>
5:18 pm - Monday June 14, 5238

"በአብን ላይ የኦህዴድ ሴራና ደባ ብትንትኑ እየወጣ ነው ...!!!" (ግርማ ካሳ)

“በአብን ላይ የኦህዴድ ሴራና ደባ ብትንትኑ እየወጣ ነው …!!!”

ግርማ ካሳ


አቶ በለጠ ሞላ የአብን ሊቀመንበር፣ አቶ ጣሂር መሃመድ የአብን የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ፣  አብን እንደ ድርጅት ሳይፈቅድላቸው፣ እነ ዶር አብይ አህመድ ፣ ለይስሙላና ለማታለል፣ “ከተቃዋሚዎች ጋር አብረን እየሰራን ነው”  የሚለው ቅፈላቸውንና  ድራማቸውን ለመስራት ብለው፣ ተራ ፍርፋሪ ሹመት ሲሰጣቸው፣ ፣  እሺ ብለው በመቀበል የብልጽግና አፋኝ መንግስት ተባባሪ አካል ሆነዋል፡፡ በወቅቱ “ተው ይቅርባችሁ፣ ከሕዝብ ሊያጣሏችሁ ነው” ብለን መክረናቸዋል፡፡ አስጠንቅቀናቸዋል፡፡ በተለይም ደግሞ በለጠ ሞላ፣ ሲጀመር ፣ “የተሰጠህ ስልጣን ካንተ ጋር የሚሄድ አይደለም፣ አንተ ፍልስፍና፣ ስለ ፐሊቶ፣ አሪስቶተል፣ ካርል ማርክስ …ነው የተማረከው፣ ፣ ፊዚክስ፣ ኢንጂነሪን፣ ቴክኖሎጂ እውቀት ሳይኖርህ የሳይንሳን ቴክኖሊጂ ሚኒስቴር የመሆን ብቃት የለህም” ብለነው ነበር፡፡ ግን ሊሰማን ፍቃደኛ አልሆነም፡፡

ይሄን የነ በለጠ ሞላ  ውሳኒያቸው የአብን አባላት በመቃወም በጠቅላላ ጉብዬ ላይ ያሳወቁ ሲሆን፣ አዲስ አመራር እንዲመረጥ ጠይቀዋል፡፡ ሆኖም ፣ እነ በለጠ ሞላ የጠቅላላ ጉብዬውን ውሳኔ አንቀበልም በማለት ረግጠው የወጡበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው፡፡ ፡ ይሄንን የታዘበው ምርጫ ቦርድ አብን በአስቸኳይ እንደገና ጠቅላላ ጉብዬ ጠርቶ ነገሮችን እንዲያስተካክል አዟል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የብልጽግና መንግስት የአማራውን ማህበረስበ አንገት ለማስደፋት፣ ፋኖን ትጥቅ የማስፈታትና በማሀበረሰቡ አንቂና አክቲቪስት የተብሉ፣ ተደማሪ ተለጣፊ ያልሆኑትን የማሰደድ ፣ የማፈንና የማሰር አሳፋሪ እንቅስቃሴ ላይ ተጠምዷል፡፡ ከዚህ ጋር በተገናኘ  የወረድና የዞን ጽ/ቤት ሃላፊዎችን ጨምሮ፣ ከ126 በላይ የአብ አባላት  በብልጽግናዎች ታፍነው ተወስደዋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ኢትዮጵያዉን በሁሉም ማእዘናት ተቃውሟቸውን እያሰሙ ሲሆን፣ እንደ ፖለቲካ ድርጅት፣ ባልደራስ፣ መኢአድ፣ ህብር ኢትዮጵያና  እናት ፓርቲ ጠንካራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ እዚህ ጋር ልብ እንድትሉ የምፈልገው፣ በአማራው ማህበረሰብ ላይ እየደረሰ ያለውን አፈና በመቃወም፣ ድምጻቸውን በቀዳሚነት ያሰሙት፣  ሁሉም የዜግነት ፖለቲካ አራማጅ የሆኑ ድርጅቶች መሆናችውን ነው፡፡

ለአማራ ቆሚያለሁ የሚለው አብን፣ ሊቀመንበሩን ጨምሮ ጥቂት አመራሮች ስልጣን ስላገኙና በስልጣናቸው ተጠሪነታቸው ለኦህዴዶች በመሆኑ በግፊት  ቆየተው መግለጫ አውጥተዋል፡፡  ያወጡትም መግለጫ በነ ሺመልስ አብዲሳ ተጽፎ በነበለጠ ሞላ የጸደቀ  መግለጫ ነው የሚመስለው፡፡ እጅግ በጣም አሳዛኝና አሳፋሪ መግለጫ፡፡

ይህን የአብንን አባላት የማይወክል፣ አብንን የማይመጥን፣ በአብን ስም የወጣዉን የኦሮሙማ መግለጫ የምለውን፣  የአብን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሳይቀሩ እንደማያውቁትና እንደማይቀበሉት ነው የገለጹት፡፡ ዶር ቴዎድሮስ ኃይለማሪያም የአብን የጽ/ቤት ሃላፊ፣ አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ የአብን የመጀመሪያው ሊቀመንበር፣ ስልጣኑንን በሰለጠነ መልኩ አስረክቦ ያስክረበው፣ ስልጥን ለምን ልቀቅ ተባልኩ ብሎ ስብሰባ ረግጦ ያልወጣ፣  ዶር ደሳለኝ ጫኔ፣ የቀድሞ የአብን ምክትል ሊቀመንበር የነበረውና ባለፈው ጠቅላላ ጉብዬ፣ የአመራር ለውጥ ይደረግ ሲባል፣   በፍቃዱ ከሃላፊነቱ መልቀቁን ያሳወቀው የሱፍ ኢብራሄም መግለጫውን አጥብቀው ከተቃወሙ አመራሮች መካከል ይገኙበታል፡፡

በዚህ መልኩ የአብይ አህመድ ቅጥረኛ የሆኑና ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ በአብን ሃላፊነት ላይ የተቀመጡ እጅግ በጣም ጥቂት አመራሮች የሚፈጽሙትን ትልቅ አደርባይነት፣ የአብን አባላትና ደጋፊዎች ፣ ከፍተኛ አመራሮች ሁሉ ሳይቀሩ መቃወማቸው  አብን  በርግጥም ትልቅ ሕዝባዊ መሰረት ያለው፣ ጠንክራ ድርጅት መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡

ዶር አብይ አህመድ የአማራ ብልጽግናን ሲስተማቲክ በሆነ መንገድ ነው የበታተናቸውና ሙሉ ለሙሉ በርሱ የሚጋለቡ ትርፍ አንጀቶች እጅ ውስጥ እንዲወቅ ያደርገው፡፡  በአብን ውስጥ እነ በለጠ ሞላ በመያዝ አብንንም ለመቆጣጠር ፣ ለማምከን ያቀደው፣ ለትንሽ ጊዜ ተሳክቶለት የነበረ ቢሆንም፣ በአባላት ጥንካሬ እየከሸፈ ነው፡፡ በአብን ላይ የኦህዴዶች ሴራ ብትንትኑ እየወጣ ነው፡፡ በዚህ በከባድ ወቅት አብን ለእውነት፣ ለፍትህ፣ ፣ለሕዝብ የቆሙ ጠንካራ አመራሮችና አባላት እንዳሉት የታየበት ነው፡፡

Filed in: Amharic