ፋኖን ለማፈን የተሰማራው የአገዛዙ ሰራዊት እርስ በእርሱ ተዋጋ…!!!
ጌጥዬ ያለው
*… የእዙ ም/አዛዥ ተገድሏል
/
ፋኖን ለማፈን በምዕራብ ጎጃም ዞን፤ በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ የተሰማራው የአገዛዙ ሰራዊት ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. እየተዋጋ ነው። በወረዳው ወንዳጣ ቀበሌ፤ ማርያም ተራራ አካባቢ በሚገኝ ጫካ የእርስ በእርስ የተኩስ ልውውጡ አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን በስፍራው የተሰማራው ሰራዊት ምክትል አዛዥ ከበታች የሰራዊት አባሉ በተተኮሰ ጥይት መገደሉን ከስፍራው የመረጃ ምንጮች አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ አንድ ሌላ ወታደር በጥይት ቆስሎ ወደ ባሕር ዳር ከተማ ተወስዷል። አስቸኳይ ሕክምና ይደረግለታል የሚል ግምት አለ።
ሰራዊቱ ፋኖዎችን አፍኖ ለመያዝ ብሎም ለመውጋት በቦታው ከተሰማራ ቀናት ቢቆጠሩም ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አንድም ፋኖ አልያዘም።