>

ከፋኖዎች አንደበት:- "መስቀል እያሳዩ ዲሽቃ ተኮሱብን" የአማራ ሕዝባዊ ሃይል (ፋኖ) አባል በሞጣ

ከፋኖዎች አንደበት:-

“መስቀል እያሳዩ ዲሽቃ ተኮሱብን” የአማራ ሕዝባዊ ሃይል (ፋኖ) አባል በሞጣ


መጀመሪያ ጫካ ነበርን። አንድ አባላችን ድንገት ታፍኖ መወሰዱን ሰማን። “አባሎቻችንን አትንኩ፤ የአፈናችሁትንም ልቀቁ” እያልን ወደ ከተማ ስንሄድ ይባስ ብሎ ከ6ዐ በላይ የሚሆኑ ከሀገር መከላከያ ሰራዊትና ከአማራ ልዩ ሃይል የተመለሱ ወታደሮችን በሁለት መኪና አፍነው ከጎንቻ አመጧቸው።  አያያዛቸው ወደ ሌላ ቦታ ወስደው ለመሰወር ወይም ለመረሸኝ ሳይሆን አይቀርም። እነርሱን በሰላም መልቀቅ ስላልቻሉ ትንሽ የተኩስ ልውውጥ ተደረገ። በዚህ መሃያ አስቀድሞ የታፈነው አባላችን እና ስልሳዎቹን ምልስ ወታደሮች አስለቅን።

ከእነርሱም ስድስት ሰዎች ማርከን ያዝን። እግዚአብሔር አምላክ አግዞን ይህ ሁሉ ሲሆን ከእኛ በኩል እምብዛም የተጎዳ የለም።

በኋላ ቀርበን ስናያቸው የማረክናቸው የአማራ ልዩ ሃይል ልብስን የለበሱ ኦሮምኛ የሚናገሩ ሰዎች ናቸው።

እንደተለመደው የአገር ሽማግሌዎችንና ቄሶችን ልከው “ልቀቁልን አሉ። እኛም ‘ሰላም ከፈጠራችሁማ ምን ቸገረን’ ብለን ለቀቅንላቸው።

ከዚያም ቃላቸውን አጥፈው ሃይል ጨምረው በሦስት አቅጣጫ ቀይ ለባሽ የመከላከያ አጋዚ ኮማንዶዎችን አስመጥተው ከበባ ውስጥ አስገቡን። እነዚህ ኮማንዶዎችም ያው ኦሮሞዎች  ናቸው። በሰላማዊ ከተማ መስቀል አሳይተው ዲሽቃ ተኮሱብን። በየ ሕንፃዎች ላይ እየወጡ በዲሽቃና በስናይፐር ሲተኩሱ ብዙ ንፁሃን ኗሪዎችን ገደሉ። በእግዚአብሔር ቸርነት አሁንም እኛ ላይ እምብዛም ጉዳት አልደረሰም። አሁንም እያሳደዱን ነው ጫካ ነው ያለነው። (ጌ.ያለው)

Filed in: Amharic