>

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች  ከኢትዮጵያ ፖለቲካ እንዴት ሊገለሉ ቻሉ? ሸንቁጥ አየለ

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች  ከኢትዮጵያ ፖለቲካ እንዴት ሊገለሉ ቻሉ?

ሸንቁጥ አየለ


–ምናምንቴዎች እና ከሃዲዎች ላለፉት 50 እና 60 አመታት  ክርስቲያን ፖለቲካ እና ሀገር ጉዳይ ዉስጥ አያገባዉም የሚል ሰፊ የፕሮፖጋንዳ ስራ ሰርተዋል

-ኢ አማኞቹ የሶሻሊስት እምነት ተከታይ ፖለቲከኞች ክርስትናን ቅስሙን ለመስበር እና ከፖለቲካ ለማስወጣት ብዙ ሰርተዋል

– ህዉሃት ኢትዮጵያን ለማጥፋት ተዋህዶን ማክሰም ባለዉ ስትራቴጂው ቤተክርስቲያኗም ላይ ተከታዩዋም ላይ ዘርፈ ብዙ ጥቃት እና የማግለል ስራ ተሰርቶባታል

-ኦነግ/ኦህዴድ ተዋህዶን መንቀል በሚለዉ ፖሊሲዉ ተዋህዶን እና አምኟን ከሁሉም ነገር ማግለል ብቻ ሳይሆን ቤተክርስቲያንን ከማቃጠል   ዘሎም ክርስቲያኑን ሰፊ ጭፍጨፋ እያደረገበት ነዉ

-እሥስቱ ብአዴን አንዴ ከህዉሃት ሌላ ጊዜ ከኦህዴድ እየወገነ ክርስትናን በማጥፋት እና ክርስቲያኖችን በማግለል ቁልፍ ሚና ተጫዉቷል

-በዚህ ሁሉ መከራ ዉስጥ ያለፈዉ ክርስቲያን ሀገራዊ እጣፈንታዉን እና የኢትዮጵያን ጉዳይ ለምናምንቴዎች አሳልፎ ሰጥቶ እሁንም ስለራሴ እጣ ፋንታ እያገባኝም ብሎ ለሽ ብሏል፥፥

-በዚህም ክርስቶስ ኢየሱስን የሚጠሉ ጎሰኛ ፖለቲከኞች ጥባጥቤ የሚጫወቱበት፥ በጎሳ ከሱ ወገ  ስለሆኑ ብቻ ና ሲሉት የሚሮጥ ሀገር አፍርስ ሲሉት ሀገር የሚያፈርስ ፥ ሄደህ ከሌላዉ ጎሳ ጋር ተጨፋጨፍ ሲሉት እንደ እንሰሳት የታዘዘዉን የሚያደርጎ ሆኗል

ልብ ላለህ ጥሪ

-ልብ ያለህ የኢሱስ ክርስቶስ ልጅ ንቃ፥፥ ኢትዮጵያን በመድሃኒዓለም ሀይል ተመርተህ የምታድናት አንተ ነህ፥፥ የጎሰኝነትን ስሩን የምትነቅልላት ፥ የኢትዮጵያን ህዝብ አንድነት የምትመልስለት አንተ ነህና ተገፍተህ እዳር ቆመህ አታስተዉል፥፥

ህዝብህን ለማዳን ተነሳ፥፥ነጠላ ለብሰህ ቤተክርስቲያን መሄድህ እይደለም ክርስቲያን የሚያሰኝህ፥፥ ክርስቲያን የሚያሰኝህ ለህዝብህ የምትከፍለዉ  የህዝብ የፍቅር ዋጋ እንጂ፥፥

ኢትዮጵያን እግዚእብሄር ይባርካት

Filed in: Amharic