>

ዝክረ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ...!!! (ታደለ ጥበቡ)

ዝክረ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ…!!!

ታደለ ጥበቡ


እኚህ ታላቅ የቀዶ ጥገና ሕክምና ሊቅ መስዋዕት የሆኑት ለኢትዮጵያ ነበር። በመጀመሪያ የኤርትራን የመገንጠል ፍላጎት የኢሕአዴግ መንግስት ሲያፋጥነው ጉዳዩ ልክ አለመሆኑን በአደባባይ የተቃወሙ የግንባር ስጋ ናቸው።

ሕዝብ በየቦታው ሲገደል ሲፈናቀል ትርምስምሱ ሲወጣ ተቃውሞ በማሰማት ከፊት የመጡ ናቸው። በግፍ ታስረው ተሰቃይተዋል። እርሳቸው ችሎት በቀረቡ ቁጥር ፍርድ ቤት የምንገኝ ጋዜጠኞች ጭምር ይደርስብን የነበረውን መከራ አልረሳውም።

በመጨረሻም፣ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ እስር ቤት ውስጥ ታመሙ። ተገቢውን ሕክምና እንዳያገኙ የሕወሓት ኢሕአዴግ መንግስት ከለከላቸው። እርሳቸውም ሀኪም ስለሆኑ ስለ በሽታቸው ጉዳይ ተናገሩ። ተገቢውን ሕክምና ካላገኙ በአጭር ጌዜ ውስጥ እንደሚያልፉ ገለፁ። እናም በሽታቸው ታክሞ ወደማይድንበት ደረጃ ደረሰ። የዚያን ወቅት ኢሕአዴግ  ከእስር ቤት አወጣቸው። ለሕክምና ወደ አሜሪካ ሄዱ። ሊድኑም  አልቻሉም። ታላቁ ኢትዮጵያዊ አረፉ።

አስከሬናቸው ከአሜሪካ መጣ። ቅድስት ስላሴ ስርአተ ቀብራቸው እንዳይፈፀም መንግስት ብዙ ጫና አደረገ። በመጨረሻም  ቅዱስ ባለወልድ ቤተክርስትያን እንዲቀበሩ ተደረገ።  ለቀብራቸው ከወጡት ሰዎች መካከል ሁለት ወጣቶችን ቤተመንግስት አካባቢ የነበሩ ጠባቂዎች ተኩሰው  ሲገሏቸው አይቻለሁ።

በወቅቱ የፕሮፌሰር አስራትን የሕይወት ታሪክ ከተናገሩት ሰዎች መካከል አንዱ ታላቁ የታሪክ ፀሐፊ አቶ ተክለፃዲቅ መኩሪያ ነበሩ። እርሳቸውም እንዲህ አሉ፣ ለአስራት ሞት የመንግስት እጅ አለበት።

ውዱ እና ታላቁ ሰው ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ሆይ፣ ፈጣሪ ነፍስዎን ይማርልን።

የፕሮፌሰር አስራት ህልፈተ ህይወት ሀያ አንደኛ አመት መታሰቢያ

https://www.facebook.com/aster.mantegafto/videos/342817521282937/

Filed in: Amharic