ለፋኖ እስረኞች ቦታ እንዲለቁ የህወሀት እስረኞች በፖለቲካዊ ውሳኔ እየተፈቱ ነው…!!!
ግርማ ካሳ
*…. ሌተና ኮሎኔል ሰጠኝ ካሳዬ: ሌተና ኮሎኖል ፍፁም አብርሃም: ሻለቃ ዋልታንጉስ ተስፋውና ሻለቃ ክንድያ ግርማይ ጨምሮ በርካቶች ከሜቴክ ጋር እንዲሁም ከህወህት ጋር ከተደረገው ጦርነት ጋር በተገናኘ ታስረው የነበሩ እንዲፈቱ ትእዛዝ ከአራት ኪሎ ተሰጥቷል:::
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ፍርድ ቤት ለይስሙላ አለ ይባላል እንጂ ፍርድ ቤቱ በኦህዴድ ፕለቲከኛ ሹመኞች የተሞላ አብዛኞቹ ዳኞች የኦህዴድ “አባላት” እንደሆኑ ይታወቃል::
ስለዚህ አብይ አሀመድ ፍቱ ሲል ይፈታሉ : አትፍቱ ሲል አይፈቱም::
ምን አልባትም ደግሞ አሁን ተራው ፋኖዎች የአማራ አክቲቪስቶችን ማሰር ስለሆነ እስር ቤቶች ስለሞሉ ቦታ ለማስለቀቅ ይሆናል::
ማንም ያለ ወንጀሉ መታሰር የለበትም:: የታሰረ በቶሎ ጉዳዩ ታይቶ ወንጀል እንዳለበት ካልተረጋገጠ መለቀቅ አለበት:: በፍርድ ቤት::ቀደም ሲል የትግራይ ወገኖች በጅምላ ሲታፈኑ ስቃወም የነበርኩ ሰው ነኝ::
አሁን እስረኞች የተፈቱት በፍርድ ቤት አይደለም: በፖለቲካ ውሳኔ ነው:: ነገ አብይ አህምድ መልሶ ሊያስራቸው ይችላል::