>
5:13 pm - Wednesday April 18, 2694

ጠ/ሚ አብይ አሕመድ ከሕወሓት አመራሮች ጋር በናይጄሪያ መገናኘታቸው ተሰምቷል...!!! (እናድን ኢትዮጵያን)

ጠ/ሚ አብይ አሕመድ ከሕወሓት አመራሮች ጋር በናይጄሪያ መገናኘታቸው ተሰምቷል…!!!

እናድን ኢትዮጵያን


*… የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጥምረት መፍረሱንም ለሕወሓቶች ጠቅላይ ሚኒስትሩ አምነዋል…!!!

ፓርላማው በሃገር ጉዳይ ላይ ውሳኔ እንዳይሰጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማነቆ ሆነዋል። ከሕወሓት ጋር የሚደረገውን ድርድር በተመለከተ አንድም መረጃ ፓርላማው የለውም።  በጦርነትም በሰላምም ወቅት በድርድርም ይሁን በሜጋ ፕሮጀክቶች ጉዳይ ላይ ፓርላማው ያለውን ስልታን እንዳይተቀም ጠቅላዩ ጋሬጣ መሆናቸው የሃገሪቱ የበላይ አካል የሆነውን ፓርላማ ጥርስ አልባ አድርገውታል።

የሕወሓት አመራሮች ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ሚስጥራዊ ውይይት ማድረጋቸውን ይፋ አድርገዋል። የሕወሓት አመራሮች ወደ ናይጄሪያ አቅንተው ከኬንያ ውይይት ቀጣይ ያሉትን አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በናይጄሪያ የትግራይ ዲያስፖራ አባላትንም መገናኘታቸው ታውቋል።። አብይ የተነጋገሩትን እና የተስማሙበትን ነገርበዝርዝር ለመግለፅ ፈቃደና አልሆኑም። ቢሆንም በውይይቱ በአብዛኛው ጉዳዮች መስማማታቸው ታውቋል።

በኬንያው ድርድር የትግራይ ባለሃብቶች ንብረታቸው እንዲመለስ የባንክ አካውንታቸው እንዲከፈት ብድር እንዲመቻችላቸው ገንዘባቸውን ከሃገር እንዲያወጡ በሚሉ ጉዳዮች ከስምምነት ተደርሶ ወደ ተግባር መለወጡን ባለፈው ሳምንት ያየነው ጉዳይ ነው። እንዲሁም ብሄራዊ ባንክ ከፍተኛ መተን ያለው የወረቀት ገንዘብ ወደ ትግራይ መላኩንም ሰምተናል።

ከሕወሓቶች የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንዳችን ከሌላው ስምምነት የለንም። ሁሉም ሰው ችግር ውስጥ ነው። የኤርትራና የኢትዮጵያ ጥምረት ፈርሷል። አማር ክልል የከፈትነውን የሕግ ማስከበር እንዳጠናቀቅን አዳዲስ ስምምነቶች እንደሚኖሩን ቃል እገባለሁ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሕወሓት ጋር መስማማታቸው ኤርትራ እና አማራ ፖለቲከኞችን አላስደሰተም። ብልፅግና በአማራ ክልል የከፈተው ዘመቻ እና ሕወሓት በኤርትራ ላይ የከፈተው ጥቃት የስምምነቱ አካል መሆኑም ተጠቁሟል። ስምምነቱ ለማሳካት ስምምነቱን የሚቃወሙ ኃይሎችን ማዳከም ።

Filed in: Amharic