>

 ምርኮኛ ጠቅላይ! (ዘምሳሌ )

 ምርኮኛ ጠቅላይ!

ዘምሳሌ 

ቃልኪዳን ሲገባ ሀ ብሎ ሲጀምር

ስልጣን ተረክቦ ህዝብ አዳም ሲያማርር

ወስዶ እንጅ መንሻ  ሀገር የሚገብር

የዘመኑ  ጠቅላይ   ስራው  የሚያሳፍር

ነጋሪት ምህላው የጠንቋይ ስብከቱ

በይስሙላ ፀሎት ጅኒ እየጎተቱ

ጋዜጠኛ አሳዳጅ የሚጠልፍ ከቤቱ

ኒሻን ተሸላሚው  ህዝብን እያገቱ

ሳይለፉ  እየጫኑ  ስልጣን ዶክተሬቱን

ሀገር እየካዱ ህዝብና መሬቱን

መግደል መሸነፍ  እያሉ ሲዋሹን

በዘር ተደራጅተው  በግላጭ ሲያስፈጁን

ሕገደንብ  ጠባቂ የለውጥ አራማጆች

ስመጥር  ኦህዴድ  ወያኔ  ምርኮኞች

ያገሪቱን መሬት በጅምላ  ሸቃጮች

መሬትና ህንፃ  ብልፅግና አዳዮች

ብር እያሳተሙ ህዝብ እየሰደቡ

ባንክ  እየዘረፉ ሲወጡ ሲገቡ

ጎሳ ጅኒ ብለው ወርደው የሚጠቡ

ይቅርታ  እያሉን መአትን የሚያዘንቡ

የአባጅፋር  ቅሬት በሻሻው  ወታደር

ምን እንደሁ የማያውቅ ሀገር ማስተዳደር

ያገር መሬት ሰጥቶ ስልጣኑን ሲማትር

ልክስክሱ ሁሉ  ከርሱ ጋራ የሚያብር

በማይፀና  ሹመት ሰራዊት  ገንብቶ

ካርዶች እያተመ ሽልማትን ሰጥቶ

ፋኖን  ለመበተን ሸኔን አደራጅቶ

ሳይለፋ  መሪነት  ባጋጣሚ አግኝቶ

ኢትዮጵያ ስላለ  በቃሉ ተጠምደው

በፓርላማ ዙሪያ ስሩ  አሸርግደው

ስልጣን ለመጋራት  ህዝባቸውን ትተው

በርሱ ክፉ ምላስ  አቅላቸውን ስተው

ደናቁርት ምሁራን  አዋቂ ነን ባዮች

ሀገር  ስትፈራርስ  በቁም ተመልካቾች

ህዝብ ሲፈናቀል  ዳንኪራ ረጋጮች

የዘመኑ ተውሳክ የኢትዮጵያ ቫይረሶች

ድንበሯ ተጥሶ ሀገር ውላ ከርማ

ሰላም በሀገር ጠፍቶ  ፓርኮችን ሲያለማ

አንድ ቤት ጠግኖ ሺውን የሚያስቀማ

የዘመኑ ጠቅላይ ዜማው  ብቻ ኦሮሙማ

ለራስ ብቻ ዝና ጠንክሮ ሲሰራ

ሀገር አስረክቦ በጉራ እያወራ

ህሊናው ምርኮኛ  ለቅኝ ገዢ ሴራ

ሀገር  ያደከመ በየሁሉ ጎራ

ህዝቤ  ሆይ  ተነሳ  ስቃይህ ያባራ

በምርኮኛ ጠቅላይ  መቼም አትመራ!

ዘምሳሌ የኢትዮጵያ ልጅ!

Filed in: Amharic