://youtu.be/nlZ69ip27EoI

Filed in: Amharic