ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ይዛ ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል ስትጓዝ የነበረችው መኪና ከመንገድ እንድትመለስ ታዘዘ…!!!
ሀብታሙ አያሌው
ዐብይ አህመድ ፋሽሽት ነው ስንል በምክንያት ነው !!
*****
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (ተሜ) ወደ ሆስፒታል እየሄደ ሳለ ህክምና እንዳያገኝ ከመንገድ እንዲመለስ ትዕዛዝ በመስጠት ጭምር ፋሽሽቶቹ በማንአለብኝነት ቀጥለዋል። በድብደባ የተጎዳው የጎን አጥንቱ ህመም እረፍት ስለነሳው ህክምና ያግኝ ተብሎ በሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ሐኪም የተሰጠው ትዕዛዝ በፖለቲካ ውሳኔ እንዲታገድ አድርገዋል። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ይዛ ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል ስትጓዝ የነበረችው መኪና ከመንገድ እንድትመለስ ከበላይ አካል ትዕዛዝ ተሰጠ… መኪናዋ በህህመም የሚሰቃየውን ጋዜጠኛ ይዛ ወደ ታፋኞች ማጎሪያ ጣቢያ ተመለሰች። አስደብድቦ ህክምና የሚከለክለው የበላይ አካል ማነው እያልክ በፍለጋ አትባዝን አትጠራጠር ፋሽሽቱ ዐብይ አህመድ እና ነውረኛው አባ ብላ ገመዳ ነው !!
የአብይ አህመድ ቡድን … ፋሽሽታዊው ኦህዴድ በቃህ ሊባል ይገባዋል !!