>

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ታሰረ!!

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ታሰረ!!

ባልደራስ

*…. አፋኝና ታፋኙ


የፍትሕ መፅሔት ባለቤትና ማኔጂንግ ኤዲተር እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ደሳለኝ ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ.ም. በአገዛዙ ፖሊሶች ታስሯል።

ተመስገን አድዋ ድልድይ አካባቢ በሚገኘው ቢሮው ውስጥ በሥራ ላይ እያለ ነው ራሳቸውን በደበቁ ሲቪል ለባሽ ፖሊሶች የተወሰደው ።

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ወደ የት እንደተወሰደ አልታወቀም።

ግፍ በቃ አፈና በቃ…!!!

አብይ አህመድና ጓዶቻቸው በጀመሩት አፈና ቀጥለዋል ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝም ዛሬ ተራው ደርሶት ታፍኖዋል። ግልገል ጁንታው በተረኝነት እየሄደበት ያለው አክሳሪ የአፈና መንገድ የትም እንደማያደርሰው ይልቁኑ ውርደቱንም ውድቀቱንም እንደሚያፋጥን ብዙ ግልጽ ምልክቶች አሉ። ይልቅ አፈና በቃ ብሎ በጋራ መቆም ያስፈልጋል።

ትላንት ፍትህ ተጓደለ ብለው ሲጮሁ የነበሩ እነ ብር አምላኩ አፈናውን ለማስቀጠል አብረው ጠፍ እርግፍ ሲሉ

እየተስተዋለ ።

/

Filed in: Amharic