ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም እያሽከረከረ የነበረ ሹፌር ከእነ መኪናው በኦነግ/ ሸኔ ተቃጥሎ ተገደለ !!
ባልደራስ
ትናንት ሰኞ ማታ፤ ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም. ለዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 23 አጥቢያ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ጎጃም እያሽከረከረ የነበረ ሹፌር፣ ከእነ ኤፌ ኤስ አር መኪናው ጎሃ ፅዮን ከተማ ሊደርስ ጥቂት ኪሎ ሜትር ያህል ሲቀረው በፅንፈኛው ኦነግ-ሸኔ ታቃጥሎ ተገድሏል።
ረዳቱ በከፍተኛ ደረጃ ቆስሎ ታግቶ የቆየ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት ወደ ህክምና መወሰዱንም የአካባቢው የመረጃ ምንጮች አረጋግጠዋል። ተሽከርካሪው “አማራ” የሚል ታርጋ እንደነበረውም ተረጋግጧል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በዚያው በጎሃ ፅዮን ከተማ የኦሮሞ ፅንፈኛ አሸባሪዎቹ አንድ የ12 ዓመት አማራ ሕፃን ልጅን አግተው ወስደዋል።
ሽብርተኞቹ በአካባቢው አንዳንዳንድ የአገዛዙ ባለሥልጣናት እንደሚደገፉም ምንጮች ጠቁመዋል።