>

"እባብ ለእባብ ይተያያል ካብ ለካብ!!!" (ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት)

“እባብ ለእባብ ይተያያል ካብ ለካብ!!!”

ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት


*. .. አሁን በእነ ዘመነ ላይ መንግስት የከፈተው የስም ማጥፋት ዘመቻ ትልቅ የፖለቲካ ዓላማ ያለው መሆኑን ብዙዎች የተገነዘቡት አይመስለኝም። ጉዳዩ ህግ የማስከበር አይደለም። አናርኪን ከመከላከልም ጋር አይገናኝም። ጉዳዩ የመንግስትን ሃይል የመጠቀም ብቸኛ መብት የማስጠበቅ አይደለም። ጉዳዩ ከላይ ከጠቀስኳቸው ነገሮች ከፍ ያለ ዓላማ ያለው ነው።

የዶ/ር አብይ አህመድ አስተዳደር ከህወሃት ጋር በሚያደርገው ግልፅነት የጎደለው ድርድር ብዙ መስዋዕትነት የተከፈለባቸውን የህዝብ አጀንዳዎች ለህወሃት እና ለፈረንጆች አሳልፎ ለመስጠት ቆርጦ ተነስቷል። ዶ/ር አብይ ስልጣኑን ለማንበርና የአማራን ህዝብ ጥቅም አሳልፎ ለመስጠት ስለወሰነ ይህንን ጥፋቱን ለህዝብ የሚያጋልጥና የአማራን ህዝብ አጀንዳዎች በተደራጀና በታቀደ ሁኔታ የሚገፋ ህዝባዊ ሃይል እንዲፈጥር አይፈልግም። ለእዚህ እቅዱ መፈፀም ደግሞ እነ ዘመነ ካሴ የጉሮሮ አጥንት እንደሚሆኑበት በሚገባ ተገንዝቧል። የአማራ ህዝብ አልቃሽ ብቻ ሁኖ የሚመራው ድርጅትም ሆነ ግለሰብ ሳይኖር ዶ/ር አብይ የፈለገውን ለፈለገው ሰቶ በስልጣኑ እንዲቀጥል እንደ አማራ ህዝባዊ ሃይል ያሉ አደረጃጀቶችን አስቀድሞ መምታት እንዳለበት ስለወሰነ ነው።

አሁን መንግስትን ደግፈው ጉዳዩን ህግ እና ስርዓት የማስከበር አድርገውና  ነገሩን አቃለው የሚያቀርቡ ሰዎች ነገ ዶ/ር አብይ የአማራን ህዝብ ጥቅም አሳልፋ ሰጠ እያሉ ዋና አስለቃሾች እንደሚሆኑ አልጠራጠርም። እውነት እንነጋገር ከተባለ የዶ/ር አብይን የአስተዳደር ብሂል ለመረዳት ባለፉት አራት ዓመታት በአማራ ህዝብ ላይ ከደረሰው ፍርጃ በላይ ምን ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል?

ስለሆነም የአማራ ህዝብ ሰቆቃ የሚያማችሁ፣ ለሞራላችሁና ለታሪካችሁ የምትጨነቁ ከሆነ ግልብ መመፃደቃችሁን ትታችሁ ከወንድሞቻችሁ ጎን እንድትቆሙ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

Filed in: Amharic