>

በአቃቂ አካባቢ የአዲስ አበባ ኗሪዎች በግዳጅ ወደ ኦሮሞ ክልል እየተጠቃለሉ ናቸው!! (ባልደራስ)

በአቃቂ አካባቢ የአዲስ አበባ ኗሪዎች በግዳጅ ወደ ኦሮሞ ክልል እየተጠቃለሉ ናቸው!!

ባልደራስ

*…. ኗሪዎቹ የአዲስ አበባ መታወቂያ እንዲመልሱ ታዘዋል!!


በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፤ በተለምዶ አቃቂ ኬላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩ አዲስ አበቤዎችን፣ ያለ ኗሪዎቹ ፍቃድ በኦሮሞ ክልል ስር ወዳለው ገላን ከተማ አስተዳድር መዋቅር ውስጥ እንዲገቡ መደረጉን ተናገሩ።

በገላን ከተማ በተጠራው ስብሰባ ላይ ተገደው የተገኙ አዲስ አበቤዎች፣ የአዲስ አበባ የኗሪነት መታወቂያቸውን እንዲመልሱና የኦሮሞ መስተዳድር የነዋሪነት መታወቂያ እንዲወስዱ መታዘዛቸውን ተናግረዋል።

አቃቂ ኬላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በኦሮሞ መስተዳድር ስር የሚተዳደር የቀበሌ መሥሪያ ቤት እየተዘጋጀ ነው።

አዲስ አበቤዎች ያለ ፈቃዳቸው ወደ ኦሮሞ መስተዳድር ከመወሰዳቸውም በላይ፣ ወደ ፊት በማያውቁት ቋንቋ አስተዳድራዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት እንደሚቸገሩም ገልፀዋል።

Filed in: Amharic