>

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በማረሚያ ቤት ፓሊሶች ድብደባ ተፈጸመበት...!!! ተደበደበ!!  (በታሪኩ ደሳለኝ)

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በማረሚያ ቤት ፓሊሶች ድብደባ  ተደበደበ!!

 በታሪኩ ደሳለኝ (የተመስገን ወንድም)


ዛሬ ግንቦት 25/2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ፖሊስ በተለምዶ 3ተኛ ተመስገንን ለመጠየቅ ፖሊስ ጣቢያ ተገኝቼ ነበር::

በዚህ እስር ቤት በታሳሪና በጠያቂ መካከል በሁለት ሾቦ የተጋረደ ከ10 ሜትር የሚበልጥ ርቀት አለ::

በታሳሪና በጣያቂ መካከል ባለው ርቀት የተነሳ፣ ንግግር ለማድረግ እጅግ አዳጋች ነው። አጠቃላይ ነገሩ መጯጯህ ነው:: ተመስገን ከዚህ በፊት በእስር ቤት እያለ ባጋጠመው በጆሮ ህምም ምክኒያት በዚህ ግር ግር ውስጥ ጆሮው ለመስማት ያዳግተዋል::

ይሄ በመሆኑ ተመስገን ለፖሊሶቹ “ትንሽ ቀረብ ብሎ ቢያወራኝ ” ሲለው ፖሊሱ በእጁ የማመናጨቅ ምልክት አሳየው፣ ተመስገንም ድጋሜ ለማስረዳት ሲሞክር አንዱ ፖሊስ ከነበረበት ከጠያቂ ቦታ ሌላው ፓሊስ ከስረኛቹ መቆሚያ ደረጃ ላይ በመውረድ ለሁለት ተመስገንን አብረውት ከቆሙት እስረኞች መካከል ጎትተው በማውጣት በቦክስ፣ በጫማ ጥፊ ለሁለት ደብድበውታል።

ይህ ሲሆን የሌሎች እስረኛ ጠያቂ ቤተሰቦችና እስረኞችም አይተዋል። ድብደባውን እየፈፀሙ ወደ እስረኛ ክፍል ሳይሆን ወደ ሌላ ቦታ ይዘውት ሄደዋል::

ከቆይታ በኃላ በቢሮ ውስጥ ተመስገንን ስናገኘው፣ የግራ ዓይኑ ስር አብጦ የለበሰው ቲ-ሸርት ተቀዶ አግኝተነዋል::

አሁን ከእስር ቤቱ አስወጥተውኝ በሩ ላይ እገኛለሁ::

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ሚዲያዎች ጉዳዮን እንድታውቁልን፣ ማጣራት አድርጋችሁ ለሕዝብና ለሚመለከተው አካል እንድታደርሱልን።

 

Filed in: Amharic