>
5:18 pm - Sunday June 15, 2797

እኔም የሕዝብ ትግል እቀላቀላለሁ - እኔ ፋኖ ነኝ...!!! (ግርማ ካሳ)

እኔም የሕዝብ ትግል እቀላቀላለሁ – እኔ ፋኖ ነኝ…!!!

ግርማ ካሳ


ይህ በጣም የሚጮኹ የአብይ አህመድ ጉጅሌዎች፣ ብልጽግናዎች፣ ተደማሪ ተለጣፊዎች፣ ኦነጎችና ህወሃቶችና እንዲሁም ደጋፊዎቸውን አይመለከትም፡፡ ከነዚህ ውጭ ላላችሁ ወገኖች

እኔም ፋኖ ነኝ – ፩

የሚል ጦማራችሁ ላይ እንድታካተቱ እጠይቃለሁ፡፡ የተጀመረውን እኔም ፋኖ ነኝ እንቅስቃሴ በያላችሁበት እንድትቀላቀሉ አበረታታለሁ፡፡ በአካባቢያችሁ ከሌላም እናንተው ይሄን እንቅስቃሴ ጀመሩት፡፡

ፋኖ፡

1ኛ  ህዝባዊ ኃይል ነው፡፡

2ኛ አገርን ለመከላከል የቆመ ነው፡፡

3ኛ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የማይደራደር ነው፡፡

4ኛ የዘር ፖለቲካን የሚቃወም ነው፡፡

5ኛ አገር  በሕወሃት እጅ እንዳትወድቅ ዋጋ የከፈለ፣ አሁን ባለው ከህውሀሃት በባሰው በኦህዱድ/ኦነግ  የተጀመረው አገርን የማጥፋት እንቅስቃሴ እንዲገታ ለማድረግ የተዘጋጀ ነው፡፡

ህወሃቶች፣ ኦነጎች፣ ኦህዴዶች፣ ኦፌኮዎች  … በአብዛኛው አገር አጥፊና ጨፍላቂ የጎሳ ፖለቲካ እንዲቀጥል የሚፈልጉ፣  ጥርሳቸውን ነክሰው በፋኖ ላይ መነሳታቸውን፣ ፋኖን ሌት ተቀን እያወገዙ መሆናቸውን፣ ኦህዴዶችማ  ከማውገዝ አልፈው በፋኖ ላይ ጦርነት ማወጃቸውን  በማየት ብቻ ፋኖ በርግጥም የሕዝብ ጠበቃ መሆኑን ለመደምደም አስቸጋሪ አይሆንም፡፡

እኔም ፋኖ ነኝ – ፪

እኔም ፋኖ ነኝ በሚል በተለያዩ የአለም ግዛቶች ሰላማዊ ሰልፎች ይደረጋሉ፡፡ እየተደረጉም ነው፡፡ በቴል አቪቭ ደማቅ ሰልፍ ነበር፡፡ በዋሺንግተን ዲሲ  ፣ በስዊዘርላንድ  በመሳሰሉት ይኖራል፡፡

ከአራት አመት በፊት የአብይ መንግስት 90%  የዳያስፖራው ድጋፍ ነበረው ማለት ይቻል ነበር፡፡ ከሁለት አመት በፊት  ወደ  60% ወረደ፡ ከአንድ አመት በፊት ወደ 40%፡፡ አሁን ከ10% በታች የሂነ ነው የሚመስለው፡፡ እንደውም በወያኔ ጊዜ ከነበረው ተቃውሞ ይልቅ አሁን በተረናውና አባገዳዊው ኦህዴድ አገዛዝ ላይ ያለው ተቃውሞ እጅግ በጣም እየጨመረ ነው፡፡

እኔም ፋኖ ነኝ – ፫

የአብይ መንግስት : ምን ወንጀል እንደሰሩ ባላውቅም ፋኖዎች ላይ ጦርነት ከፍቷል:: ነጥሎ ተራ በተራ ለመምታትም የተወሰኑ የፋኖ መሪዎችን ለጊዜው ዝም ብሎ አንዳንዶቹን ሸላልሞ የተወሰኑት ላይ  ነው ያነጣጠረው:: በዋናነት ትኩረቱን ያደረገው የጎጃም ፋኖዎች ላይ ነው:: በተለይም አነ ዘመነ ካሴ : ማስረሻ ሰጤ ላይ::

በምስራቅ ጎጃም በመርጦ ለማሪያም በምእራብ  ጎጃም ደግሞ በመራዊ አካባቢ  በጀነራሎች  ሳየቀር የተመሩ በርካታ የኮማንዶ ኦፐሬሽኖች ተደርገዋል:: በርካታ:: ሆኖ የአብይ ትጣቂዎች ሞተዋል:: እነ አብይእስከ አሁን እልቻሉም:: አዳንዶች  ደግሞ ፋኖዎችንም እየተቀላቀሉ ነው::

አሁን ለነ እብይ አህመድ እንጥፍጣፊ ማስተዋል ካላቸው አፋኝ ቡድናቸውን ከአማራ ክልል ያስወጡ:: ይፈኗቸውን ይፍቱ::

እኔም ፋኖ ነኝ – ፬

ይች የአብይ አህመድና ኦህዴድ ስትራቴጂ ናት፡፡ አዲስ ስትራቲጂ አይደለችም፡፡ ከፋፍሎ፣ ለያይቶ፣ አጣልቶ መምታት የተለመደች አሰራር ናት፡፡

ወልቃይትን ለመውረረ የመንግስት እና ብአዴን ፕላን

1. ቅድሚያ የጎጃም ፋኖን ማሰር ማሳደድ እና መግደል

2. የጎንደርን ፋኖ ለጎጃም ወንድሙ እንዳደርስ መዝጋት

3. ጎጃም በጎንደር ቂም ይዞ ለወልቃይት እንዳይዋጋ ማድረግ

4. አፈናውን በአክቲቪስቶቻቸው አማካኝነት የጎንደር እና ጎጃም ጦርነት በማስመሰል ልዩነትን ማስፋት

5. የወሎን ፋኖ በራያ ጦርነት ከፍቶ ማስመታት

6. የሸዋን ፋኖ በኦነግ ማስመታት

7. ወልቃይትን  የጎንደር አማራ ጦርነት ብቻ በማድረግ የጎንደር አማራ ፋኖን በመከላከያ በህውሀት በሱዳን በቅማንት ኮሚቴ በመሳሰሉት  በአንዴ አዋክቦ ከቦ ለመደምሰስ እና ወልቃይትን ለመውሰድ

ንቃ አማራ ከጥላቶችህ ሴራ ቅደም

አንድ አማራ!

አንድ ፋኖ!

እናሸንፋለን

Filed in: Amharic