>

ፋኖ ዘመነ ካሴን ለመውጋት ወደ መርዓዊ የዘመተው የአገዛዙ ጥምር ሰራዊት ከሁለት ተከፈለ ...!!! (ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው)

ፋኖ ዘመነ ካሴን ለመውጋት ወደ መርዓዊ የዘመተው የአገዛዙ ጥምር ሰራዊት ከሁለት ተከፈለ …!!!

ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው


የአማራ ሕዝባዊ ሃይል (ፋኖ) ሰብሳቢ የሆነው አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴን ለመውጋት ወደ ምዕራብ ጎጃም፤ መርዓዊና አካባቢው የዘመተው የአገዛዙ ጥምር ጦር እስርስ በእርሱጠ ባለመግባባት እየተጨቃጨቀ መሆኑን የውስጥ ምንጮች አረጋግጠዋል። ጥምር ሰራዊቱ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ከአድማ ብተና ፖሊስ እና ከአማራ ልዩ ሃይል የተውጣጣ ሲሆን “ልዩ ሃይሉ ለፋኖ ይወግናል” የሚል ቅሬታ በመቅረቡ ነው መከፋፈል የተፈጠረው። ከአማራ ልዩ ሃይል ውጭ ያሉት የአፋኝ ሰራዊቱ አባላት በአብዛኛው ኦሮሞዎች ሲሆኑ፤ ልዩ ሃይሉን ወቃሾችም እነርሱ ናቸው።

“ፋኖ ናችሁ” በሚል የተፈረጁት የአማራ ልዩ ሃይል አባላት ሊታሰሩ እንደሚችሉም በኦሮምኛ ተናጋሪ የጥምር ሰራዊቱ አዛዦች ተዝቶባቸዋል። የልዩ ሃይል አባላት በበኩላቸው እጃቸው ውስጥ የእስር ካቴና ሲጠልቅ ዝም ብለው እንደማያዩ አስጠንቅቀዋል።

በዚህም ምክንያት ከሁለት የተከፈለው የኦሕዴድ-ብልፅግና አፋኝ ጥምራዊት በሰሜን ሜጫ ከመርዓዊ በ5 ኪሎ ሜትር ርቀት ገደማ ላይ እርስ በእርሱ ሲጨቃጨቅ ውሏል።

ፋኖ ዘመነ ካሴን ለማፈን የመጣው ቡድን ከይልማና ዴንሳ ወረዳ፤ አዴት እስከ ሰሜን ሜጫ ወረዳ፤ ብራቃት ድረስ  መንገድ ዘግቶ ውሏል። በአካባቢው ነበሪዎች ላይም ከፍተኛ ወከባ እያደረሰ ይገኛል። በተለይም ለሰኔ ዘር የተዘጋጀው አርሶ አደር ከአመቱ ዋነኛ ሥራው እየተስተጓጎለ ነው።

Filed in: Amharic