>

የሲሸልሱ ስምምነት በአቋራጭ ዛሬ ተፈፅሟል.!!!!" (ቬሮኒካ መላኩ)

“. .የሲሸልሱ ስምምነት በአቋራጭ ዛሬ ተፈፅሟል.!!!!”

ቬሮኒካ መላኩ


የአማራ ልዩ ሃይል ከወልቃይት ሁመራ ኮሪደር ጠቅልሎ ወጣ። ዛሬ የወጣው የመጨረሻው 3 የአማራ ልዩ ሀይል ሻለቃም ዛሪማ አካባቢ እንዲሰፍር ተደርጓል። ፋኖ ግን ቀደም ብሎ ሙሉ በሙሉ ከአካባቢው ነቅሎ እንዲወጣ ሆኗል። በባዕከር እና ሁመራ እንዲሁም በሱዳን ኮሪደር ቀጠናውን ከአሸባሪ ሀይል ሲቆጣጠር የነበረው የኤርትራ ጦርም በአብይ አህመድ ውጡልኝ ትዕዛዝ፣ ዛሬ ሙሉ በሙሉ አካባቢውን ትቶ ወደ ራሱ ቀጠና እንዲሄድ ተደርጓል። አሁን ወልቃይት ሁመራ ኮሪደር ተሸፈነ የሚባለው በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሲሆን፣ መከላከያውም በአብይ አህመድ ቀጭን ትዕዛዝ ወልቃይትን ለቀህ ውጣ ሲባል ለቅቆ እንደሚወጣ ግልፅ ነው። ወልቃይትን ለወያኔ የሚሰጠው የሲሸልሱ ስምምነት በአቋራጭ ዛሬ ተፈፅሟል።

Filed in: Amharic