>

የካፒቴን ማስረሻ ሰጤ እህት የሚፈጸምብንን ግፍ ህዝቡ ይስማልን አለች...!!! (ባልደራስ)

የካፒቴን ማስረሻ ሰጤ እህት የሚፈጸምብንን ግፍ ህዝቡ ይስማልን አለች…!!!

ባልደራስ


*…. ወንድሙን በመያዣነት ይዘው እያሰቃዩት ነው!!!

*…. 6 የማስረሻ ሰጤ ቤተሰቦች እየተሳደዱ እና ከፊሎቹ ደግሞ በእስር ቤት እየተሰቃዩ ነው!!

 የእኔና የቤተሰቤ ስቃይና መከራ ፦ ከወለድኩ 5 ወር ሆኖኛል የማህፀን ጥበት ተብየ የወለድኩት በኦፕሬሽን ነዉ እንደልቤ መንቀሳቀስ አልችልም መንግስት ከላከዉ አፋኝ ቡድን ጋር ድብብቆሽ ከጀመርን ሳምንትና ከዚያ በላይ ሆኖኛል አሁን ግን ድብብቆሹ መሮኛል እንደተናገርኩት እንደልቤ መሮጥ አልችልም ከቤተሰባችን እኔንና መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤን ጨምሮ 5 ቤተሰባችን ከእነሱ የእስርና እንግልት መነፅር ዉስጥ ነን አርሶ አደር ወንድማችን ዕሮብ ለት የታሰረ እየተሰቃየ ነዉ።

ከትላንት በፊት ታላቅ ወንድማችንን ለማየት እኔ መሄድ ስላልቻልኩ ሌላ ሰዉ ልኬ ነበር ያ ወንድማችንን ያየ ግለሰብ አይቶት ከመጣ በኋላ እኔጋ መጣና እግሩ በደንብ መራመድ እንደማይችል አይኑ በደንብ ማየት እንደማይችል ነገሩኝ  አልቻልኩም ከያዙ ይያዙኝ ብየ ታስሮ ወደተሰቃየበት ጊቢ ገባሁ ከዚያ አይኔን ማየት አልቻለም ማልቀስ ጀመረ ጥያቄ ጠየኩት ፦ ገረፉህ” አልኩት ያቀረቀልኝ ወታደር አንችንም እንዳንጨምርሽ አለኝ ግን የጥያቄ መአት ፈላ ?!

~~~ ወንድምሽ ነዉ?  አወ ተደጋጋሚ ጥያቄ ?

ያኛዉ ዘራፊ ወንድምሽን ግባ ማትይዉ ለምንድን ነዉ ? የት ይግባ ፦ ለመንግስት እጁን ይስጥ ኢ መደበኛ አደረጃጀት ፈጥሮ የዲያስፖራን ኪስ እያወለቀ 2 መንግስት አማራ ክልል ላይ የለም ጭቅጭቅ ውስጥ ገባን ታላቅ ወንድሜ ልጅ ትተሽ ያስሩሻል ዝም በይ ለኛ ቀን እስኪወጣ በማለት ክፉኛ አለቀሰ አልቻልኩም

እኔ ደግሞ አንተ ወንድ ልጅ ነህ ለሀገርና ለህዝብ ሚከፈል ዋጋ ስለሆነ ደስ ሊልህ ነዉ ሚገባ ” እንኳን አንተን የ 3 አመት ህፃን ያስሩ አይደል ” ብየ ጮክ ብየ ተናገርኩ የወንድሜን እንባ ሳይ ውስጤ ግሏል ራሴንም አልተቆጣጠርኩ ከዚያ በኋላ ሊይዙኝ ሲሮጡ ጫካ ገብቼ አመለጥኩ ዛሬ ደግሞ አጎታችንና ሌላ ቤተሰብ አምጥተዉ እያሰቃዩ ነዉ ከእኛ ቤተሰብ 3 ቱ ታሰሩ 5 ቱ ገና ተፈላጊ ነን ይህንን ሳያዉቅ ሀገር ጤና ብሎ የተቀመጠ የእነብሴ ህብዝ ይኖር ይሆን ?

የአብይ መንግስት ከህወሀት ሚለይበት መንገድ ምን ይሆን ?

ህዝብ ይስማ ሀገር ይወቅልን ❗

ዘገባው—-ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ

Filed in: Amharic