የመምህራን ትንቅንቅ በኦሮሚያ ሰንደቅ አላማ ጉዳይ…!!!
ስንታየሁ ቸኮል
*…. እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት መዝሙሩ “የክልል” መዝሙር ከመሆኑም ባሻገር፣ የመዝሙሩ መልዕክት ኦሮሞን የሚያሞግስ ሌላውን ደግሞ የሚዘልፍ እንደሆነ ቋንቋውን የሚሰሙ መምህራን አረጋግጠዋል።
*…. ከቀን ወደቀን እየከፋ የመጣዉ ተረኝነት በአዲስ አበባ ከተማ ት/ቤቶች የሰንደቅ ዓላማ እና የባንዲራ ሰቀላ ጉዳይ ባጭሩ ካልተቀጨ ወደከፋ ችግር እንዳያስገባ መምህራን ጥሪ አቀረቡ
ከውስጥ በተገኘ መረጃ በአዲስ አበባ ከተማ፤ መሪ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የኦሮሚያ መስተዳድር መዝሙር በዘመሩና የመስተዳድሩ ሰንደቅ አላማ በመሰቀሉ ከፍተኛ አለመግባባት ተፈጥሯል።
በተለይም ከኦሮሚያ መስተዳድር በተላኩ መምህራን እና በአዲስ አበባ ነባር መምህራን መካከል ውጥረቱ ከሯል።
በኦሮምኛ የሚያስተምሩ መምህራን በማናለብኝነት መዝሙሩ እንዲዘመር አድርገዋል። እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት መዝሙሩ “የክልል” መዝሙር ከመሆኑም ባሻገር፣ የመዝሙሩ መልዕክት ኦሮሞን የሚያሞግስ ሌላውን ደግሞ የሚዘልፍ እንደሆነ ቋንቋውን የሚሰሙ መምህራን አረጋግጠዋል። ሰንደቅ አላማው ከመሰቀሉ አስቀድሞ ለውስን ቀናት መዝሙሩ የተዘመረው ያለትምህርት ቤቱ አስተዳደር ፈቃድ ነበር።
ባለፈው ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ደግሞ፤ ቅዳሜና እሁድ ላይ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር በሌሉበት ራሳቸው የኦሮምኛ አስተማሪዎች ሰንደቅ አላማውን ሰቀሉ።
ይህንን ያደረጉት በከፍተኛ ደረጃ ቡድን በመፍጠርና በመደራጀት ነው። ለመስቀል ከፍተኛ ሚናውን የወሰዱት፦
1.መምህር አባይ ለማ 2.መምህር ጉቱ ጌታቸውና 3.መምህር ሰቦቃ ጉልማ የተባሉ ግለሰቦች ሲሆኑ ሌሎችንም በጎን በማሰለፍ ነው።
ከውስጥ ምንጮች እንዳረጋገጥነው ባለፈው ግንቦት 2 ቀን 2014 ዓ.ም. የክፍለ ከተማው የትምሕርት ፅህፈት ቤት ሓላፊ አቶ ቀነኒ ት/ቤቱ ስልክ ደውሎለት መጣ። ጉዳዩን ተመለልክቶ ራሱን ነፃ ለማስመሰል የት/ቤቱን አስተዳደሮች ማን ፈቅዶላቸው ነው የሰቀሉት አለ። ውስጡ ግን ሲታይ የእሱም እጅ አለበት። ለምን ለጉዳዩ ትኩረት ቢሰጠው ኖሮ እሱም መፍታት ይችል ነበር። ት/ቤቱም ከበስተጀርባ ገፊ ሀይል ለመምህራኑ አላቸው እንጅ ማንም ፈቃድ አልሰጣቸውም ብሎ መለሰ። አቶ ቀነኒም እንፈታዋለን በማለት ነገሩን መፍትሄ ሳይሰጡት ሄዱ። ከኦሮምኛ ውጭ ያሉት መምህራን የት/ቤቱ አስተዳደርን በቀን 03/09/2014 ጠዋት ላይ ባፈሰንደቅ አላማወሰ እንዳይሰቀልና መዝሙሩም መዘመር እንደሌለበት አቤቱታ አቅርበዋል። ምክንያቱ ደግሞ መምህራኖቹ ድርጊቱን የፈፀሙት በሀይልና የት/ቤቱንም ሆነ የሌላም አካል ህጋዊ ፈቃድ የለም የሚል ነው። “አሁንም መታወቅ ያለበት ግን ከውጭ ከባለሥልጣናት እና የሆነ ፖለቲካ የሚያራምድ አካል እጅ እንዳለበት ነው የሚያመላክተው። ሆኖም ባቀረብነው ጥያቄ መሰረት የት/ ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ደመላሽ ዘነበ ጥያቄውን ተቀብለው፣ጉዳዩን እንደያዙትና አቶ ቀነኒን አስመጥተው ምላሹን እንደሚሰጡን ነገሩን። በቀን 03/09/2014 ጠዋት ጠይቀን 5:00 ሰዓት ላይ አቶ ቀነኒ መጥቶ ከኦሮምኛ መምህራንና በአማርኛው ት/ት ክፍል ከሚያስተምሩ መምህራን በመምረጥ “የኦሮምያ ባንዲራ መሰቀልና የኦሮሞኛ መዝሙር በመዘመሩ” የተፈጠረ ችግር ተብሎ ቃለ ጉባኤ ተይዞ ብዙ ከወያየን በኋላ፣ በአጠቃላይ በውይይቱ ከበላይ አካል ትዕዛዝ ሳይሰጥ ሰንደቅ አላማ መሰቀል እንደሌለበትና መምህራኖቹ የፈፀሙት ህገ ወጥ ድርጊት እንደሆነ፤ አቶ ቀነኒ እየመረራቸውም ቢሆን መዝሙሩና ባንዲራው እንደ አዲስ አበባ አይሰቀልም ተብሎ ትዕዛዝ ስለተላለፈ ከዚህ በኋላ ለጊዜው አይሰቀልም ብለው ወሰኑ። ቃለ ጉባኤው ጋ ተፈራርመን ወጣን ።ውሳኔው ያላስደሰታቸው ፅንፈኞቹ መምህራን የእኛ ቦታ ነው በማለትና የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ነው በማለት፣በቀን 04/09/2014 ጠዋት ላይ ሀይላቸውን በማጠናከር ራሳቸው እንዲሰቀልና መዝሙሩ እንዲዘመር አደረጉ። አሁንም ተሰቅሎ ነው ያለው። መምህሩም እርስ በእርሱ ተፈራርቶ እስከአሁኗ ሰዓት ድረስ አለን” በማለት ሃሳባቸውንና የነበረውን ክንውን ገልፀዋል። ችግሩ በዚህ ከቀጠለ የሰው ሕይዎት ሊጠፋ እንደሚችልም አስጠንቅቀዋል።
በተያያዘ ዜና:-
የአባ ገዳ ባንዲራ ካልተሰቀለ በሚል የኦሮሞ መምህራን ከተማሪዎች ጋር ወደ ብጥብጥ ገቡ
ዛሬ ግንቦት 5/2014 ዓ.ም አያት ፀበል ኮንዶሚኒየም አካባቢ በሚገኝ ጨፌ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ላይ የኦሮሚያ ባንዲራ እንሰቅላለን አንሰቅልም በሚል በተማሪዎች እና መምህራን በተፈጠረ አለመግባባት ወደ ግጭት አድጎ ትምህርት ተቋርጦ ተማሪዎች ወደቤተሰቦቻቸው ተመልሰዋል። የኦህዴድ አባል የኦሮሞ መምህራን ጊዜዉ የኛ ነው በሚል እብሪት ከሕግና ስርዓት ውጪ እንደሚገኙ መምህራን እና ተማሪዎች ይገልፃሉ።