>

የሁለት ንጉሶች ወግ - ስለጅማና አካባቢው...!!! (ገለታ ጋሞ)

የሁለት ንጉሶች ወግ – ስለጅማና አካባቢው…!!!

ገለታ ጋሞ


“…. የሙት መንፈስ የሚያሸብራቸው ግኡዛን ኦህዴዶ ች በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል መሬት አስቆፍረው በሚልዮኖች ልብ ላይ የታተመውን የእምዬን ስም ያስጠፋሉ።

እምዬ ምኒልክ ስምህም ግብርህም ስራህም ህያው ነው!!!

የእናሪያ ንጉስ ዘውድ ተረክቦ ከኦሮሞ አባገዳዎችና አባጅፋር ቤተሰቦች ጋር ተመሳጥሮ (አባ ጅፋር ኦሮሞ እንኳን አይደለም) የገዛ ህዝቡን ባሪያ እያደረገ እየሸጠ፣ ቋንቋቸው ባህላቸው ጠፍቶ እናሪያዎች  ስማቸው እንኳን ዛሬ የሚታወቀው ዳውሮና ከፋ የሸሹት ናቸው።

የየም (ጃንጀሮ) ንጉሶች ለ150 ዓመታት ከአባገዳዎች ጋር ተፋልመው፣ ህዝባቸው ተመናምኖ፣ መሬታቸው አብዛኛው ተቀምቶ በመጬረሻው ሰዓት ምኒሊክ ከመጥፋት በመታደጉ ይኸው ዛሬ ትልቅ አገር የነበሩት ቢያንስ አንድ ወረዳ ሆነው ይኖራሉ።

ያንን ያደረገው ምኒሊክ ስሙ ከግድግዳና ከወለል ላይ ሳይቀር ሲፋቅ ባሪያ በፈነገለበት፣ ዘር ባጠፋበት አባጅፋር አውሮፕላን ማረፊያ ይሰየምለታል።

እወነት ሁሌም ተደብቆ አይቀርም።

እንደ ችግኝ የሰውን ልጅ ከገዛ አገሩ እየነቀሉ ይሸጡ ስለነበሩት የጋሞ፣ የወላይታና የዳውሮ ባላባቶች ተናገር።

Intellectual integrity ካለህ 2/3ኛውን የገዛ ህዝቡን ባሪያ ስላደረገው የከፋ ንጉስ አጥናና ጻፍ። ከኦሮሞ አባገዳዎች ጋር ተመሳጥሮ የገዛ ህዝቡን በነቂስ ባሪያ አድርጎ ያሸጠው፣ ባህሉን፣ ቋንቋውን ስላስጠፋው የእናሪያ ንጉስ አጥናና ጻፍ።

እስቲ ወኔው ካለህ፣ 29 ብሔሮችን ከምድር ስላጠፉት፣ የጋሞን ህዝብ ከመሬቱ አባረው ተራራ ሳላስወጡት (ዛሬም እያደርጉ ናቸው)፣ በህይወት እንዲኖርና እንዲያገለግልላቸው የፈቀዱለትን ህዝብ አባት እናቱን እንዳያስታውስ አድርገው ስሙን ብቻ አይሆን የአባቱን ስሙን፣ ቋንቋና ባህሉን አስቀይረው ገርባ ስላደረጉትና፣ ዛሬም በገዛ ወንድሙና እህቱ ላይ አያዘመቱ ስላለሉት የኦሮሞ አባገዳዎችና ልጆቻቸው ጻፍ። እወነተኛ ከሆንክ።

መቼም መሪ ሆኖ በግዛቱና በስሙ ጥፋት ያልተሰራ የለም።

ግን በየትኛውም መመዘኛ በወቅቱም ሆነ ዛሬ ካሉት መሪዎች ምኒሊክ በማይስተካከል ሁኔታ የተሻለ እነደነበረ በተጨባጭ መረጃ ማሳየት ይቻላል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝብ በመሬቱ የሚኖረው፣ ቋንቋን የሚናገረው፣ ባህሉን ጠብቆ የሚኖረው በምኒሊክ ምክንያት ነው። ኤክስፖርት ይሆን ነበር።

ይህ ብቻ አይደለም፣ መላው የ ዓለም ጥቁር ህዝብ ዛሬ ከሰው እኩል መቆጠር የቻለው በምኒሊክ ምክንያት ነው።

ምኒሊክ ባይኖር ብዙዎቻችሁ በምታመልኳቸው ነጮች ዛሬም ከቤት እንስሣ ባልተለየ መልኩ ጥቁር ህዝብ ይኖር ነበር።

Filed in: Amharic