የድሬዳዋውን ድምፅ አፈኑት…!!!
የኋላሸት ዘሪሁን
” ሁሌም “ሌብነታችሁን ስታቆሙ” እኔም ጩኸቴን አቆማለሁ” ይላቸዋል… በጥቅማጥቅም ዝም ሊያሳኙት ባለመቻላቸው ዛሬ አፍነው ወስደውታል…!!!
የፍቅር ያሸንፋል ማህበር መስራች አባል የሆነው በቃል ድሬዳዋ ከተማ ላይ ስለሚፈፀመው ሌብነት በተደጋጋሚ ጮኋል ፤በከተማ መስተዳድሩ ውስጥ የተሰገሰጉትን ሌቦች በማስረጃና በመረጃ በተደጋጋሚ አጋልጧል፤ ይሄም ከከተማዋ ከንቲባ እና የሌብነት ሰንሰለቱ ተጠቃሚዎች ጥርስ አስነክሶበታል ።
በነገራችን ላይ በቃል በከተማዋ ላይ እሚፈፀመውን በደል ማጋላጡን ካቆመ ጠቀም ያለ ነገር እንደሚሰጠው እየነገሩት በተደጋጋሚ ሊያባብሉት ሞክረዋል የእርሱ ምላሽ አንድና አንድ ነበር ።
“ሌብነታችሁን ስታቆሙ” እኔም ጩኸቴን አቆማለሁ”እሚል ነው። ከዚህም የተነሳ በተደጋጋሚ እንደ ሚዝቱበት ነግሮኛል ። እውነት ትዘገያለች እንጂ መቼም ተቀብራ አትቀርም ፍትህ ለወንድማችን በቃል ( Bekal Dire)