>
5:13 pm - Thursday April 18, 0774

ፋኖ ባለፉት 2 ቀናት በምን ላይ ይገኛል? እስሩ ወከባው በስፋት ቀጥሏል...!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

ፋኖ ባለፉት 2 ቀናት በምን ላይ ይገኛል? እስሩ ወከባው በስፋት ቀጥሏል…!!!

ቬሮኒካ መላኩ

•  በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ መራዊ ከተማ እና ደቡብ አቸፈር ወረዳ ዱርቤቴ ከተማ 32 ከመከላከያ ሰራዊት የተመለሱ ወጣቶች የአማራን ህዝባዊ ሀይል ተቀላቅላችኋል በሚል ምክኒያት በፖሊስ ታስረዋል። ከነዚህ መካከል 18 በመራዊ ፖሊስ ጣቢያ ከታሰሩ በኋላ 5ቱ ተለይተው ለመከላከያ ሰራዊት ተላልፈው ተሰጥተዋል፤ ያሳዝናል።

•በደቡብ ወሎ መካነ ሰላም ከተማ ከ20 በላይ የፋኖ አሰልጣኞች ትናንት ታስረዋል፤ ዛሬ የአካባቢው ወጣቶች ፋኖዎቹ እና የፋኖ አሰልጣኞቹ እንዲፈቱ የሚጠይቅ መፈከር ይዘው የከተማ አስተዳደሩ በር ላይ ድምፃቸውን አሰምተዋል። ይሁን እንጂ እስከ አሁን አልተፈቱም።

•በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ፣ አንጎት ወረዳ እና ላሊበላ ከተማ የዞኑና የወረዳ አመራሮች የመንግስት ሰራተኛው ፋኖዎችን ለማጥፋት የሚደረገውን እንቅስቃሴ እንዲደግፉ የሚዪትት ሰነድ ይዘው ህዝቡን ለማወያየት ሞክረዋል፤ ሁኖም መንግስት ሙሉ ተቃውሞ የገጠመው ሲሆን ይሔን በግልፅ የተቃወሙት ላይ ማስፈራሪያ እና ዛቻ እያደረሰባቸው እንደሆነ ታውቋል።

•የሸዋ አማራ ፋኖ አመራርና አባላት በጫጫ ከተማ በስራ ላይ እያሉ ትናንት ታፍሰው ታስረዋል። ፀጋውአከበረኝ የስልጠና ሀላፊ፣  ሙሉጌታ ወንዶሰን የሒሳብ ሹም እና አራጋው ፀጋው የተባላ የፋኖ አመራር ታስረዋል።

Filed in: Amharic