>

ፖሊስ ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስን  "ህዝቡ መንግስት እንዲያምጽ አናሳስቷል!" ብሎ ከሰሰው...?!? (ኢትዮ ኢንሳይደር)

ፖሊስ ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስን  “ህዝቡ መንግስት እንዲያምጽ አናሳስቷል!” ብሎ ከሰሰው…?!?

ኢትዮኢንሳይደር

ፍ/ቤቱም የአስር ቀን ጊዜ ቀጠሮ አዘዘ

የጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስን ጉዳይ የያዙት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሁለት መርማሪዎች፤ “ተጠርጣሪው ሆን ብሎ ሁከት እና ብጥብጥ ለማነሳሳት ገንዘብ ተከፍሎት ሃይማኖት ከሃይማኖት እንዲጋጭ፣ በተለያዩ ዩቲዩብ ሚዲያ ንግግር በማድረግና በፌደራል መንግስት ላይ ህዝቡ እንዲያምጽ፣ ሆን ብሎ ሀገር እንዲረበሽ ህዝብ በመንግስት ላይ አመኔታ በማሳጣት፣ ሁከት እንዲፈጠር፣ ሀገር እንዳይረጋጋ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ነበር” ሲሉ ለችሎቱ የተጠረጠረበትን ወንጀል ዝርዝር አስረድተዋል።

መርማሪዎቹ ጋዜጠኛው ወንጀሉን ፈጸመባቸው ያሏቸው “አሁን መግለጽ አስፈላጊ ያልሆኑ ብዙ የሚዲያ ተቋማት አሉ” ብለዋል። መርማሪዎች የሚዲያ ተቋማቱን “መግለጽ አስፈላጊ አይደለም” ቢሉም ያየሰው አዘጋጅ የነበረበትን “ኢትዮ ፎረም” የተሰኘውን የዩቲዩብ መገናኛ ብዙኃን ግን በስም ጠቅሰዋል።

በሀገሪቱ ላይ “የሚዲያ እና የኢኮኖሚ ጦርነት” ታውጇል ያሉት መርማሪ ፖሊሶች “የሚዲያ ጦርነቱን ይመራል ብለን የምናስበው ተጠርጣሪው ነው” ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል። ከመርማሪዎቹ ውስጥ አንዱ “የሚዲያ ጦርነቱን የሚመራ የተደራጀ ስውር ቡድን አለ። በስውር የተደራጀው ኃይል ይኼ ተጠርጣሪ ያለበት ኃይል ነው” ሲሉ አክለዋል።

በጽህፈት ቤት በኩል የተካሄደውን የዛሬውን የችሎት ውሎ በአካል ተገኝቶ የተከታተለው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ፤ ለዳኞች ባቀረበው ገለጻ በትላንትናው ዕለት መኖሪያ ቤቱ መበርበሩን ተናግሯል። “ቤቴን በርብረው ያገኙት ነገር በ2008 ዓ.ም. በስሜ የተጻፈ መጽሐፍ ብቻ ነው። በእኔ ላይ ምንም ያገኙት ነገር የለም” ሲል ገልጿል።

ዝርዝር የችሎት ውሎ ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2022/6946/

Filed in: Amharic