>

የብርሃኑ እና የአንዷለም ልዩነት የመርህ ነዉ ወይስ ግለሰባዊ? (ሸንቁጥ አየለ)

የብርሃኑ እና የአንዷለም ልዩነት የመርህ ነዉ ወይስ ግለሰባዊ?

ሸንቁጥ አየለ

—ሰሞኑን ብርሃኑ ነጋና እና አንዷለም  በፓርቲዉ ዉስጥ ልዩነት አለን እና የኢዜማ የወደፊት መሪ እኔ ነኝ ፥ እኔ ነኝ  የሚል ሙግት ይዘዋል፥፥

– ብርሃኑ ሚኒስቴር እንዲሆን በኢዜማ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ላይ  አንዷለም ደግፎ የቆመ ነዉ፥፥

–   አንዷለም ኢዜማ ስልጣን መጋራት አለበት፥  አቢይ አሻጋሪያችን ነዉ በሚለዉ አቋሙ ይታወቃል፥፥

–  አንዷለም በአማራ ህዝብ  እና በክርስቲያን ኢትዮጵያዉያን ላይ ኦነግ/ ኦህዴድ የፈጸሙት የዘር ማጥፋት ወንጀል የለም በሚለዉ አቋሙ ይታወቃል፥፥ እንደሚታወቀዉ ብርሃኑ ነጋ የተደረገዉን የዘር ፍጅት መካድ ብቻ ሳይሆን ኦነግ/ ኦህዴድ የዘር ፍጅት አደረገ አትበሉ እስከማለት የተራመደ ሰዉ ነዉ፥፥

-ኢዜማ ኢትዮጵያ የተፈጠረችዉ በቅኝ ግዛት የተፈጠረች ነች የሚለዉን አቋሙን አንዷለም ተቃዉሞ አያዉቅም፥፥ የዚህ ሀሳብ ዋና አቀንቃኞችም እነ ብርሃኑ ነጋ ኦነግ/ ኦህዴድን ለማስደሰት በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ እንደሚቀባጥሩ ይታወቃል፥፥

-አንዷለም የኦነግ/ኦህዴድ መሪዎችን እነ በቀለ ገርባን እንዲሁም ሌሎች የፖለቲካ ሰዎችን ሰብስቦ የኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሪዎችን አጼ ቴዎድሮስን እና አጼ ምኒሊክን ታሪክ ያንቋሸሸ ሰዉ ነዉ፥፥  ባደረገዉ ንግግርም የአጼ ምኒሊክ የአደዋ የድል ታሪክ  የተሟላ የድል ታሪክ አይደለም እንዲሁም አጼ ቴዎድሮስ በእንግሊዝ የተሸነፈ መሪ እና የሽንፈት ታሪክ ያለዉ ንጉስ ነዉ ሲል የጸረ ኢትዮጵያዊነት ጽንሰ ሃሳብ አራማጆችን ለማስደሰት በአባቶቻችን ነገስታት ላይ ክህደት የፈጸመ ሰዉ ነዉ፥፥ በዚህ ንግግሩም በመድረኩ ላይ ከተሳተፉ እዉነተኛ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ሀይሎች  በርካታ ተቃዉሞ የገጠመዉ ሰዉ ነዉ፥፥

Filed in: Amharic