>

"... በኢትዮጵያ በቅርቡ የታሰሩ 11 ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ሰራተኞች በአፋጣኝ እንዲፈቱ ... !!! (ሲፒጄ)

“… በኢትዮጵያ በቅርቡ የታሰሩ 11 ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ሰራተኞች በአፋጣኝ እንዲፈቱ … !!!

ሲፒጄ

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በቅርቡ የታሰሩ ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ሰራተኞችን በአፋጣኝ እንዲፈቱ ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች (CPJ) ጥሪ አቀረበ። ባለስልጣናቱ የፕሬስ አባላትን ከማዋከብ እንዲታቀቡም ተቋሙ ጠይቋል።

መቀመጫውን በኒውዮርክ ያደረገው ሲፒጄ ትላንት ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ ከግንቦት 11፤ 2014 ጀምሮ በአማራ ክልል እና በአዲስ አበባ 11 ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ሰራተኞችን መታሰራቸውን አስታውቋል። ጋዜጠኞቹ እና የመገናኛ ብዙኃን ሰራተኞቹ የታሰሩት የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት “ህግ ማስከበር” ብለው በሚጠሩት እርምጃ መሆኑንም ተቋሙ ጠቅሷል።

የሲፒጄ የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ አንጌላ ኩዊንታል የአስራ አንዱ ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ሰራተኞች እስር “መንግስት ለፕሬስ ነጻነት እና ዜጎች ከብዙ ነጻ የሚዲያ ምንጮች ላላቸው መረጃ የማግኘት መብት ክብር እንደሌለው በድጋሚ ያሳየ ነው” ሲሉ ነቅፈዋል። “የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሁሉንም ያለ ክስ በአፋጣኝ ሊፈቱ ይገባል” ያሉት አስተባባሪዋ፤ ጋዜጠኞች በዘፈቀደ የመታሰር፣ የመጨቆን እና የሳንሱር ስጋት ሳይኖርባቸው መዘገባቸውን እንዲያረጋግጡም ጥሪ አቅርበዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ለማንበ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2022/6914/

ምንጭ:- ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

Filed in: Amharic