>
5:13 pm - Friday April 20, 1714

ፖሊስ በጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ጉዳይ ላይ  ምላሹን እንዲያቀርብ አምስት ቀናት ተሰጠው...!!! (ኢትዮ ኢንሳይደር)

ፖሊስ በጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ጉዳይ ላይ  ምላሹን እንዲያቀርብ አምስት ቀናት ተሰጠው…!!!

ኢትዮ ኢንሳይደር


የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በእስር ላይ የሚገኘው የጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ጉዳይ መታየት ያለበት “በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ነው” በሚል በተጠርጣሪው ጠበቃ ለቀረበለት አቤቱታ የፖሊስን ምላሽ ለመቀበል ለመጪው ረቡዕ ሰኔ 8፤ 2014 ቀጠሮ ሰጠ። ፍርድ ቤቱ ቀጠሮውን የሰጠው፤ በትላንትናው ዕለት በመርማሪ ፖሊስ በተጠየቀው ተጨማሪ 14 የምርመራ ቀናት ጉዳይ ላይ ትዕዛዝ ሳይሰጥ ነው።

አራት ኪሎ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ግንቦት 19፤ 2014 በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ጋዜጠኛ በቃሉ፤ በፍርድ ቤት የተፈቀደበትን 12 ቀናት የምርመራ ጊዜ ያጠናቀቀው ትላንት ሐሙስ ነበር። የጋዜጠኛውን ጉዳይ የሚመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት፤ ፖሊስ በተፈቀዱለት የምርመራ ቀናት ያከናወናቸውን ተግባራት ለማድመጥ ለትላንት ሰኔ 2 ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር።

መርማሪ ፖሊስ በትላንትናው ዕለት በጹሁፍ ለችሎቱ ባስገባው ደብዳቤ፤ “ወንጀሉ ውስብስብ በሀገር ላይ እና በህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለ” እና “ሰፊ ጊዜ የሚጠይቅ መሆኑን” በመጥቀስ ፍርድ ቤቱ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲፈቅድለት ጠይቋል። ፖሊስ ተጨማሪ ጊዜውን ከጠየቀባቸው ምክንያቶች አንዱ  ተጠርጣሪውን በተለያዩ መንገዶች በገንዘብ እየረዱ ያሉ ግለሰቦችን በመለየት በቁጥጥር ስር ለማዋል መሆኑን አስታውቋል።

ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2022/7119/

Filed in: Amharic