ዋስትናው ተሻረ …
ኢትዮ ኢንሳይደር
*… የከፍተኛው ፍርድ ቤት በጽ/ቤቱ በኩል የፖሊስ ጊዜ ይራዘምልኝ ጥያቄን ተቀብሎ ለሰኔ 10/2014 ዓ.ም ቀጠሯ በመስጠቱ ጋዜጠኞቹ ወደ እስር ቤት ተመልሰዋል::
ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ እና ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ የተፈቀደው የ10 ሺህ ብር ዋስትና ተሻረ ።
ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን የሻረው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በዋስትና ትዕዛዙ ላይ ይግባኝ ካቀረበ በኋላ ነው።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 2 ቀን 2014 ከሰዓት በጽህፈት ቤት በኩል በሰጠው ትዕዛዝ ለመርማሪ ፖሊስ የ8 ቀናት የምርመራ ጊዜን ፈቅዷል።
ዛሬ ሰኔ 2/2014 ዓ.ም የኮሚሽኑን መርመሪ ፖሊስንና የጠበቃን ሃሳብ ምርመምሬለሁ ያለው የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ለፖሊስ የበለጠ ጊዜ ስለሚያስፈልገው በማለት የእስር ፍርድ ቤቱ የሰጠውን የዋስትና መብት በማንሳት በጽ/ቤቱ በኩል የፖሊስ ጊዜ ይራዘምልኝ ጥያቄን ተቀብሎ ለሰኔ 10/2014 ዓ.ም ቀጠሯ በመስጠቱ ጋዜጠኞቹ ወደ እስር ቤት ተመልሰዋል::
ፖሊስ በመጀመሪያ ጋዜጠኛ ተመስገን ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት በዩትዩቦች ይጠቀማል አሉ፤ ከአስር ቀን ቀጠሮ በኋላ በዩትዩብ ሳይሆን በፍትሕ መፅሔት ይጠቀማል አለ፤ ፍርድ ቤቱ ይሄን ተከትሎ በዋስ እንዲወጣ ወሰነ፤ ትላንት ፖሊስ ይግባኝ ብሎ ወንጀሉ ውስብስብና ሌሎች አባሬዎች አሉ አለ፤ ዛሬ ሰኔ 2/2014 ደግሞ ፖሊስ 8 ቀን ወስዷ ምርምሮ ለሰኔ 10/2014 በድጋሚ ያቅርባቸው ብሎ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ወሰነ::