>

ጋይንት እስር ቤት የሚገኙ ወጣቶች " ወይ አልተከሰስን ወይ አልተለቀቅን ለምን ታግቱናላችሁ" በሚል ተቃውሞ አሰሙ...!!! (ምኒልክ ሳልሳዊ)

ጋይንት እስር ቤት የሚገኙ ወጣቶች ” ወይ አልተከሰስን ወይ አልተለቀቅን ለምን ታግቱናላችሁ” በሚል ተቃውሞ አሰሙ…!!!

ምኒልክ ሳልሳዊ


*…. ጋይንት ማረሚያ ቤቱ ከተቀበለው የታጋች ብዛት አንፃር በቂ ምግብም ሆነ ውሀ የለውም…!!!

– ማረሚያ ቤቱ ከአቅሙ በላይ ሰው ያግቶበታል፤ በዚህም ምክንያት ሁሉ ነገሩ ተጨናንቋል።

– የታገቱ ወገኖቻችን አልተከሰስን ወይ አልተለቀቅን ለምን ታግቱናላችሁ በሚል እሁድ ግንቦት 21/2014 ከፌደራል ፖሊሶች ጋር ግጭት ተፈጥሮ ነበር፤ ግጭቱም ሆነ የደረሰው ጉዳት አልታወቀም፤ ታፍኗል።

– ማረሚያ ቤቱን የፌደራል ፖሊስ ተረክቦታል። የተመደቡ የፌደራል ፖሊሶችም አማርኛ የማይችሉ ኦሮሞዎች ናቸው።

– መጠየቅም ሆነ ገንዘብ፣ አልባሳትና ምግብን ጨምሮ እንዳይገባ ከልክለዋል። በጃፖኒ ብቻ የገባ ታጋች ጭምር ልብስ እንዳይገባለት ተከልክሎ ራቁቱን ይገኛል። ከእሩቅ ሀገር ልብስ ይዛለት የሄደች ባለቤቱ በፌደራል ፖሊሶቹ እንግርግሪያ በጭንቀት እየወደቀች እየተነሳች ስትጮኽ እንደነበርና ራሷን መሳቷን የአይን እማኞች ገልፀዋል።

– ማረሚያ ቤቱ ከተቀበለው ታጋች ብዛት አንፃር ምግብም ሆነ የመጠጥ ውሀ የለውም። ካፌውም ምግብ ገዝቶ ለመጠቀም ሊበቃ አልቻለም። ገንዘብ እንደማይገባ ከላይ ተገልጿል። ውሀም ተከልክሏል።

በዚህ ውስጥ እየታመሙ ያሉ ታጋቾች ህክምና የማግኘት ዕድልም ተከልክለዋል።

የተወሰኑ ታጋቾች በተለይም ወታደራዊ ልምድ ያላቸው ከ8-ባስ በላይ ከማረሚያ ቤቱ ወደ ሌላ ቦታ የተወሰዱ ቢሆንም የት እንደተወሰዱ አልታወቀም። ወልቃይት አከባቢ አዲስ ማገቻ ቦታ (ምናልባት የወያኔው ባዶ-6 ሊሆን ይችላል) እንደተወሰዱ ጭምጭምታ ቢኖርም ቤተሰቦቻቸውም ማወቅ አልቻሉም።

የማረሚያ ቤቱ አመራር የሆኑ የአማራ ፖሊስ ማረሚያ ቤት ፖሊሶች ከስራ ታግደዋል።

የፌደራል ፖሊሶቹ ንፋስ መውጫ ከተማዋን ጭምር እየዞሩ ወጣቶች ጋር “ለምን አየህኝ” በሚል ትዕቢት ጭምር እየተጋጩ ወጣቶችን እየደበደቡ እያሰሯቸው ነው። ከህገወጥ እንቅስቃሴያቸው አንፃር ከተማዋን ራሱ እስር ቤት እያደረጓት ነው።

ህዝቡንም እየሰበሰቡ የመንግስት የአፈና እርምጃ ትክክል ነው በሚል ማስፈራሪያ እያስጨበጨቡ ለማሳመን እየሰሩ ነው።

የነቃውንና ብልጽግናን የሚቃወመውን የአማራ ትውልድ በእንዝላልነት እንዳናስበላው በጊዜ መንቃትና መታገል አለብን።

ነፋስ መውጫን ጨምሮ ታጋቾች የታገቱባቸው ማረሚያ ቤቶች ሁሉ በአስቸኳይ የአገር በቀልም ሆነ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ፍተሻ ያስፈልጋቸዋል።

Filed in: Amharic