በአዲስ አበባ ኮተቤ ብርሃነ ሕይወት ት/ም ቤት አመፅ ተቀሰቀሰ …!!!
ስንታየሁ ቸኮል
*…. ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ያላት ልዩ ጥቅም በመቃብራችን ላይ ነዉ የተማሪዎች የተቃውሞ ድምጽ
*… በአዲስ አበባ ከተማ መ/ደ ት/ቤቶች የኦሮሚያ ባንዲራ ከመስቀል እና መዝሙር ከማዘመር ጋር በተያያዘ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ወላጆች ጨርቁን በማውረድ መዝሙሩም ልጆቼን አይወክልም በማለት በድፍረት ተረኛዉን አገዛዝ እየተጋፈጡ ይገኛል። ይህ ሰላማዊ የተቃዉሞ ገለፃ በሌሎችም ት/ቤት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መምህራን ይገልፃሉ።
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ኮተቤ ብርሃነ ሕይወት መ/ደ/ ት/ቤት ተማሪዎች የኦሮሚያ ባንዲራ አንሰቅልም በማለታቸው ተረኛው የኦህዴድ መምህራን በማስገደድ ሲሰቅሉ በተማሪዎች አመፅ ወላጆች በር ሰብረው በመግባት ይውረድ ይሄ አዲስ አበባ እንጅ ኦሮሚያ አይደለም ሲሉ እረብሻ ተነስቷል። ተማሪዎችም በግቢው ውስጥ አመፅ ጀምረዋል ትምህርት ተቋርጧል መምህራኑም በዚህ ሁኔታ ማስተማር አንችልም በማለት እየወጡ ይገኛል።