>

የበላይ ዘለቀ አገር ለኦህዴድ አፋኝ ቡድን እረመጥ  (የተዳፈነ ፍም) ሆኖ እንደቀጠለ ነው...!!! (ሀብታሙ አያሌው)

የበላይ ዘለቀ አገር ለኦህዴድ አፋኝ ቡድን እረመጥ  (የተዳፈነ ፍም) ሆኖ እንደቀጠለ ነው…!!! 

ሀብታሙ አያሌው


*…. ትንታጎቹ ጎጃሜዎች ሥራ ጀምረዋል። ሕዝቡ ፋኖ እኔ ነኝ እያለ አፋኞቹን እያስፈተለካቸው ነው።

ሰው ከደም መላሹ ጋር እንዴት ጠብ ይጭራል? ጥፊ ያላት ከተማ ነጋሪት ቢጎሰም አትሰማ ኾነ ነገሩ። አትዳኑ ተብለው የተረገሙት ብልጽግናዎች መንገዱ ጨርቅ እየኾነላቸው ነው።

መርጡለ ማርያም፣ ፍኖተ ሰላም፣ ሞጣ፣ አዴት፣ ዱርቤቴ፣ ዳንግላ እያለ ነው ክላ።

የኦህዴድ የአፈና ቡድን በአማራ ክልል ፍኖተ ሰላም ከተማ  ታርጋው በተሸፈነ መኪና የአፈናውን  ስምሪት ለማሳካት መራወጡን ቢቀጥልም… የጎጃም ህዝብ ተገቢውን ምላሽ እየሰጠ ይገኛል!!

1. የሞጣ ህዝብ የኦህዴድ ኮማንዶ ልጆቹን እንዳይበላ   ለመከላከል የአብዮት ጀማሪ ሆኖ አደባባይ ወጥቷል።

2. ምስራቅ ጎጃም (የጁቤ) የአካባቢው ህዝብ ወደ አደባባይ

ወጥቶ  ልጆቹን ከበላተኛ ማዳን ብቻ ሳይሆን እንደ ህዝብ

ወታደራዊ ልምምድ ወደ ማድረግ ተሸጋግሯል።

3. መርጡ ለማርያም ላይ ልማደኛው የብአዴን ሎሌ የአፈናው

ሙከራ ሲከሽፍ ያለምንም ጫረታ የህዝብ ሀብት ጭኖ

ለማስወሰድ ሞክሯል።

አይቀመሴው ህዝብ ግን ለሊቱን በየአቅጣጫው ገንፍሎ ወደ አደባባይ በመውጣት ፋኖ   ሲያወድስ ፣ በፋኖ መሪዎች ስም ግጥም ፣ሽለላ እና ቀረርቶ ሲያሰማ የጀነራል ተፈራን ስም ከፍ አድርጎ ሲያደምቀው  አድሯል።

4. በጎጃም – ልዩ ኃይል ወደ ህዝባችን አንተኩስም በማለት

ደማቅ ታሪክ አስመዝግቧል።

5 .ሞጣ ላይ ህዝብ ወደ አደባባይ የጎረፈው  አፋኙ የኦህድድ

ቡድን ከበባ ውስጥ አስገብቶት የነበረውን የፋኖ አመራር

ለማስለቀቅ ፋኖ በግልፅ እርምጃ ከበባውን ለመስበር

የአፀፋ እርምጃ  መውሰዱን ተከትሎ ነበር። በውጤቱም

ከበባው ተሰብሮ ፋኖ ነፃ ወጥቷል።  ህዝቡም ቤቱን ትቶ

አደባባዩን ጣህሪር ስኩየር አድርጎት አድሯል።

#የአማራህዝባዊእምቢተኛነት

     ድል የህዝብ ነው !!

Filed in: Amharic