>

"ከፋኖ ጋር ባለው ግጭት ኦህዴዶች  ሳይሆኑ ብአዴኖች ናቸው የሚሞቱት...!!!"  (ግርማ ካሳ)

“ከፋኖ ጋር ባለው ግጭት ኦህዴዶች  ሳይሆኑ ብአዴኖች ናቸው የሚሞቱት…!!!”

ግርማ ካሳ


*…. ሰዎቹ በጣም ጭፍን ፣ ደንቆሮ፣ ከታሪክ መማር የተሳናቸው፣ ዞር ብለው ሜዳ ላይ ያለውን ሁኔታ መገንዘብ ያልቻሉ፣ ትንሽ እንኳን እንጥፍጣፊ ማስተዋል ካላቸው፣ በአማራ ክልል በፋኖ ላይ እየወስዱት ያለው አሳፋሪ  ተግባር በአስቸኳይ ማቆም አለባቸው…!

 

ወገኖች በአማራ ክልል የትጥቅ ትግል ተጀመሯል፡፡ በአገዛዙ ላይ የሽምቅ ዉጊያዎች፡፡ በርካታ የአገዛዙ ታጣቂዎች እየተገደሉ ነው፡፡ የአገዛዙ ታጣቂዎች እርስ በርሳቸው በአንዳንድ ቦታ መቷከስ ጀምረዋል፡፡ ሕግን የማስከበር ዘመቻ የሚሉት ኝ ሕኝ የማስቀከበር ሳይሆን ሰላማዊ ቦታዎች የማሸበር ተግባር የምለው እንቅስቃሴ፣ አላማዋን የፋኖ መሪዎች በማሰር ፣ የፋኖን እንቅስቃሴ ዜሮ ማስገባት ነበር፡፡ ግን ይህ ዘመቻ ሙሉ ለሙሉ ከሽፏል፡፡

ብልጽግናዎች ጀነራል ተፈራ ማሞን የሽብር ክስ ነው  የመሰረቱባቸው፡፡ ህዝብን ማገለግል፣ ለሕዝብ መቆም በብልጽኛዎች አሸባሪነት ነው፡፡

ሰዎቹ በጣም ጭፍን ፣ ደንቆሮ፣ ከታሪክ መማር የተሳናቸው፣ ዞር ብለው ሜዳ ላይ ያለውን ሁኔታ መገንዘብ ያልቻሉ፣ ትንሽ እንኳን እንጥፍታፊ ማስተዋል ካላቸው፣ በአማራ ክልል በፋኖ ላይ እየወስዱት ያለው አሳፋሪ ተግባር በአስቸኳይ ማቆም አለባቸው፡፡

ይህን አሳፋሪ ድርጊታቸውን ካአልቆሙ፣ የተጀመረው የትጥቅ ትግል የበለጠ ይጠናከራል፡፡ ለምን ሕዝብ የደገፈው እንቅስቃሴ ምን ጊዜም አሸናፊ ስለሚሆን፡፡

የሚያዋጣቸውም ይከው በህዝብ ላይ ትልቅ በደል ከፈጸመችው ሕወሃት ጋር እየተደራደሩ የለም እንዴ ? ከነ ዘመነ ካሴ ጋር ይልቅል ከፍያለ ቁጭ ብሎ መደራደርና ክልሉን ሰለማዊ የተረጋጋ እንዲሆን ማድረግ መቻል አለበት፡፡ ለአብይ አህመድና ኦህዴድ አሽከር አልሆንም ብሎ ቢያንስ አሁን እንኳን የሕዝብ ፍላጎት ለማስፈጸም ይስራ፡፡ ሰው ከሆነ ማለት  !!!!!

ክልሉ ውደ ባሰ ጦርነት እንዲገባ መደረግ የለበትም፡፡ ይሄንን እነ አብይ አህመድ ይፈልጉት ይሆናል፡፡ በክልሉ እርስ በርስ መገዳደል ቢኖር፡፡ እርስ በርስ ሲሰባሰቡ “የት አባታቸው፣ አባላናቸው ” ብለው ነው የሚደሰቱት፡፡

ግን  በአማራ ክልል ያሉ ብልጽግ ናዎች ከፋኖ ጋር በመላተማችው የሚያተርፉት ነገር የለም፡፡ በመሃል የሚጎዱት፣ የሚሞቱት እነርሱ ናቸው የሚሆኑት፡፡

Filed in: Amharic